15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
ህፃኑ ጥርስ አብቅሎ ተወለደ።
በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዋላጅ ነርስ መንግስቱ ኤባ አንድ የወተት ጥርስ ያበቀለ ህጻን መወለዱን ገለጹ።
ህጻናት ቀድመው ከ6 ወራት በፊት የወተት ጥርስ የሚያበቅሉበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ሁሉ ሲወለዱም አልፎ አልፎ የወተት ጥርስ አብቅለው የመወለድ እድል እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡
ክስተቱ ሲያጋጥም በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ አቤ፣ የበቀለው የወተት ጥርስ ለቀጣይ የህጻኑ ጥርስ አበቃቀል እንዲመች እንደሚወገድ፣ ክስተቱ በህጻኑ ጤና የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው ገልጸዋል፡ #Dessie Fm96.0
@EyobTikuye @ThiqahETH
ኩባ የአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት እንደገጠማት አስታወቀች።
ሀቫና በቅርብ ጊዜ ውስጥ አለማቀፍ በረራዎች ሊቋረጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቃለች።
በዋና ከተማዋ ሀቫና የሚገኘው የጆዜ ማርቲ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሰሩ ፓይለቶች የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን በዚህ ሳምንት መግቢያ የመንግሥት ባለስልጣናት ነግረዋቸዋል።
አሜሪካ በኩባ ላይ የጣለችው ማዕቀብ ለአውሮፕላን ነዳጅ እጥረቱ እንዳጋለጣት ተገልጿል።
ለኩባ ነዳጅ የሚያቀርቡት ሜክሲኮ እና ቬንዙዌላ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ውሳኔ ያቆሙ ሲሆን፣ ሌሎች ሀገራትም ነዳጅ እንዳያቀርቡ በአሜሪካ የታሪፍ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። #9news
@EyobTikuye @ThiqahEth
በሊቢያ የ53 ስደተኞች ህይወት አለፈ።
55 ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በሊቢያ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ የ53 ሰዎች ማለፉ ተገለጸ።
በዚህ አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ስደተኞች ናቸው ተብሏል። በህይወት የተገኙት ሁለቱ ስደተኞች የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው ሴቶች ናቸው።
ስደተኞቹ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸውን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።
ጀልባዋ ከሰመጠች በኋላ ለስድስት ሰዓታት ያክል አልተገኘችም ነበር ተብሏል።
IOM 2026 ከገባ ወዲህ 500 ስደተኞች በተመሳሳይ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ሲል ገልጿል። #bbc
@EyobTikuye @ThiqahETH
ኤርትራ ለኢትዮጵያ ምላሽ ሰጠች።
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳልህ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ለተፃፈላቸው ደብዳቤ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሚንስትሩ፣ "በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤርትራ ላይ የቀረበው የሀሰት ክስ አስደናቂና አጠቃላይ ዓላማዋው ሌላ ምኞት እንዳለው የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
ኦስማን፣ "በሚያሳዝን ሁኔታ በኤርትራ ላይ ከሁለት አመት ለበለጠ ጊዜ የቆየው ዘመቻ ላይ ተጨማሪ ወቀሳ ነው" ሲሉም ገልጸዋል።
"ካሁን በፊት እንደተገለጸው የኤርትራ መንግስት ትርጉም በሌለው ነገር ሁኔታውን ለማባባስ አሁን ካለው ውዝግብ ላይ በመሳተፍ ነዳጅ የመጨመር ፍላጎት የለውም" በማለት ሀገራቸው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንደማይትገባ አስታውቀዋል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
በኢራን የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ናርገስ መሀመዲ የሰባት አመት እስር ተፈረደባት።
ታዋዊዋ ኢራናዊ አክቲቪስት መሀመዲ የፍርድ ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት የረሃብ አድማ ጀምራ እንደነበር ጠበቃዋ ሙስጦፋ ኒሊ በኤክስ ገፃቸው አስፍረዋል።
የ53 አመቷ ናርገስ መሀመዲ ክስ የቀረበባት "ግጭት በመቀስቀስ ወንጀል" መሆኑን ኒሊ ገልጸዋል።
መሀመዲ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የህግ ባለሙያው እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበረው ኮስሮው አልኮርዲ የቀብር ስነስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት ነበር በደህንነት አካላት ተይዘው የተወሰዱት።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ፣ የኢራን ባለስልጣናት በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሷቸውን የመብት ጥሰቶች በመቃወሟ ለእስር ተዳርጋ ቆይታለች። #huffpost
@EyobTikuye @ThiqahETH
#AddisAbaba
11 አመራሮች እና ሠራተኞች ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍ/ቤት ቀረቡ።
የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 11 አመራርና ሰራተኞች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመጠቀም ወንጀል ተጠርጥረው በፓሊስ ተይዘው ፍ/ቤት ቀረቡ።
"በ2016 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አየር መንገድ አከባቢ የህዝብ እና የመንግስት ይዞታ የሆነውን በ9ኛው መዋቅራዊ ፕላን በአደዋ ፓርክነት ተይዞ የነበረውን እና በ10ኛ መዋቅራዊ ፕላን በዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ልዩ ልዩ የከተማው መተንፈሻ አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት በከተማ ደረጃ በመናፈሻነት ለህዝብ አገልግሎት የተያዘ እና በመሬት ባንክ ውስጥ ያለን ይዞታ ያለ ህጋዊ ምክንያት ሰነድ አልባ ይዞታ ነው በማለት፦
ለዮርዳኖስ፤ ዘውዲቱ እና ጓደኞቻቸው የሲሚንቶ አከፋፋይ ህብረት ሽርክና ማህበር የቦታው ስፋት 2905 ካ.ሜ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የቦታው ሊዝ ዋጋ 168 ሚሊዮን 724 ሺሕ 405 ብር የሚገመትን ጉዳት" አድርሰዋል ተብሏል።
በዚህም "ከወረዳ፤ ክ/ከተማ እና መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ድረስ በጥቅም ተሳስረው ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል" ተጠርጥረዋል።
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበውም ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠይቆ ምርመራው ቀጥሏል ተብሏል። #FMC
@EyobTikuye @ThiqahEth
"የዓለም ሀገራት ለእስራኤል ትጥቅ መስጠታቸውን አላቆሙም" - የሃማስ አመራር
የሃማስ ፖለቲካ መሪ ካሊድ ማሻል ከእስራኤል ጋር የተፈጸመው ስምምነት ጉዳቱ ማመዘኑን ገለጹ።
ማሻል "ህዝባችን በጠላት ቁጥጥር ስር ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የቡድኑ የፖለቲካ መሪ በሰጡት አስተያየት "በቀላሉ በእስራኤል እየጠፋ ነው፣ የዓለም ሀገራት ለእስራኤል ትጥቅ መስጠታቸውን አላቆሙም" ሲሉ ወንጅለዋል።
"እኛን ትጥቅ ማስፈታት ፍልስጤማውያንን ለጥፋት አጋልጧል" ሲሉም ስምምነቱ ተግባራዊ አለመደረጉን ጠቁመዋል።
"በስምምነቱ መሰረት አሁን መነጋገር ያለብን ስለ መልሶ ግንባታ እና ሰብዓዊ እርዳታ ነበር፣ ግን ያ አልሆነም" በማለት አጥብቀው ተችተዋል። #thejerusalempost
@EyobTikuye @ThiqahEth
"የንጹሐንን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ጉዳት ደርሷል" - የአፍሪካ ህብረት
"ህይወት ለማጥፋት ሳይሆን ህይወት ለማዳን ነው እርምጃ የወሰድነው" - ኤም 23
የአፍሪካ ህብረት በኪሳንጊ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ "የንጹሐንን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ጉዳት ደርሷል" ሲል ገለጸ።
የ"የኪሳንጊ ጥቃት በሀገሪቱ የሽብር ጥቃቶች የሚያበረታታ አሰቃቂ ጥቃት ነው" ሲልም አውግዟል።
የማርች 23 (M23) በበኩሉ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ ተችቷል።
የኤም 23 አማፂ ቡድን በኮንጎ ጦር፣ በሩዋንዳ ቅጥረኛ ገዳዮች እና በቡርንድ አጋዥ ኃይሎች ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል።
የኤም 23 ዋና ፀሐፊ ቤንጃሚን ምቦኒምፓ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ "የተዛባ እና ስም የሚያጠፋ መግለጫ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።
"ህይወት ለማጥፋት ሳይሆን ህይወት ለማዳን ነው እርምጃ የወሰድነው" ያሉት ምቦኒምፓ "ተቋሙ ገለልተኛ አለመሆኑን በግልጽ ያሳየ መግለጫ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
"የኪንሻሳ መንግስት ኃይሎች ባለፉት 2 ወራት ብቻ በምዌቦቤ፣ ሪትሳንኩ፣ ካቶጎታ፣ ሳንጌ እና በከፍተኛው ፕላቶ የሚገኙ ንጹሐን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት 12 ጊዜ ፈፅመመው ያወገዘ አካል አልነበረም" ብለዋል። #thenewtimes #nilepostnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
በሱዳን "በአማፂያኑ ጥቃት" 8 ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 24 ተፈናቃዮች ተገደሉ።
በጦርነቱ ምክንያት ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሸሹ የነበሩ ተፈናቃዮችን የጫነ መኪና ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) አስታውቋል።
ተፈናቃዮቹ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ከሰሜን ኮርዶፋ ወደ ደቡብ ኮርዶፋ ሲጓዙ አል ራሃድ ከተማ ላይ እንደሆነ ገልጿል።
ጥምረቱ ጥቃቱን የፈጸመው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) አባላት ናቸው ብሏል።
ከሟቾቹ ውስጥ ስምንት ህፃናት እና በርካታ እናቶች ይገኙበታል ተብሏል።
በሱዳን በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ቢያንስ 114 ሰዎች በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) መረጃ ያመላክታል። #shafaaqnews
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የሩሲያ አስተሳሰብ ተቀይሯል፣ መተማመናችን ግን ገና ዜሮ ነው" - ዘለንስኪ
ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል መተማመን የለም አሉ።
ቮለድሚር ዘለንስኪ በአቡዳቢው የሦስትዮሽ ውይይት የተሳተፈውን ልዑካን ሪፖርት ካደመጡ በኋላ፣ "ሩሲያውያን ለእኛ ያላቸው አመለካከት ተመሳሳይ ነው ምክንያቱም እኛን ይጠሉናል" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ፣ "የሩሲያ አስተሳሰብ ተቀይሯል፣ መተማመናችን ግን ገነሠ ዜሮ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"ስላለፈ ታሪክ ማውራት አቁመዋል፣ እኛ ምን እንደምንፈልግና እንደማንፈልግ ነው ያውቃሉ፣ ተኩስ አቁም ስለሚደረግበት ሁኔታ ብቻ" ሲሉም አክለዋል።
"እነርሱ ወደኛ የመጡት በጦርነት ነው፣ ጦርነቱን የጀመረችው ዩክሬን አይደለችም" በማለትም ገልጸዋል።
"እኛ አሜሪካን ጨምሮ የውጭ ሀይሎች እቅዳችንን ለማስፈጸም እንደሚያስፈልጉን ተናግረናል፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ይህንን በደምብ ያውቃሉ" ነው ያሉት። #interfax
@EyobTikuye @ThiqahEth
"በተፈጸመብን ጥቃት በብዙ ክልሎች መብራት ጠፍቷል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ሽምይሀል
ሩሲያ በዩክሬን የኃይል መሰረተ ልማት ላይ ከባድ ጥቃት ማድረሷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ።
በቡርሽትንስካ እና ዶብሮትዢስካ ከተሞች በደረሰው በዚህ ጥቃት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሀይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል ተብሏል።
ሌሊት ላይ በከተሞች በደረሰው ጉዳት የተቋረጠውን ኃይል ለመተካት ከፖላንድ የእርዳታ ድጋፍ መጠየቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ደኒስ ሽምይሀል ተናግረዋል።
ሽምይሀል፣ "ሞስኮን ሆን ብላ በኢነርጂ ጣቢያዎች ላይ የታቀደ ጥቃት እየፈጸመች ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "በጠላት አማካኝነት በተፈጸመብን ጥቃት በብዙ ክልሎች መብራት ጠፍቷል" ብለዋል።
"ጥቃቱ አሁንም ቀጥሏል" ያሉት ደኒስ ሽምይሀል "የተቋረጠውን ሀይል ለመመለስ የተቻለንን እየሰራን እንገኛለን" ሲሉ ገልጸዋል።
የሦስትዮሽ ውይይቱ በቀጠለበት ወቅት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አላቆመችም ተብሏል።
በአሜሪካ አደራዳሪነት በአቡዳቢ የተወያዩት ሞስኮ እና ኪቭ የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ እና ተኩስ ለማቆም ተስማምተው፣ ሦስተኛ ዙር ውይይታቸውን በቀጣይ ሳምንት ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘው መለያየታቸው ይታወሳል። #euractive
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ቴህራን በመጥፎ ሁኔታ ስምምነት ማድረግ የፈለገች ይመስለኛል" - ዶናልድ ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን ከስምምነት ለመድረስ የተጠቀመችበትን አካሄድ ነቅፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሌሊት ላይ በኦማን ከተደረገው የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ድርድር በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ "ኢራን ስምምነት ላይ ካልደረሰች ውጤቱ ውድቀት ነው የሚሆነው" ሲሉ ዝተዋል።
"የስምምነታቸውን ሀሳብ ማየት አለብን" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ "ቴህራን በመጥፎ ሁኔታ ስምምነት ማድረግ የፈለገች ይመስለኛል" ብለዋል።
አክለውም፣ "ውይይቱ ቀጣይ ሳምንት ይቀጥላል፣ የኑክሌር ፕሮግራም ደግሞ ዋነኛ አጀንዳችን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
"ይህ ስምምነት ከሁለት አመት በፊት ነበር የሚያልቀው፣ ግን በእነሱ በኩል ፍላጎት አልነበረም" በማለትም ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።
ምንም እንኳን ትራምፕ ባያደንቁትም በአንፃሩ
አደራዳሪዋ ሀገር ኦማን እና ኢራን ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር አስታውቀዋል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahETH
#Update
"ኢራን እና አሜሪካ ጥሩ ለውጥ ያሳየ ውይይት አካሂደዋል" - አልቡሳይዲ
የኢራን እና አሜሪካ (የቴህራን እና የዋሽንግተን) የመጀመሪያውን ዙር ኢ-ቀጥተኛ ውይይት ዛሬ በኦማን መድና ሙስካት ተካሂዷል።
በዚህም ሁለቱ ሀገራት ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል።
በዚህም የድርድሩ አሸማጋይ ሀገር ኦማን ቀጣዩ ውይይት ኤፕሪል 23 እንደሚካሄድ አስታውቃለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እና የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ የሀገራቱን ልዑካን በመምራት በውይይቱ ተሳትፈዋል ተሳትፈዋል።
አራግቺ "በአወንታዊ መንገድ አንዱ የሌላውን ሀሳብ ተቀብሏል" ሲሉ የውይይቱን አንድምታ አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ ከውይይቱ በኋላ ለኢራን መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አጭር ቃል "ድርድሩን ለማስቀጠል ተስማምተናል፣ አካሄዱን እና ጊዜውን በሌላ ቀን እናሳውቃለን" ሲሉ ተናግረዋል።
"ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው የኑክሌያር ፕሮግራም ላይ ብቻ ነው፣ ሌላ አጀንዳ አልነበረም" ብለዋል።
የአሜሪካ ልዑካን ግን ከኑክሌር ድርድር ባለፈ ኢራን በምትደግፋቸው የቀጠናው ታጣቂዎች ላይ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል።
የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አልቡሳይዲ በኤክስ ገፃቸው፣ "ኢራን እና አሜሪካ ጥሩ ለውጥ ያሳየ ውይይት አካሂደዋል" ሲሉ አስፍረዋል።
አልቡሳይዲ "ውጤት የሚያመጣ ተመሳሳይ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት አልመናል" በማለት የውይይቱን ቀጣይነት ጠቁመዋል። #euronews
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ስምምነቱ ውጤታማ ካልሆነ አሜሪካ ለኢራን ከዲፕሎማሲ ጎን ለጎን ብዙ አማራጭ አላት" - ካሮሊን ሌቪት
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ለሚደረገው ውይይት ወደ ኦማን አቅንተዋል።
የዋይትሐውስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ካሮሊን ሌቪት "ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን በኑክሌር ፕሮግራም ላይ ድርድሮች ካልተሳኩ በሚል ሌሎች አማራጮችን አዘጋጅተዋል" ብለዋል።
"ፕሬዚደንት ትራምፕ ግልጽ ፍላጎታቸውን አስቀምጠዋል" ያሉት ሀላፊዋ "የኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ዜሮ መሆን አለበት" ሲሉ ተናግረዋል።
ሌቪት በሰጡት መግለጫ "ስምምነቱ ውጤታማ ካልሆነ አሜሪካ ለኢራን ከዲፕሎማሲ ጎን ለጎን ብዙ አማራጭ አላት" ካሉ በኋላ ትራምፕን "በአለም ታሪክ የጠንካራው ጦር አዛዥ ናቸው" ሲሉ አማራጩ የሀይል እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሌቪት በመግለጫቸው ስለ ኩባ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ "የኩባ መንግስት በመጨረሻ እግሩ ላይ ነው፣ ለመውደቅ ተቃርቧል" ሲሉ መልሰዋል።
"ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዲፕሎማሲ ሁሌም ዝግጁ ስለሆኑ ከኩባ ጋርም ተመሳሳይ ነገር ያለ ይመስለኛል" ብለዋል። #trtworld
@EyobTikuye @ThiqahETH
ትራምፕ ከኦባማ ጋር በተያያዘ ያጋሩት የዘረኝነት ተንቀሳቃሽ ምስል ተቃውሞ አስከተለ።
ዶናልድ ትራምፕ ከምርጫ ሴራ ጋር የተገናኘና የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ጋር የተያያዘ ምስል ማጋራታቸው ተቃውሞ አስከትሎባቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በባይደን የተሸነፉበት የ2020 ምርጫን የሚመለከት እንጂ ሆን ብለው ያጋሩት አለመሆኑን ገልጸዋል።
60 ሰከንድ የሚረዝመው ተንቀሳቃሽ ምስል የድምፅ መሰጫ ጣቢያዎች ሲጭበረበሩ ኦባማ ደስተኛ መሆናቸውን ያሳያል ተብሏል። #associatedpress
@EyobTikuye @thiqaheth
"በቡድኑ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣል ንጹሐንን ከሞት መታደግ ይገባል" ቮልከር ተርክ
ተመድ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) በኤልፋሽር ወንጀል መፈጸሙን በመግለጽ፣ ማዕቀብ እንዲጣልበት አሳሰበ።
በተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ በሱዳን የርስበርስ ጦርነት ከሱዳን ጦር ጋር ውጊያ ውስጥ የሚገኘው "የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ እና አጋሮቹ በኤልፋሽር የግድያ ወንጀል ፈጽመዋል" ብለዋል።
"ስጋቱ ግልጽ ነው፣ ግን ማስጠንቀቂያዎች አይሰጡም፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ የተሻለ መስራት አለበት" ነው ያሉት።
"RSF በአሳዛኝ ሁኔታ ግድያ፣ ፆታዊ ጥቃት እና እገታ ፈጽሟል" ሲሉ ወንጅለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ፣ "ቡድኑ ኤልፋሽርን ታህሳስ 1/2025 ከተቆጣጠረ በኋላ ከ62,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል" ብለዋል።
"በቡድኑ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣል ንጹሐንን ከሞት መታደግ ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል። #unnews #eurasiareview
@EyobTikuye @ThiqahETH
በናይጄሪያ በተከሰተ የመንገድ አደጋ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞቱ።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በካኖ ግዛት የተከሰተው በአሽከርካሪ ድክመት የተከሰተ ነው ተብሏል።
በናይጄሪያ ባለፈው አመት መንገድ ላይ በደረሰ አደጋ 5,421 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።
በዓለም ላይ 3% ተሽከርካሪዎች የሚገኝባት ናይጄሪያ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ትራንስፖርት የምታስተናግድ ሀገር እንደሆች ተመላክቷል። #thegleaner
@EyobTikuye @ThiqahEth
በሊባኖስ በደረሰ የህንፃ መደርመስ ቢያንስ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
እስካሁን ባለው የተጣራ መረጃ 8 ሰዎች ተጎድተው ወደሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።
ባለ ስድስት ፎቅ የመኖሪያ አፓርታማ በድንገት መደርመሱን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
አደጋው የደረሰው በሰሜን የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ በሆነችው የትሪፖሊ ከተማ ነው።
ለህንፃው መደርመስ ዋነኛ ምክንያቱ የግንባታ ጥራቱ ደካማ መሆኑ ነው ተብሏል። #mailonline
@EyobTikuye @ThiqahETH
አንቶኒዮ ጆሴ ሰጉሮ የፖርቱጋል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
የሶሻሊስት ፓርቲ መሪው ሰጉሮ 66.2% ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸውን እና የቼጋ ፓርቲ ተወካዩ አንድሬ ቬንቱራ 33.8% ድምፅ ማገኘታቸውን የፖርቱጋል ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ጆሴ ሰጉሮ ለሁለት የስልጣን ዘመን ፖርቹጋልን ያስተዳደሩትን ማርሴሎ ሮቤሎን በመተካት የሀገሪቱ መሪ መሆን ችለዋል ተብሏል።
የ63 አመቱ ሰጉሮ ከዚህ ቀደም በነበረው ምርጫ ቢሳተፉም ማሸነፍ ሳይችሉ፣ 11 ሚሊዮን መራጮች በተሳተፉበት ሁለተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ አሸንፈዋል ተብሏል።
አዲሱ ፕሬዚዳንት ከ2001-2002 የፖርቱጋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። #radiowpsu
@EyobTikuye @ThiqahETH
በከ168 ሚሊዮን በላይ ብር ሙስና የተጠረጠሩት አመራሮች እና ሠራተኞች እነማን ናቸው?
- የቀድሞ አዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሞሊቶ አባይነህ ኤርቃሎ፤
- የቀድሞ የቦለ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳዳር ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ቸርነት አበበ የአደቴ፤
- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቴክኒክ ጉዳይ ወሳኝ ባለሙያ ሰለሞን በላይ መኮንን፤
- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቅሬታ እና አቤቱታ ባለሙያ አድማሱ አዳነ ወንድሙ፤
- የከተማ አስተዳዳሩ መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ ግዛቸው ሙሉጌታ ደሴ፤
- የቀድሞ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደረጀ ጎሹ ሀይሌ፤
- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 መሬት ልማትና አስተዳዳር የሰነድ አጣሪ ባለሙያ አለምፀሃይ ለማ ኪ/ማርያም፤
- የከተማ አስተዳዳሩ መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ህግ /ቴክኒክ ጉዳይ ክትትል ዳይሬክተር ግርማ ተፈራ አያና፤
- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቴክኒክ ባለሙያ አማኑኤል አለማየሁ ማሞ፤
- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቴክኒክ ባለሙያ ቢኒያም ሀይሉ ገብሬ እንዲሁም፤
በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ፍትህ ቢሮ የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቢዮት ጁፋሬ ባይሳ ናቸው ተብሏል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
ደቡብ አፍሪካ ከ700 የሚልቁ ወታደሮቿን ከኮንጎ አስወጣች።
ጆሃንስበርግ የመለሰቻቸው በተመድ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ (MINUSCO) ስር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተሰማርተው የነበሩ ወታደሮች ናቸው።
ወታደሮቹ የተመለሱት፣ የሀገሪቱን ጦር የሰው ኃይል "ለማመጣጠን ነው" ሲል የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጽ/ቤት አሳውቋል።
ደቡብ አፍሪካ ከ1999 ጀምሮ ላለፉት 27 አመታት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት ከፍተኛ የሰላም ማስከበር ኃይል ከሚያዋጡ አስር ሀገራት መካከል አንዷ ናት። #iol
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የኤርትራ ኃይሎች በእኛ ሰሜን ምስራቅ ድንበሮችን ጥሰው ገብተዋል" - ኢትዮጵያ
ኤርትራ የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ "ወረራ" ያለችውን "ጥቃት" መፈጸሟን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለኤርትራ በይፋ በደብዳቤ አሳወቀች።
በዚህም፣ "የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በቀጥታ የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።
ባለፉት ቀናት ያለው ሁኔታ የኤርትራ መንግስት ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያመላክቱ ናቸው። የኤርትራ ኃይሎች በእኛ ሰሜን ምስራቅ ድንበሮችን ጥሰው ገብተዋል። በሰሜን ምዕራብ በኩልም ከአማፂ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት የጋራ ወታደራዊ ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ። ይህ ፀብ አጫሪነት ብቻ ሳይሆን ወረራ ነው።
እንዲህ አይነቱን ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ለመቋጨት የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት የሚገኙ ሀይሎችን በአስቸኳይ እንዲያስወጣ እና ከታጣቂ ቡድኖች ጋር ያለውን ትብብር እንዲያቆም በአስቸኳይ እንጠይቃለን።
ከግማሽ በላይ ለሚሆን ክፍለ ዘመን ግጭት የሁለቱ ሀገራት መለያ ገፅታ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አይነቱን የጦርነት አዙሪትና አለመተማመን በውይይትና በዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ማስወገድ ይገባል ብለን እናምናለን።
ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ፍላጎታችን አወንታዊ ምላሽ ካገኘን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር ጉዳዮችን እና በአሰብ በኩል የቀይ ባህር አቅርቦትን ጨምሮ በጋራ ጥቅሞቻችን ላይ በጥሩ መተማመን ለመነጋገር ፍላጎት አለው።
በጋራ መከባበርና ትብብር ግንኙነታችንን በማሳደግ ብዙ የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ያሏቸውን የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች አዲስ የሰላም እና የብልግና ዘመን ማምጣት እንችላለን" ብላለች። (ሙሉ የደብዳቤው ሀሳብ ከላይ ያለው ነው)
@EyobTikuye @ThiqahETH
ታይላንድ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።
በዚህ ምርጫ ለመሳተፍ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል።
ወደ 5000 የሚጠጉ እጩዎች ለ500 የፓርላማ መቀመጫ ይወዳደራሉ ተብሏል።
19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሶስት ዕጩዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መምረጣቸው ሲገለፅ 12 ሀለቱ በቀጣይ እንደሚያሳውቁ፣ ቀሪዎቹ 12 ደግሞ በጋራ አንድ ዕጩ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መርጠዋል ነው የተባለው።
ከተወዳዳሪዎቹ ውስጥ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርናቪራኩል ይገኙበታል።
የምርጫ ውጤቱ ከሶስት ወር በኋላ ኤፕሪል 9 ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። #bloomberg
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Update
አይኤስ በፓኪስታን ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት ወሰደ።
በዓለማቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት የተፈረጀው የአይኤስ (IS) ቡድን በዋና ከተማዋ እስላማባድ በሚገኝ መስጊድ ላይ የደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በቡድኑ የተቀነባበረ መሆኑን ገልጿል።
ሺቴ ሙስሊሞች የሚገለገሉበት የባርጋህ ቃጅር ኩርባህ መስጊድ ላይ ትናንት በጁምአ ሶላት ወቅት በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት 31 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 169 ተጎድተዋል።
የሟቾቹ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahETH
#Gambella
"ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል" - ጋምቤላ ክልል
የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ "ከሰኞ የካቲት 2/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል" ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት አስታወቁ።
በዚህም፦
- እስካሁን ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት 30 የነበረው የሥራ ሰዓት ከ1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት 30፤
- እንዲሁም ከ9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ተኩል የነበረው ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት 30 እንዲሆን ተወስኗል።
- የሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ተመልክቷል። #GMMS
@EyobTikuye @ThiqahETH
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባንግላዴሽ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በኒፓህ ቫይረስ ሞት መመዝገቡን አስታወቀ።
በዚህም አንዲት ሴት በኒፓህ ቫይረስ ህይወቷ አልፏል። ሟቿ የውጭ ሀገር ጉዞ አላደረገችም ተብሏል።
በህንድ የተከሰተው የኒፓህ ቫይረስ ወደተለያዩ የእስያ ሀገራት እንዳይስፋፋ ስጋት ደቅኗል።
ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኢንዶኔዥያ እና ፓኪስታን በአየርመንገድ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ እንደሚገኙ የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ቫይረሱ የመስፋፋት እድሉ ዝቅተኛ በመሆኑ የጉዞ ገደብ መጣል አስፈላጊ አይደለም ብሏል።
ድርጅቱ ቫይረሱን ለመከላከል እውቅና የተሰጣቸው መድሃኒቶች አለመኖራቸውን ጠቁሟል። #straitstimes
@EyobTikuye @ThiqahETH
ፈረንሳይ እና ካናዳ በግሪንላንድ ዙሪያ ከፍተኛ ውይይት እንደሚያስፈልግ ገለጹ።
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በዋና ከተማዋ ኑክ ተገናኝተዋል።
መሪዎቹ ራስ ገዝ በሆነችው የዴንማርክ ግዛት ተገኝተው ባደረጉት ውይይት የኔቶ አባል ሀገራት ለድርጅቱ መርህ መገዛት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በግሪንላንድ ብዛት ያላቸው የሁለቱም ሀገራት ዜጎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው አሜሪካ ለብሄራዊ ደህንነቷ ስትል ግሪንላንድን ታስተዳድራለች ማለታቸው ይታወቃል።
የሩቴ እና የማክሮ ውይይት የተካሄደውም ፕሬዝዳንቱ ይህን አቋማቸውን ባልቀየሩበት ወቅት ነው። #kyivpost
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ለውይይት ዝግጁ ነን፣ ግን በጫና ውስጥ ሆነን አይደለም" - ፕሬዚዳንት ካኔል
ኩባ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።
ፕሬዚዳንት ሜጉዌል ዲያዝ ካኔል ሀገራቸው ለንግግር መዘጋጀቷን ገልጸው፣ "የትኛውም ውይይት በሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ መግባትን አያካትትም" ብለዋል።
ካኔል "ለውይይት ዝግጁ ነን፣ ግን በጫና ውስጥ ሆነን አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
የኩባ እና የአሜሪካ ውይይት በቀጣይ ሳምንት ሐሙስ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
"ኩባ በቅርቡ ትወድቃለች" ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ኩባ ነዳጅ እንዳይገባ ከልክለዋል።
የነጩ ቤተመንግስት ዋና ፀሐፊ ካሮሊን ሌቪት በበኩላቸው፣ "የኩባ መንግስት በመጨረሻ እግሩ ላይ ነው፣ ለመውደቅ ተቃርቧል" ብለዋል። #aninews #dw
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ዳግም ወደ ኔፓል መግባት እንዳይችሉ ተወስኗል" - ቲኪራም ዳካል
ኔፓል በ6 ወራት በተደረገ ዘመቻ በህገወጥ ተግባራት የተሰማሩ 333 የውጭ ዜጎች መያዛቸው አሳወቀች።
የኔፓል ኢሚግሬሽን ዲፓርትመንት (DOI) ኃላፊ ቲኪራም ዳካል በመግለጫቸው፣ "ብዙዎች በቱሪስት/በቢዝነስ ቪዛ ገብተው ነገር ግን መንግስት በህግ በከለከላቸው ጉዳዮች ላይ ሲሳተፉ ነበር" ብለዋል።
"ህገ ወጥ የትዳር እና የእምነት ተቋማት ቢሮ በማቋቋም ስራ ተሰማርተው እንደነበር ደርሰንበታል" ያሉት ኃላፊው፣ "ለማሳያነት የኔፓል ሴቶችን በጋብቻ ወደ ቻይና ሲልኩ ነበር" ነው ያሉት።
ሁሉም 333 ሰዎች ከሀገር መውጣታቸውን የገለፀው ቢሮው "ዳግም ወደ ኔፓል መግባት እንዳይችሉ ተወስኗል" ሲሉም ገልጸዋል።
በ2025 ብቻ 501 የውጭ ዜጎች ከሀገር መባረራቸውን ጠቁመዋል። #thekathmandupost
@EyobTikuye @ThiqahETH
የአዲስ አበባ ከተማ በ6 ወራት ከ10 ሺሕ በላይ አካላት ብልሹ አሰራርና ጥፋት መፈጸማቸውን ተናገረ።
በዚህም፣ በ2018 ዓ/ም 6 ወራት ብቻ ከ10 ሺሕ 500 በላይ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች፣ ሠራተኞች ብልሹ አሰራር መፈጸማቸውን ገልጿል።
ይሁን እንጂ፣ "ተጠያቂ ተደርገዋል" ከማለት በዘለለ ምን አይነት እርምጃ እንደተወሰደባቸው አልተገለጸም።
በከተማዋ፦
- ባለፉት 6 ወራት ከ162 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል። ደረሰኝ ሳይቆርጡ በተገኙ 7 ሺሕ 678 ነጋዴዎች፣ ብልሹ አሰራር በፈጸሙ 282 ሠራተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል።
- 18.72 ቢሊዮን ብር ለተማሪ ምገባ፣ ለዩኒፎርም፣ ለጤና መድህንና ለትራንስፖርት ድጎማ ውሏል። በልማታዊ ሴፍቲኔት ደግሞ 1.135 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል"።
- 370 አገልግሎት በቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት እንዲሰጡ፤ በተቋማት ውስጥ 183 የህጻናት ማቆያ፣ 100 የሰራተኞች ካፊቴሪያ፣ 166 የሸማቾች ሱቆች እንዲደራጁ ተደርጓል።
- ተገልጋዮችን በማንገላታትና ጥፋት የፈጸሙ 61 አመራሮች፣ 126 ዳይሬክተሮችና የቡድን መሪዎች፣ 3 ሺህ 542 ሰራተኞች በፈጸሙት ጥፋት ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡ #AMN
@EyobTikuye @ThiqahETH