Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
የደብረብርሐን ዩንቨርስቲ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበብ አባላት ጨምሮ 48ቱም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የተሳተፉበትን የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከግንቦት11- 12/2017ዓ.ም በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል በአካሄደው አገር አቀፍ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የወጣቶች የሥነ-ምግባር አምባሳደርነት የዕውቀት፣ የአመለካከት እና የተግባር አቅም ግንባታ ጥያቄ እና መልስ የማጠቃለያ ውድድርን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር አምባሳደርነት ውድድር 1ኛ በመሆን አሸናፊ ሆነ።
በውድድሩ ለተሳተፉ ለ5ቱም የዩኒቨርሲቲው(ጎንደር) ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በብር 180 ሺ/አንድ መቶ ሰማንያ ሺ ብር የተገዛ ዘመናዊ ላፕቶፕ እና መፅሀፍ ተሸልመዋል።
በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ዩኒቨርስቲዎች የዋናጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
@dbu11
@dbu111
ከሳምንታቶች በሗላ ብሔራዊ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) አንዱ አስፈላጊ ዶክመንት በመሆኑ ነገር ግን በተለያዬ ምክንያት እና ችግር national ID ያልያዛችሁ (ያላገኛችሁ) ተማሪዎች national ID support team ይኽንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀላሉ ከታች የተቀመጠላችሁን የgoogle form መጠቀም እንደምትችሉ ገልፃል። ሊንኩን በመንካት አፋጣኝ ምላሽን በዛ በኩል ማግኘት ትችላላችሁ google form Link 👉https://forms.gle/4a9NBgKF94JR5qGB7
በተጨማሪም ለዚሁ አገልግሎት በከፈቱት የቴሌግራም ግሩፓቸው ላይ ጥያቂያችሁ በተቻለ መጠን በቶሎ እንዲመለስ 29 ዲጂት የምዝገባ ቁጥራችሁን እና የተመዘገባችሁበትን ስልክ ብቻ በመላክ እርዳታቸውን ማግኘት ትችላላችሁ።
national ID support telegram group👉/channel/+bPjoXp1TQBdhN2E8
@dbu11
@dbu111
ዛሬ በተደረገ GC cup (የዕጩ ተመራቂዎች) እግር ኳስ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ የምድብ አንድ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው Management Computer science ን በመለያ ምት በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል።
የዋንጫ ግምት ከተሰጣቸው ቀዳሚ ቡድን አንዱ የሆነው Sociology በተመሳሳይ በመለያ ምት (penalty) በጥምር ቡድኑ Biotechnology, geology and psychology ሽንፈትን በማስተናገድ የዋንጫ ጉዞው ተገቷል።
የSociology squad በሐገር አቀፍ የዩንቨርስቲዎች ስፓርታዊ ውድድር ዩንቨርስቲውን በእግር ኳስ ወክለው የተጫወቱ ከ 3 በላይ ተጫዋቾችን የያዘ ስብስብ ቢሆንም ግማሽ ፍፃሜ መድረስ አልቻለም።
ነገ ቀጥሎ በሚካሔደው የምድብ ሁለት ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ
2፡30 ህግ(Law) vs NARM &agroeconomics
4:30 Economics vs Tourism&logistics ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
#be ready with the necessary document
#Notice
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ለተማሪዎቹ ያወጣው ማስታወቂያ።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት መልዕክት ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ👇
የመውጫ ፈተና መሠረት በማድረግ ሙሉ መረጃችሁ national id እና ሌሎችም መረጃዎች ተደራጅተው ወደ ት/ት ሚኒስቴር በቀን 14/02/2017 ዓ/ም ስለሚላክ
በስህተት መረጃችሁ ያልተሟላ ተማሪዎች ከፈተና ውጭ #እንዳትሆኑ ባሉት 2 ቀናት በየዲፓርትመንታችሁ እየሄዳችሁ check list እያያችሁ እንድታረጋግጡ እናሳስባለን ‼️
#ማሳሰቢያ
📝 ሙሉ መረጃው ወደ ት/ት ሚኒስቴር ከተላከ በኋላ ስህተት ያለበት ተማሪ ቢኖር ማስተናገድ የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን። (የአርባ ምንጭ ተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት)
ከATC ገፆች።
@dbu11
@dbu111
ዛሬ የሚደረጉ የመጀመሪያ ዙር የጥሎማለፍ ጨዋታዎች
8:00 ላይ Tourism&logistics ከ Biology,sport and plant science የሚያደርጉት ጨዋታ 7:30 ለይ የሚጀመር ይሆናል።
እንደተለመደው ተጨዋቾች በሰዓቱ እንድትገኙልን እናሳስባለን።
@DBU11
@DBU111
ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን
በዛሬው ዕለት የሆሄ ተስፋ የኪነ ጥበብ ቡድን የዓመቱ የመጨረሻ መድረኩን በደማቅ ሁኔታ አቅርቦ ዋለ።
የግቢያችን ብቸኛው የኪነጥበብ ቡድን ሆሄ ተስፋ የመጨረሻ በሆነው መርሀ ግብሩ ላይ እንደተለመደው ድንቅ ድንቅ ግጥሞች፥ ወግ፥ ሙዚቃዎች (live music) ፥ ተውኔት እና ስነ-ስዕል (live painting) ስራውን አሳይቷል።
@dbu11
@dbu111
✨የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት ከፌደራል ፍትህ እና ህግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከአርብ ግንቦት 8 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የህግ ትም/ት ቤቶች የምስለ ችሎት ውድድር (National moot Court competition) ፍጻሜውን አግኝቶል ።
💺በውድድሩ ላይ 12 ዪኒቨርሲቲይዎች የተሳተፉ ሲሆን የውድድሩ የመጨረሻ ውጤትም የሚከተለው ነው።
1.ቤተልሔም ገበየሁ ጸጋነህ👉National champion Team/የውድድሩ አሸናፊ ቡድን ባህርዳር ዩኒቨርስቲ
ሆኗል።
👉Best Runner Up Team (2ኛ ደረጃን) የያዙት ሰላሌ ዩኒቨረሲቲ ናቸው
👉Second runner up team(3ኛ ደረጃን የያዙት) ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሰሆን
👉Best Memorial Applicant
👉Best Memorial Respondet winner
👉Best orator of the preliminary round competition
እዮብ ይመች ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
👉Best Femal orator of the preliminary round Competition
👉Best orator of the final round competition competition
ማስታወቂያ
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
የወጭ መጋራት ፎርም ለማዘጋጀት አንድ ተማሪ ሁለት (2) ጉርድ ፎቶ 3በ4 የሆነ ስለሚያስፈልግ
በክፍል ተወካያችሁ መሠረት ከቀን 08/9/2017ዓ.ም እሰከ 15/9/2017ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በዋና ሪጅስትራር ስር በወጭ መጋራት ቢሮ ቁጥር- 4 ድረስ እንድታመጡ እናሳስባለን::
ማሳሰቢያ:- ከፎቶግራፍ ጀርባ ላይ ሙሉ ስም እስከ አያት እና ዲፓርትመንት አንድተፅፋ ፤ከቀኑ ካለፈ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
@DBU11
@DBU111
ለተስፋ አዲስ የካንሰር ታማሚ ህፃናት የሚደረገው የደም ልገሳ ፕሮግራም ከአሁን ሰዐት ጀምሮ በዋናው ግቢ ይካሄዳል ።
ኑ በደማችን ታሪክ እንፃፍ
የህፃናቱን ህይወት አብረን እንጠብቅ።
@dbu11
የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት ማህበር(DBU law school association) የስራ ርክክብ አድርጓል።የ 3 ተኛ አመት ህግ ተማሪ አብርሐም ተክሌን የማህበሩ ፕሬዘዳንት እና የአራተኛ አመት ህግ ተማሪ ሀና ዘውዱን ምክትል ፕሬዘዳንት አድርጎ ሾሟል።
አዲስ የተመረጡ የማህበሩ ሰብሳቢዎች እና ስራ አስፈፃሚዎች ማህበራችን በዩንቨርስቲ ውስጥ ካሉ ጠንካራ እና አርዓያ የሚሆን የግቢያችን የውስጥ አደረጃጀት እንዲሆን ከሌሎች ዩንቨርስቲዎች ተሞክሮዎችን በመጋራት ጭምር ለመማር ማስተማሩ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር እና አስፈላጊ ክህሎቶችን ለማዳበር ዕድሎችን ለመፍጠር ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል።
@dbu11
@dbu111
የተማሪዎች ሙያ ማሻሸያ ማዕከል ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች👇👇👇 “Employability and Job
Readiness” በሚል ርእስ በሁለት ዙር ስልጠና ለመስጠት በዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን
የሕግና እንጅነሪንግ ተማሪዎች የመጀመሪያው ዙር ስልጠና (Career focused self-assessment
and understanding the employment world, Job searching Strategies, CV writing, Cover
Letter Development, እና Interview Skill) በተሰኙ ርእሶች በዶ/ር ቤተጊዮርጊሰ ማሞ ግንቦት
10 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 2፤30 ጀምሮ በSE- 06- F2- R05 ይሰጣል፡፡
ዝርዝሩን ከላይ በተያያዘላችሁ ፎቶ ላይ መመልከት ትችላላችሁ።
@dbu11
@dbu111
#Ad
Hp.....pavilion
Core i 3
HDD....512GB
RAM...4GB
can run for 3hrs for single charge
Contact me...0933704204
Price 15K.....negotiable
በዛሬው ዕለት በአስራት ወልደየስ የጤና ግቢ የሕክምና ተማሪዎች የነጭ ጋወን ማልበስ ስነ-ስረዓት (white coat ceremony) ተዘጋጅቶ ውሏል።
ዝግጅቱ ተማሪዎቹ የ3 ዓመት የትምህርት ቆይታቸውን አጠናቀው፤ ነጭ ጋወን ለብሰው፤ ሆስፒታል ላይ ማገልገል መጀመራቸውን ለማብሰር ነው።
የግቢው መምህራን ዶክተሮች፥ የግቢው ነጭ ጋወን ለባሽ ተማሪዎች እና መደበኛ ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን
በቦታው ተገኝተው የነበሩ ዶክተሮችም "ነጭ ጋወን መልበስ ለሀኪም አንዱ ትልቁ መንገድ ነው። ነጭ ጋወን ስትለብሱ ነው ታካሚ የሚለያቹ አምኖ ሕመሙን የሚነግራቹ። እየተቀበላቹ ያላቹት ትልቅ ኃላፊነት ነው። ትዕግስተኛ እንድትሆኑ አደራ!" የሚሉ ንግግሮችን አድርገዋል።
ለተማሪዎቻቸውንም ነጭ ጋወን አልበሰዋል።
ተማሪዎቹም አሁን እስካሉበት ድረስ ላስተማሯቸው መምህራኖች በየትምህርት ክፍሉ የምስጋና ወረቀት እና ለትምህርት ክፍል ኃላፊያቸውም የምስጋና ስጦታ እንዲሁም ለክፍል ተወካዮቻቸውም የምስጋና ወረቀት እና ስጦታ ሰጥተዋል።
ለዝግጅቱ ድምቀት ደግሞ ከዋናው ግቢ የሆሄ ተስፋ የኪ-ነጥበብ ቡድን ቦታው ላይ ተገኝተው በተለያዩ የጥበብ ስራዎች አድምቀውቷል።
የሕክምና ተማሪዎች እንኳን ደስ ያላቹ
@dbu11
ግንቦት ፮ ፲፱፻፺፩ ዓ.ም ከዛሬ ፳፮ ዓመት በፊት አንጋፋውና የመጀመሪያው የሀገራችን የቀዶ ጥገና ሐኪሞ ፕ/ር አስራት ወልደየስ ከዚህ አለም ድካም ያረፉበት ዕለት ነበር።
ከአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ
@dbu11
🚀 DBU HackX 2025 is here!
📍 Debre Berhan University – College of Computing
🗓 May 16–18, 2025
🎯 Theme: Building Tech for Community Impact
💡 Solve real-world problems
👥 Open to all students (no coding required!)
🏆 Prizes • Internet • Certificates
📝 Register now 👉 Here link
📞 Contact: +251 93 646 0356
📌 Follow Us: 💬 Channel 👥 Group 🎥 tech_tonic_tribe">Tik Tok 💼 LinkedIn
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መመዘኛ ፈተናዎችን ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ መስጠት መጀመሩን ገለፀ።
ተቋሙ አብዛኛው የመማር ማስተማር ሂደት ከወረቀት ነጻ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብቴ ዱላ (ዶ/ር)፤ ከአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጀምሮ ፈተና በበይነ መረብ እንዲሰጥ መደረጉን ለኢፕድ ተናግረዋል።
ይህም ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ቀድመው ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
ተማሪዎች ከመደበኛው መማር ማስተማር ሒደት በተጨማሪ በኢ-ለርኒግ የሚማሩበትና የትምህርት ግብዓት የሚያገኙባቸው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች መሟላታቸውን ጠቅሰዋል።
በቀጣይ ወር የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሚወስዱ 1,400 ተማሪዎች ለማዘጋጀት እየተሠራ ነው ብለዋል።
via Ethiopian press agency
@dbu11
@dbu111
#ማስታወቂያ። ከ ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት ለ 5 ተኛ አመት ህግ ተማሪዎች በሙሉ 👆👆👆 student portal is open for such issue. here is the link👉
https://studentportal.dbu.edu.et
@dbu11
@dbu111
#ማስታወቂያ
ለደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች በሙሉ👆👆👆👆👆
@dbu11
@dbu111
ባይንደር [የአጭር ጊዜ ቅናሽ]
የተማሪዎች መመረቂያ ባይንደር ቀድመው ለሚያዙ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
የአንድ ባይንደር ዋጋ
የቀለም ህትመት 270
የሲዘር ህትመት 320
የባይንደር አይነት
መልክ - በርገንዴ፥ሰማያዊ፥ጥቁር
የውስጥ ማቴሪያል- ፋይዜት
የውስጥ መሸፈኛ - ካንጋሮ
የጠርዝ ፍሬም- ጎልድ ብረት ፍሬም
[ ቀድመው በብዛት ለሚያዙም ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል ]
ቅናሹ የሚቆየው ከኦርደር መጨናነቅ ቀድመው ለሚያዙ ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ
0940219376
_inbox @shikret007
ባይንደር
የተማሪዎች መመረቂያ ባይንደር ቀድመው ለሚያዙ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
የአንድ ባይንደር ዋጋ
የቀለም ህትመት 270
የሲዘር ህትመት 320
የባይንደር አይነት
መልክ - በርገንዴ፥ሰማያዊ፥ጥቁር
የውስጥ ማቴሪያል- ፋይዜት
የውስጥ መሸፈኛ - ካንጋሮ
የጠርዝ ፍሬም- ጎልድ ብረት ፍሬም
[ ቀድመው በብዛት ለሚያዙም ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል ]
ቅናሹ የሚቆየው ከኦርደር መጨናነቅ ቀድመው ለሚያዙ ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ
0940219376
_inbox @shikret007
#MoE
በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ያሏቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስፈላጊውን ክፍያ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በርቀት፣ በማታ እንዲሁም በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር የመውጫ ፈተና የሚወስዱ አመልካቾች ክፍያ የፈጸሙበትን የባንክ ደረሰኝ እስከ ማክሰኞ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል eexmoe@gmail.com እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
መረጃው የ ቲክቫ ነው
@DBU11
@DBU111
#Gc cup
ዛሬ በተደረጉ ሁለት የጂሲ ካፕ የመጀመሪያ ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች
በ Law እና በ Accounting መካከል በተደረገው ጨዋታ.
Law 3-1 Accounting በሆነ ውጤት
Law አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፍ እንዲሁም
በ IS እና በ Biotechnology,Geology and Psychology መካከል የተከናወነወ ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ በተሰጠው መለያ ምት Biotech,Geology and psychology አሸንፎ ወደቀጣዩ ዙር አልፏል።
በተጨዋቾች ላይ እያየን ስላለው መልካም ስነምግባር ከልብ እናመሰግናለን።
@DBU11
@DBU111
ታላቅ የኪነ-ጥበብ ድግስ በሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን!
ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን እሁድ 10/09/17 ከ10 ሰዐት ጀምሮ በPR አዳራሽ live music፥ ግጥሞች ወጎችን እንዲሁም የተለያዩ መርሀ ግብሮችን አሰናድቶ ተጋበዙልኝ ይላቹሀል።
@DBU11
@DBU11
🚀 DBU HackX 2025 is here!
📍 Debre Berhan University – College of Computing
🗓 May 16–18, 2025
🎯 Theme: Building Tech for Community Impact
💡 Solve real-world problems
👥 Open to all students (no coding required!)
🏆 Prizes • Internet • Certificates
📝 Register now 👉 Here link
📞 Contact: +251 93 646 0356
📌 Follow Us: 💬 Channel 👥 Group 🎥 tech_tonic_tribe">Tik Tok 💼 LinkedIn
በአማራ ክልል የቀጠለው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ
Fana broadcasting corporation እንደዘገበው👇👇
በአማራ ክልል የተጀመረው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወ/ሮ ባንቺአምላክ ገብረማሪያም እንደገለፁት÷ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።
የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ሥራው በሶስት ዙር እንደሚከናወን ጠቅሰው÷ በመጀመሪያው ዙር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ማስረጃ ላይ ማጣራት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
በሁለተኛ ዙር ደግሞ በክልል ደረጃ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም በሶስተኛው ዙር የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች ማስረጃ ማጣራት እንደሚከናወን አመላክተዋል፡፡
በክልሉ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የመንግስት ሰራተኞች ቢኖሩም የማጣራት ሥራውን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የሐሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሥራው በዋናነት ብቁ የሰው ሀይል ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ሐሰተኛ ማስረጃ በሚገኝባቸው አመራሮች እና ባለሙያዎች ላይ ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል።
@dbu11
@dbu111
ስርቆት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል!
[ በስርቆት ላይ የተሰማሩ ተማሪዎችም ተይዘዋል! ]
ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚገባም የዩኒቨርሲቲው ጥበቃና ደህንነት ጽ/ቤት ገልፀዋል።
ቀን 07/09/2017
ለሁሉም መደበኛ ተማሪዎቻችን እንደሚታወቀው የ 2017 የትምህርት ዘመንን ለማጠናቀቅ የቀረን ትንሽ ቀናቶች ናቸው።
ይሁን እንጂ በቀረን ትንሽ ቀን ውስጥ በራሳችን ቸልተኝነት እንዝላልነት በንብረታችን ማለትም ሞባይል laptop ጥሪት ገንዘብ እና አልባሳቶች እንዳይሰረቁብን የራሳችንን ጥንቃቄ በማድረግና ተጠርጣሪ በመሆን ንብረቶቻችንን በማንኛውም ሰዓት ከሌቦች መጠበቅ ያስፈልጋል።
በቀን 05-09-2017 ዓመተ ምህረት ከቀንኑ 10:30 ብሎክ 27 እና 25 ላይ ዶርም በተመሳሳይ ቁልፍ ተከፍቶ አንድ ላፕቶፕ የተሰረቀ ሲሆን የተማሪ ፖሊሶች ባደረጉት ጥብቅ ክትትል 07-09-2017 ላፕቶፑ ከነ ተጠርጣሪዎቹ ተይዞ የተገኘ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ ተደርጓል።
አስገራሚው ነገር ስርቆቱን የፈፀሙት ከዶርም ተማሪዎች መካከል ሆነው ተገኝተዋል
በዛሬው ዕለት ደግሞ ከብሉክ 17 dorm 207 ከቀኑ 10:30 በተመሳሳይ ቁልፍ ተከፍቶ ሶስት smart ስልክ እና አምስት ሺ ብር በላይ ተሰርቀናል በማለት ተማሪዎች አመልክተው እየተጣራ ይገኛል።
በትምህርት፣በጥናት እና በመዝናኛ ቦታዎች ላይ በምትገኙበት ጊዜ ለንብረቶቻችሁ የደህንነት ጥንቃቄን እንድትወስዱ እናሳስባለን።
የደ/ብ/ዩ ጥበቃና ደህንነት ጽ/ቤት
@DBU11
@DBU111
የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ለዩንቨርስቲው ሴት ተማሪዎች ያዘጋጀዉን የሜንተርሽፕ ፕሮግራም የመክፈቻ መርሀ ግብር በዛሬው እለት (07/09/2017) አካሄዷል።
በዝግጅቱም ስለ ሜንተርሽፕ ፕሮግራሙ ምንነትና አላማ የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ሮ አዲስ አስፍው ወሰን ማማብራሪያ ተሰቷል።
ሜንተሮች እራሳቸውን ያስተዋወቁበት ከሜንቲዎች ጋር የተገናኙበት ይህ ዝግጅት በሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን የኪነጥበብ ስራዎች የደመቀ ነበር።
@DBU11
@DBU11
"DBU daily news" አምስት አመታትን በአገልግሎት !
በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ የ daily news ቤተሰቦች በዚህ ሳምንት DBU daily news አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ አምስተኛ አመቱን ያስቆጣራል።
ታማኝ እና ተደራሽ የመረጃ ምንጭ በመሆን ሲያገለግላችሁ የቆየው ገፃችሁ(DBU daily news) በዚህ ሳምንት አምስተኛ አመት ልደቱን ያከብራል።
daily news በአምስት አመት ቆይታው የማይረሱ ትዝታዎችን የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በመስራት እና በማስተባበር ከእናንተ ጋር አሳልፏል ለትውስታ የወንድማችን ለገሰ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ከ daily news ጋር ያደረጋችሁት በጎ ተግባር አይረሳም ክፉ እና ጥሩ ግዜያቶችን አሳልፈናል። እስኪ የእናንተን ትዝታ በመልዕክት መስጫ ሳጥን (comment) ላይ አስቀምጡልን።
ከ 14 ሺህ በላይ community 👉 የዩንቨርስቲው መደበኛ እና extension ተማሪዎች፤ መምህራን፤ የዩንቨርስቲው አስተዳደር አካላት እና የከተማው ህዝብ እንዲሁም የተማሪ ወላጅችም ጭምር የሚከታተሉት የቴሌግራም ገፅ ነው። የመወያያ ጥያቄ(መረጃ) እርስ በእርስ ወይም ከቻናሉ መጠየቂያ ዕርዳታ መጠየቂያ ግሩፕም አለው ይህ ሊንኩ ነው 👉 @dbu111 ።
አምስተኛ አመቱን ሲያከብር ጥያቄዎችን ወደ እናንተ ይለቃል ለአሸናፊዎች የሞባይል ካርድ ሽልማት የሚያደርስ ይሆናል።
ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃን በሶፍትዌር ቴምፕሌት እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡
በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ እጩ ተፈታኞችን ለማጣራት የተፈታኞችን መረጃ በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለስልጣኑ ለተቋማቱ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡
በዚህም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ የላካችሁ ተቋማት ብቻ በትምህርት ሚኒስቴር ሶፍትዌር ቴምፕሌት እስከ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም ድረስ እድታስገቡ ተብሏል፡፡
@dbu11
@dbu111
የደም ልገሳ ጥሪ
8ኛው ዙር የደም ልገሳ በሀገራችን 20 ከተሞች በካንሰር ታማሚ ህፃናት ስም የተዘጋጀ መርሃግብር በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል ፤ ዝግጁ ናችሁ ቤተሰብ ?
ግንቦት 9 እና 10 በ 20 የሀገራችን ከተሞች እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ባሉ የደም ባንኮች በመገኘት አብረን ደማችን እንለግሳለን።
ሁለት ሺ ሰዎች በዚህ የደም ልገሳ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
15 በላይ የግል ድርጅቶች
10 የበጎ አድራጎት ማህበራት
10 በላይ የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማት
በጋራ በመተባበር ከተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ጋር አዘጋጅተውታል።
ኑ በደማች አዲስ ታሪክ እንስራ። በሚተካውን ደም የማይተካውን የሰው ልጅ ህይወት እናድን። ለካንሰር ታማሚ ህፃናት የነገን የማየት ተስፋ ምክንያት እንሁን ።
በከተማችን ደብረብርሀንም ይህ የደም ልገሳ ለ 3ኛ ዙር ይካሔዳል የዩንቨርስቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ ለተስፋ አዲስ ካንሰር ታማሚ ህፃናት ግንቦት 9 እና 10 ከጠዋቱ 3 ሰዐት ጀምሮ ደም ባንክ በመገኘት የህፃናቱን ሕይወት በጋራ እንድንጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ለማንኛውም አይነት መረጃ 0942169900 ላይ ይደውሉ
#ግንቦት9እና10
#20የሀገራችንከተሞች
#የካንሰርታማሚህፃናት
#8ኛዙርየደምልገሳመርሃግብር
#ኑበደማችአዲስታሪክእንስራ
@dbu11