dbu11 | Unsorted

Telegram-канал dbu11 - DBU Daily News

14219

Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact

Subscribe to a channel

DBU Daily News

የዘገዩ ወይም ያልተመለሱ ጥያቄዎች ከተማሪዎች በድጋሜ እየቀረቡ ይገኛሉ።

እነዚህም
   ያሉት የዋይፋይ መስመሮች ሁሉንም የኮምፒውተር መሳሪያዎች የማያስጠቅሙ (Device compatibility ) ከመሆናቸውም በላይ በዶርም እና በመዝናኛ አካባቢዎች ላይ ጥገና ይደረግላቸዋል ተብሎ ጭራሹን መፍትሄ አላገኙም። ጥያቄ 1

ከካፌ ውጪ (Non-Cafe) ተጠቃሚዎች የኮስትሼሪንግ ክፍያ ወቅቱን ጠብቆ ያለመከፈል ጉዳይ የተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥያቄ ሆኗል። ጥያቄ 2

የላይብረሪ ፀጥታ ጉዳይ በተደጋጋሚ የተነሳ እና ለጊዜው መፍትሄ እያገኘ ወዲያው የሚያገረሽበት ጉዳይ ሆኗል። ጥያቄ 3

እነዚህንና መሰል ጥያቄዎች በተለያየ መንገድ ለቻናላችን የቀረቡ ናቸው። በእያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲ አመራር ደረጃ ላይ የሚመለከታችሁ አካላት ተማሪዎች ለጥያቄዎቻችን መልስን ከእናንተ እንሻለን ይላሉ....

ተጨማሪ ያልጠቀስናቸው ነጥቦች ካሉ በኮሜንት ስር ማቅረብ ትችላላችሁ።

@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

ማስታወቂያ ከደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ምርምር እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክቶሬት👆👆👆።




@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

ከነገ እሮብ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ለተመራቂ ተማሪዎች አገልግሎት መስጠት ያቆማል።

ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ አሳስቧል።

@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

Bezawit Getu

Psychology department
4.00

የ2017 የግማሽ ዓመት ከሴቶች አንደኛ በመውጣት ተሸልማለች።

መልካም የስራ ዘመን!
@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1811 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የሚዲያ አካላት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ተመራቂ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታውና በተከታታይ ፕሮግራሞች የካቲት 30/2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ድግሪ 1549 እንዲሁም በ2ኛ ዲግሪ 46 እና በክረምት (PDGT) 216 በጠቅላላው 1811 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 527 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

DBU Daily news የምርቃት ዝግጅቱን በቀጥታ Live stream እያስተላለፈው ይገኛል።

@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

እንኳን ደስ አላችሁ ።

የምርቃት ስነስርዓቱ ከ1:00 ሰአት ጀምሮ በአዳራሽ ውስጥ ቦታ በመያዝ ይጀምራል ።

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

The graduation ceremony is Loading.....

በአጋማሽ የበጀት አመት ምርቃቱን የሚያደርገው 2013 ባች ከነገ በስትያ ይመረቃል። በትላንትናው እለት ሐሙስ ምሽት ማለት ነው በህይወት ሆቴል እና ጌትቫ ሆቴል የመጨረሻውን የራት ፕሮግራም አድርጓል። ይህ ባች
👉አስደሳች የመውጫ ፈተና ውጤት አስመዝግቧል።
👉 በተለያዩ መሰናክሎች ምክንያት ከትምህርት ፍኖተ ካርታ ውጭ ተጨማሪ አንድ አመት ዩንቨርስቲ ቆይታውን አድርጓል።
👉 ተቋርጦ የነበረውን እና በዚህ አመት የተካሔደውን የዩንቨርስቲዎች ስፓርታዊ ውድድር ዩንቨርስቲውን በመወከል ከሌሎች ባቾች ቀዳሚ ነው ።
👉 በውጥረት እና crash program ሒደት ትምህርቱን አጠናቋል።
👉 ትምህርት ላይ ማሳለፍ ካለበት ጊዜ በ 5 ዓመት ውስጥ ምንአልባትም ዝቅተኛውን የዩንቨርስቲ የትምህርት ቆይታ አድርጓል።

ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ በያዘነው academic calendar (የትምህርት ዘመን) አዲስ ቅርንጫፍ(Branch) በመክፈት የካምፓሶቹን ብዛት 3 አድርሷል።
በ 10 ኮሌጅ ውስጥ በ118 የትምህርት ክፍል ከ 17600 ተማሪ በላይ እያስተማረ ይገኛል።

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

አዲስ ፕሬዚደንት -ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ

አስማረ መለሰ(ዶ/ር) የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትነትን ከዶ/ር ንጉስ ታደሰ ተረክበዋል።

መልካም የስራ ዘመን!

@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ከ ፊታችን ሚያዝያ ወር ጀምሮ የህግ ድጋፍ ሰጭ የህግ ተማሪዎችን (paralegals) አወዳድሮ ማሰልጠን ይፈልጋል።

በመሆኑም 3 ተኛ እና 4 ተኛ አመት የህግ ተማሪዎች በሚከተሉት የመወዳደሪያ ነጥቦች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን CGPA 60%, Motivation (cover letter) 20%, Extra curriculum activity (Certificate) 15% and affirmative action 5%

ምዝገባውን በህግ ትምህርት ክፍል ቢሮ ሔዳሁ ማድረግ ትችላላችሁ። ለበሐጠ መረጃ ከላይ የተያያዘላችሁን ማስታወቂያ ያንብቡ።

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

❗❗ NOTICE ❗❗

ለሁሉም መደበኛ እና ሪሚዲያል ተማሪዎቻችን

እንደሚታወቀው ተማሪዎቻችን ወደ ጊቢ ስትገቡ ለንብረታችሁ የራሳችሁን ጥንቃቄ እንድታደርጉ በተለያዩ ጊዚያቶች ግንዛቤ ስንሰጥ መቆየታችን ይታወቃል። ይህንን ትምህርት ተግባራዊ የሚያደርጉ ብዙ ተማሪዎቻችን ቢኖሩም አንዳንድ ተማሪዎቻችን ደግሞ ሀሳቡን ችላ በማለት ማታ ተኝተው ጠዋት ላይ ሲነቁ የዶርማቸው ቁልፍ ሳይሰበር ፣ መስታወት ሳይሰበር ሞባይል ጠፋኝ በማለት ወደኛ ቢሮ ፣ ወደተማሪዎች ህብረት ቢሮ ፣ ወደተማሪዎች አገልግሎት ዲን ቢሮ ሁኔታው ይታይልኝ በማለት ይመጣሉ። እኛም በዶርም ያደሩትን ተማሪዎች ጠርተን ስናናግራቸው ''ሞባይሉን ማን እንደወሰደው እናውቅም ፤ ከዶርማችን ሌላ የመጣ ተማሪ የለም'' በማለት መካካዶች እና አለመተማመኖች እየታዩ ተማሪዎቻችን ጭቅጭቅ እና ንትርክ እየተፈጠሩ ጊዜያቸውን ያለአግባብ እያባከኑ ስለሆነ እና በጓደኝነትም ላይ ቅራኔ እየተፈጠረ ስለሆነ ከዚህ ችግር ትምህርት በመውሰድ ሳይቃጠል በቅጠል እንደተባለው ሁላችሁም ተማሪዎቻችን ለንብረታችሁ በተለይም ለሞባይላችሁ እና ለላፕቶፓችሁ የየራሳችሁን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ልናሳስባችሁ እንወዳለን።

ለራሳችን ንብረት ጥበቃ እራሳችን ዘብ እንቁም
ያለ ህዝብ ተሳትፎ ወንጀልን መከላከል አይቻልም

ከ ደ/ብ/ዩ የሰላምና ደህንነት ስራ አስፈፃሚ ቢሮ

Читать полностью…

DBU Daily News

🚨 IMPORTANT ANNOUNCEMENTS ! 🚨

🎉 3 ቀን ብቻ ቀርቷል! 🎉

"A NIGHT TO REMEMBER" 🎶✨ በፕሮም Night ለመፍታታት ዝግጁ ነዎት? 🎊🎶

📅 ቀን: የካቲት 27
📍 ቦታ: ሂዎት ሆቴል – አጼ ዘረ ያቆብ አደባባይ
👗 የልብስ ሁኔታ: ሱፍ / የምሽት ቀሚስ

💃🕺 በመጪው ሐሙስ የሚደረገውን የዓመቱ ትልቁን event ፕሮም አይቀርም! 🔥 🎶

🎟️ ትኬት ለማግኘት በውስጥ ያናግሩን ወይም ይደውሉ:

📩
@sup_life

📞
0953947055
📞
0914718311

ወይንም በአካል ከጊቢ ፊት ለፊት ሻይ/ቡና የሚገኘው ወይንሸት ጋር

⏳ ያለን ቦታ ውስን ነው ፈጥነው ቦታ ይያዙ! 🎊🔥

HOSTED BY: ZB EVENT
SPONSOR: HABESHA BEER

#ANightToRemember 💫 #DBUProm2025 🎭 #ፕሮም2025


@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

የደ/ብርሃን ዩኒቨርስቲ መ/ሜዳ ግቢ ሰራተኞችና ተማሪዎች 129ኛውን የአድዋ ድል በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበሩ።ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ በታሪክ ት/ት ክፍል መምህር ጌትዬ ጎሳ ቀርቦ በበዓሉ ተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል።
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ትምህርት ሚንስቴር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) በያዝነው የትምህርት ዘመን ሰኔ ወር ላይ ብሔራዊ የዩንቨርስቲ(Exit exam) ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ገልፃል። ኢትዮ ቴሌኮም እና ኢትዮ ፓስት ለዚሁ ስራ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለምዝገባ ይገባሉም ብሏል።


@dbu 11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

🌙 የረመዳን ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ 1446-ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ፆም ነገ ወይም ቅዳሜ ቀን ይጀመራል።

ለእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ፆም ይሁንላችሁ።

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የቤተ መፀሀፍ ሰራተኞች እየረበሹን ነው የተማሪዎች ቅሬታ እንደወረደ 📌📌


Selam endet nachu dbu daily news yhin merja ለሚመለከታቸው በሙሉ አድርሱልን የዶ/ር ከበደ ሚካኤል ቤተ መፃሃፍት ሰራተኞች ስራቸው ሚያውቁት enkuwan aymeslum ተማሪ በማይረብሽበት ስዓት ensu በጣም eyerebeshiun deee
1 ensu sifelgu bicha yaleminm air phone video yadamitalu
2 misa sat ena yemata fereka bemigebbu et sat yalemakuware letewese dekikawechi mawrat yetelemede new enzhi negerochi endistekakel adrguln


NB :በሁሉም ላይብረሪዎች ወስጥ ፅጥታ ሊከበር ይገባል ።

እየተረበሽን ነዉ

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የእግርኳስ ክህሎት ያላችሁ ከ 1ኛ እስከ 3 ተኛ አመት የዩንቨርስቲው ተማሪዎች በሙሉ👆👆👆👆

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

ከሳይኮሎጂ ዲፓርት መንት ቤዛዊት ጌቱ የማይህበራዊ እና ስነ-ሰብ ሳይንስ ኮሌጅን ሜዳሊያ እንዲሁም የዩንቨርስቲው ሴት ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

እንኳን ደስ ያለሽ

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረብርሀን ዪንቨርስቲ በተለያዬ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን ከ1800 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል በመጨራሻም ዕጩ ተመራቂዎች በዛሬው እለት ጉንጉናቸውን (መነሳንስ) ከ ቀኝ ወደ ግራ አደረጉ (ምርቃታቸውን አበስሩ)። 2013 ዎቹ አስደምመውናል ዛሬ። ተማሪ አስማማው ሽፈራው ከ ማርኬቲንክ ትምህርት ክፍል 44 ኮርሶችን A+ በማምጣት 4፡00 በመስራት የ 17 ኛውን ዙር ምርቃት የዩንቨርስቲውን ዋንጫ አንስቷል። የሚገርም consistency! ከውስጥ መስመር በደረሰን መረጃ የ ሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል ዕንስት ደግሞ በ 40 A+(charge) ትከተለዋለች። well done አስማማው በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ ተመራቂዎች።
attached photo 👉 Gold Medalist Asmamaw shiferaw

@bu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

የተመራቂ ተማሪዎች የሰርተፍኬት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል ሙሉ የሽልማት መርሃ ግብሩን የምንለቅ ይሆናል።

Читать полностью…

DBU Daily News

ውድ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ለምትናፍቋት ለዚህች ቀን እንኳን አደረሳችሁ።

ዩኒቨርሲቲው ለ17ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል.

@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

እንኳን ደስ አለሽ ፅዮን ሙሉነህ

ላላፉት 2 አመታት በቻናላችን አድሚን በመሆን መረጃን በማድረስ ስትሰራ የነበረችው አባላችን ጋዜጠኛ ፅዮን ሙሉነህ ተመርቃለች ።

ላደረስሽው መረጃ : ለነበረሽ አገልግሎት ቻላናችን DBU DAILY NEWS ያመሠግናል 🤚🙏🙏።

በቀጣይ የህይወት ምዕራፍሽ ስኬታማ ጋዜጠኛ እንደምትሆኚ ቻናላችን ይተማመናል : መልካሙ ሁሉ ይግጠምሽ ።

በቀጣይም ከእኛ ጋር ስለምትሆኝም እናመሠግናል ።

እንኳን ደስ አለሽ !

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

#A night to remember

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

Looking for LinkedIn Account Owners to Rent? 🔑
💼 LinkedIn Rental Center is ready to help you earn extra income from your LinkedIn account!
🔹 We are looking for LinkedIn accounts with complete and credible profiles to rent out.
🔹 Get paid by renting your LinkedIn account to us.
🔹 We guarantee the security and confidentiality of your data.
👉 Benefits of Joining:
✅ Extra income without being active
✅ Your LinkedIn account stays safe and secure
✅ Easy and fast process
If you have a LinkedIn account that meets the criteria, contact us now and get the best offer! 📩 inbox me
Telegram
@awashpromotion1
WhatsApp number +251983919153

Читать полностью…

DBU Daily News

አዲሱ የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ስራ ጀምረዋል ።


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአመራር ለውጥና የስራ ርክክብ አደረገ።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከ ደብዳቤ መሰረት የአመራር ለውጥ ያደረገ ሲሆን የቀድሞ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር ) አስማረ መለሰ (ዶ/ር ) ተክተው የካቲት 25/2017 ዓ.ም የስራ ርክክብ በማድረግ በይፋ ስራቸውን ጀምረዋል።

ባላፉት አምስት አመታት ዶ/ር ንጉሱ ታደሰ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል ።

መልካም የስራ ዘመን ።

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

በዛሬው ዕለት

የሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን ከደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ የአፄ ዘረ ያዕቆብ የባህል የቋንቋ እና የታሪክ ማዕከል ጋር እንዲሁም ከሶሻል እና ሂውማኒቲ ኮሌጅ ጋር በመተባበር 129ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ መታሰቢያ በደማቁ አክብሯል።

በዕለቱ አድዋን የሚዘክሩ የተለያዩ መርሀግብሮች ተሰናድተው የቀረቡ ሲሆን ሆሄ ተስፋ የኪነ ጥበብ ቡድንም በተለያዩ ጥበባዊ ዝግጅት ዕለቱን አድምቆ ውሏል።

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

በበመሪቂያ አዳራሽ ልዩ የአድዋ መታሰቢያ ዝግጅት (በዋና ግቢ)

አድዋ
ነገ ሰኞ የካቲት 24/2017ዓ.ም ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን ከሶሻል እና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ እንዲሁም ከ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የባህል የቋንቋ እና የታሪክ ማዕከል ጋር በመተባበር 129ኛውን የአድዋ መታሰቢያ ልዩ መርሀ ግብር ስለሚቀርብ ከጠዋት 2:30 ጀምሮ በመመረቂያ አዳራሽ እንድተገኙ ግብዣችን ነው ።

@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

፨የምኒልክ ሐውልት እውነታዎች፨
፧መታሰቢያነቱ- ለዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ንጉሠ ነግሥት ዘኢትዮጵያ
፧ሐውልቱን ያሠሩት- ልጃቸው ንግሥት ዘውዲቱ
፧ሐውልቱ የተሠራበት ሀገር- ጀርመን
፧ሐውልቱ የተሠራበት ማዕድን- ነሐስ
፧ሐውልቱን የሠራው ባለሙያ- ሐርሲል የተባለ ጀርመናዊ
፧ሐውልቱ ተመርቆ ለሕዝብ የተገለጠው- ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም.
፧ሐውልቱ ተመርቆ የተከፈተው - በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን የንግሥ በዓል ዋዜማ ዕለት
፧ንግሥት ዘውዲቱ ለምረቃው ዕለት ሳይደርሱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
።።።።ከምኒልክ ሐውልት በስተግርጌ የተጻፈ።።።።
"ከትልቅ ወይም ከትንሽ መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ
ነው።"
፧በጣሊያን ወረራ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተነቅሎ እንዲቀበር ከተደረገ ከዓመታት በኋላ
በአርበኞቻችን ተጋድሎ ጠላት እንደተሸነፈና ከሀገር እንደወጣ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ
አሁን ባለበት ሁኔታ በ1934 ዓ.ም. ሚያዝያ 28 ቀን ፊቱን ወደ ሰሜን አድርጎ እንዲቆም
ተደረገ።
(ምንጭ:- ኅብር ኢትዮጵያ፤ ቴዎድሮስ በየነ)

ከ እናንብብ እናብብ የቴሌግራም ገፅ የተወሰደ

እንኳን አደረሳችሁ!

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የባህል፣ ታሪክ እና ቋንቋ ልማት ማዕከል እንዲሁም ማኅበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ ትብብር የተሰናዳ ታሪካዊ ዝግጅት!!!

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ማስታወቂያ
ሴቶችና ህጻናት ቢሮ የኢኮኖሚ ድጋፍ የምትጠቀሙ ተማሪዎች በሙሉ ፡

20/06/2017 ዓ.ም እስከ 21/06/2017
ድረስ በመምጣት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
ቢሮ ቁጥር - 38- 2 ፎቅላይ በመምጣት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
@dbu11
@DBU111

Читать полностью…
Subscribe to a channel