#DDR #Tigray
የእንግሊዝ (UK) መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም (DDR) የሚያግዝ የ16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፓወንድ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡
የድጋፍ ማእቀፉን ያሳወቁት በብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሎርድ ኮሊንስ የተመራው ልዑክ በመቐለ በመገኘት የብሄራዊ ተሀድሶ ቦርድ አባል ሌ/ጀ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ እና ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም የዩኤንዲፒ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የቀድሞ ተዋጊዎች ዲሞቢላይዜሽን ማእከል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
#UKinEthiopia
@tikvahethiopia
" አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ አሽከርክሩ " - ፖሊስ
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ የደረሱት የትራፊክ አደጋዎች የሰው ህይወት ቀጥፈዋል ፣ ከባድ እና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል፣ ንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።
በአንድ ክ/ከተማ፣ በአንድ ቀን፣ በተለያየ ቦታና ሰዓት በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ አጠቃላይ የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ9 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
አደጋዎቹ የደረሱት ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ/ም ነው።
የጉዞ መስመሩን ከጎሮ ወደ ኮዬ ፈቼ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-69867 ኢት #ሲኖ_ትራክ ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቡስ ጋር ተጋጭቶ ትኬት ሊቆርጡ ወደ አውቶቡሱ ተጠግተው የነበሩ 3 ሴቶች እንዲሁም በአካባቢው ላይ ጧፍ ስትሸጥ በነበረች ሴት ላይ የሞት አደጋ ያስከተለ ሲሆን የከባድ መኪናው አሽከርካሪም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበታል፡፡
ከተከሰተው ሞት በተጨማሪ በ7 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በዛው እለት ቡልቡላ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም አካባቢ በደረሰው አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
የጉዞ አቅጣጫውን ከመድኃኒያለም ወደ ማርያም ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-8660 ኢት #ሲኖ_ትራክ ተሽከርካሪ ከማርያም ወደ ኮዬ ይሄድ ከነበረ ኮድ 3-46737 ኦሮ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭተው የደረሰ አደጋ ነው።
በአንድ ቀን በ7 ሰዎች ላይ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ መድረሱ በእጅጉ አስዛኝ እንደሆነ የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ በአብዛኛው ለሚከሰቱት የትራፊክ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያት ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚደርሱ መሆናቸውን አስገንዝቧል።
አሽከርካሪዎች ከምንጊዜውም በላይ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የአካባቢውን߹ የመንገዱን እና የእግረኛውን የመንገድ አጠቃቀም ሁኔታ በተገቢው በማስተዋል ማሽከርከር እንደሚጠበቅባቸው ፖሊስ አሳስቧል።
ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር በኋላ ከሚመጣው መፀፀት እንደማያድን በመገንዘብ በጥንቃቄና በእርጋታ ማሽከርከር እንደሚገባ ፖሊስ ገልጿል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#Ethiotelecom
🎀 ተጨማሪ 10% ስጦታ ያግኙ!
ከውጭ አገራት ከ99 ብር ጀምሮ የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል በአጋሮቻችን በኩል ሲላክልዎ ለ30 ቀናት የሚያገለግል የ10% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
🗓 እስከ ታኅሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም!
ደንብና ሁኔታዎችን https://bit.ly/487Y93d ይመልከቱ!
#telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ሪልስቴት
ያልተገነባ ቤት / ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።
ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?
ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች ደንበኞችን #እንዳይመዘግቡ እና #ቅድመ_ክፍያ እንዳይሰበስቡ ይከለክላል።
በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል ስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ " የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ " የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል ስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን አለባቸው።
የአገር ውስጥ እና የውጭ አልሚዎች ግንባታውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን " የፋይናንስ አቅርቦት ምንጭ " የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦባቸዋል። ይሁንና ረቂቁ፤ " የቅድሚያ ቤት ሽያጭ ተጠቃሚነት " መብትን ከቅድመ ሁኔታ ጋር ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰጥቷል።
ይህ አሠራር የሪል ስቴት አልሚዎች የቤት ግንባታውን ሳያከናውኑ ወይም በሂደት ላይ እያለ ለግንባታው የሚውልን ፋይናንስ የሚያሰባስቡበት እና ገንዘቡብ ለግንባታው የሚያውሉበት መንገድ ነው።
የቤት ግንባታው ሳይከናወን በፊት ከገዢዎች ጋር ውል ማሰር እና ክፍያ መፈጸም ኢትዮጵያ ውስጥ በሪል ስቴት ልማት ላይ በተሰማሩ አልሚዎች በኩል የተለመደ አሰራር ነው።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ በዚህ ዓይነት መልኩ ለግንባታ የሚውለውን ሀብት ማሰባሰብ የሚፈልጉ አልሚዎች " አግባብ ካለዉ አካል ፈቃድ ማቅረብ " ይጠበቅባቸዋል። ይህም ግዴታ ነው።
የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል።
አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ " የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ " እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።
አዲሱ ሕግ፤ ገንዘቡ የሚቀመጥበት ዝግ የባንክ አካውንት የሚከፈተው " አግባብ ባለው አካል ፈቃድ መሠረት " እንደሆነም ያስረዳል።
በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በኋላ በሚወጣ ደንብ ይወሠናል።
ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት የመሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ " በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ " እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል።
ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት " ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ " እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።
ረቂቅ አዋጁ በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ሌሎችንም ግዴታዎች ጥሏል።
በረቂቁ መሠረት፤ የሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።
" ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም " ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል።
ሪል ስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።
አልሚዎች ምዝገባ ማድረግ እና ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉት " የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከተረከቡ " በኋላ ነው።
" በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም " የሚለውም ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ከተቀመጡት ግዴታዎች መካከል ነው።
ለሪል ስቴት ልማት አሠራር የሚዘረጋው አዲሱ አዋጅ፤ ከግዴታዎች ባሻገር አልሚዎች ከመንግሥት " መሬት በስፋት " ማግኘት የሚችሉበትን ሂደትም ያስቀመጠ ነው።
ከመንግሥት መሬት " በስፋት " የሚቀርብላቸው አልሚዎች ረቂቁ ላይ ከተጠቀሱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በብዛት ቤቶችን መገንባት እና ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ " 40 በመቶውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍል ተደራሽ " ማድረግ የሚለው አንዱ ነው።
ይህንን ቅድመ ሁኔታ የሚከተሉ አልሚዎች የሚገነቡበት ቤት ብዛት " እንደ ከተሞች ደረጃ በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ 5 ሺህ " ሊሆን እንደሚችል በረቂቁ ላይ ተጠቅሷል።
መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ መሬት " በስፋት " የሚያቀርበው " በአዲስ አበባ ከ5 ሺ በላይ ቤት ለሚገነባ እና ለሚያስተላልፍ " አልሚ እንደሆነ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
በሌሎች ከተሞች መሬት " በስፋት " የሚቀርበው እደሚኖራቸው " ተጨባጭ የቤት ፍላጎት " ሲሆን፣ " ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባሉ ከተሞች " ደግሞ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች እንደሚቀርብላቸው ረቂቁ ያስረዳል።
ከመንግሥት መሬት " በስፋት " ማግኘት የሚፈልጉ አልሚዎች የተቀመጠባቸው ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተገናኙ ናቸው።
በአገር ውስጥ " በጥራት እና በብዛት የማይገኙ " ግብአቶችን በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ (ፍራንኮ ቫሉታ) የሚያስገቡ እንዲሁም የሚያገኙትን ትርፍ እስከ አስር ዓመት ከአገር ሳያወጡ አገር ውስጥ መልሰው የሚጠቀሙ አልሚዎች የዚህ አሠራር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
" የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት እና ግመታ " የተሰኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ የቀረበለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተጨማሪ ዕይታ ወደ ከተማ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል።
መረጃው ከቢቢሲ አማርኛ የተወሰደ ነው።
@tikvahethiopia
#MoE
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
@tikvahethiopia
እሁድ ጥቅምት 3 ከሰዓት 9፡15 ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በችካጎ ማራቶን ይሳተፋሉ!
መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን! 💚💛❤️
ይህንን ደማቅ ሩጫ በቀጥታ በSS Africa ቻናል 227 በቤተሰብ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ስቴም ፖወር !
ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ3ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ !
ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ " ትጋት " የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል።
ባለፉት 2 ዙሮች 1700 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness ስልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ የስራ እድል በመፈጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል አመቻችቷል፡፡
#ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባው የሚቆየው ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 , 2017 ዓ/ም ሲሆን ቀድማችሁ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡
እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ከስር ባለውን ሊንክ ይመዝገቡ
👉Link: https://forms.office.com/r/bJedLrdqmd
#Amhara
" በአማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል። ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት
በአማራ ክልል በ " ፋኖ " ታጣቂዎችና በመንግስት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸው ይህም ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጭንቀት መደቀኑ ተሰምቷል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸውን እንደተረዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ነው።
የህብረቱ ፕሬዚዳንት ሓየሎም ስዩም፣ " አራት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል " ብሎ ተማሪዎች በጭንቀት ውስጥ በመሆናቸው ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትከረት እንዲሰጡ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
በጸጥታው ችግር የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ያራዘሙት፣ " ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና ኢንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች " መሆናቸውንም ተናግሯል።
" ወሎና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች አሁን መንገድ ስለተከፈተ ይቀበላሉ " ያለው የህብረቱ ፕሬዚዳንት ደባርቅ ዩኒቨርቲንም ቅበላውን ሳያራዝም እንዳልቀረ፣ " ሀፋ፣ ሀፋ " የሆነ ሀሳብ ላይ እንደሆነ አስረድቷ።
ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " ሲል አሳስቧል።
በአንጻሩ ወልዲያ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ተቀብለው እያስተማሩ መሆኑ ሲነገር ተስተውሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የተማሪዎቹን ቅበላ አራዝሟል ወይስ አላራዘመም ? ተማሪዎቹን ተቀብሎ እያስተማረ ነው ወይስ አልተጀመረም ? ሲል ወልዲያ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።
ዩኒቨርሲቲው በምላሹ፣ " አላራዘመም። ተማሪዎቹ እስኪገቡ ድረስ እንጠብቃለን። የመንገድ መዘጋጋቱ ስለሚታወቅ እንደ ሀገር በይፋ ባናራዝምም የቻሉ እየገቡ ነው ያልቻሉ ይገባሉ በፈለጉት ሰዓት " ብሏል።
" በውስጥ ኮሚዩኒኬት ስላደረግን ከተማሪው ከተለያዩ ቅርብ ቦታ (ለምሳሌ ደሴ) እየመጡ ስላሉ አላራዘምንም " ሲልም አክሏል።
ትምህርት ተጀምሯል ? ስንል ላቀረበነው ጥያቄ " ትምህርት አልተጀመረም " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንለት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ፣ " ተማሪዎችን ተቀብለን እያስተማርን ነው። የኛ ተማሪዎች ገብተዋል። ሲኔር ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ነው ያሉት " ብሏል።
" የአዲስ ገቢዎችን በተመለከተ ግን ትምህርት ሚኒስቴር አልመደበም ገና። እንደመደበ እንጠራለን። እኛ ምንም የምናራዝምበት ምክንያት የለም " ነው ያለው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅበላ ያራዘሙ ዩኒቨርሲቲዎችን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉት ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)፣ ' ዩኒቨርሲቲዎቹ የራሳቸው ስኬጁል አለ። እኛም የሰጠነው ስኬጁል አለ። ዩኒቨርሲቲዎቹ ይጠየቁ " ከማለት ውጪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥቧል።
#TikvahEthioiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
" ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይታደሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን
ከአዲስ መንጃ ፈቃድና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፤ " ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል " ብሏል።
በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡
አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ተመላክቷል።
ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ገልጿል።
@tikvahethiopia
#Afar
በአፋር ክልል ፣ ዱለቻ ወረዳ ሳጋንቶ ቀበሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የፈለቀውን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላለፈ።
ማሳሰቢያውን ያስተላለፈው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ነው።
ዩኒቨርሲቲው " በክልሉ በቅርቡ በተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ በተሰማው ርዕደ መሬት ሳቢያ በአካባቢው ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውኃ መፍለቅ ጀምሯል " ሲል ገልጿል።
ይህንን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ሰዎችም ሆኑ እንስሳት እንዳይጠቀሙት ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
በሬክተር ስኬል 4.9 በተመዘገበው ርዕደ መሬት የተሰነጠቀው መሬት 1.5 ሜትር ስፋት ያለው ስለመሆኑ አመልክቷል።
ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአፋር ክልል የተከሰተው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መሰጠንቅ፣ መኖሪያ ቤቶች ላይ መፍረስና መሰንጠቅ እንዲሁም እስሳት ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መጠነኛ ጉዳት ስለማስከተሉ ዩኒቨርሲቲው አስረድቷል።
ህብተረተሰቡ በተፈጥሮ አደጋው ከተሰነጠቁ አካባቢዎች፣ ድልድዮች እና ተራራዎች እንዲርቅ ጥሪ ቀርቧል። #ኢቢሲ
@tikvahethiopia
#MesiratEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የጊግ ኢኮኖሚን ጥቅም ማወቅ ይፈልጋሉ?
በቢዝነስ፣ በህግ እና በፋይናንስ ዙርያ የሚሰጠውን የጊግ ኢኮኖሚ ስልጠና በቴሌግራም ቦት በኩል ይውሰዱ!
በ http://t.me/mesirat_academy_bot ተመዝግበው ስልጠናውን ይጀምሩ!
ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፍኬቶን እንዳይረሱ!
#MesiratEthiopia #Entrepreneurship #BusinessGrowth #GigEconomy #Workshops #Mesirat
Addis Ababa University- Cisco Networking Academy,
@CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com
Online Live class - Cisco CCNA Professional Networking Course Training & Certification Preparation.
Registration Date: Sep.15 to October 18, 2024
Class start date: October 19, 2024.
Course Recognitions: CCNA trainees will receive 3 Certificate of Completion, 3 Letter of Merit, 3 Digital Badge that recognized and accepted in USA, Canada, and Europe, and you will award 58% CCNA certification exam discount voucher.
Mobile #: 0902-340070/ 0935-602563/ 0945-039478
Office : 011-1-260194
Follow our telegram channel: @CiscoExams
የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችለው የመቁረጫ ነጥብ ስንት ነው ?
በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን የመቁረጫ ነጥብ ፦
➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የወንድ ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 204 ነው።
➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የሴት ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 192 ሆኖ ተቆርጧል።
(ተጨማሪ የመቁረጫ ነጥብ ከላይ ተያይዟል)
ከዚህ ባለፈ ግን እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግልና በመንግስት ተቋማት) በራሳቸው ክፍያ የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።
ይህ ማለት ፦
➡️ ከ600ው የትምህርት ብዛት ፈተናቸውን ተፈትነው 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (186 እና በላይ) ፤
➡ ከ500 የትምህርት ብዛት የተፈተኑ (ዓይነስውራን ተማሪዎች) 31% እና በላይ ውጤት ያመጡ (155 እና በላይ) ፤
➡ ከ700ው የትምህርት ብዛት የተፈተኑ 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (217 እና በላይ) ... በፈለጉት አማራጭ ማለትም በግል ሆነ በመንግሥት ተቋማት ከፍለው የሬሜዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።
በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በቀጥታ የሚያሳልፈው ውጤት 50% እና በላይ መሆኑ ይታወቃል።
የሬሜዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ (በመንግሥት ስፖንሰርሺፕ / ተመድቦ ለመማር) ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።
በግል ከፍለው በመንግሥትም ይሁን በግል ተቋም ለመማር የሚፈልጉ ከተፈተኑት ፈተና ውጤት 31% እና በላይ ውጤት ማምጣት አለባቸው።
@tikvahethiopia
#MoE #Placement
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
Via @tikvahuniversity
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።
ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።
በዚህ መሰረት፦
➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር
➡️ የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።
መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia
“ ወደ ህክምና የሚመጡ የካንሰር ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ” - ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የካንሰር ህሙማን ቁጥር ግልጽ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን፣ የማህጸን በርና የጡት ካንሰር ህሙማን 50 በመቶውን እንደሚሸፍኑ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ካንሰር ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ሆስፒታሉ ምን ማብራሪያ ሰጠ ?
“ ግልጽ በሆነ ሁኔታ የካንሰር ህሙማን ቁጥር ጨምሯል እንጂ አልቀነሰም። በተለያዩ ምክንያቶች በዓለም ላይ እንደሚጨምረው ይጨምራል።
ሁለተኛ ደግሞ የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት በዬጊዜው እየጨመረ ነው። ስለዚህ የፔሸንት ፍሎው እየጨመረ ይሄዳል።
ወደ ህክምና የሚመጡት የካንሰር ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። አብዛኛዎቹ ህሙማን የማህጸን በርና የጡት ካንሰር ታካሚዎች ናቸው።
እንዲያው በግርድፉ እስከ 50 ፐርሰንት ልንለው እንችላለን። የነዚህ ሰዎች ህክምና በሦስት፣ በአራት ህክምና ነው የሚካሄደው። በቀዶ ህክምና፣ በመድኃኒት፣ በጨረር፣ ታርጌትድ ቴራፒ (ተራ ሳይሆን ለዬት ያለ መድኃኒት) አለ።
ስለዚህ ቁጥሩ እየጨመረ ነው። ህክምናው ደግሞ መልቲሞዳል ነው። ከዚያ በተጨማሪ ካንሰሩ ደግሞ በጊዜው አይመጣም። ከተስፋፋ፣ ካደገ፣ ከተሰራጨ በኋላ ይመጣል። ይሄ ደግሞ ከካንሰሩ ህመም በተጨማሪ ተጓዳኝ ህመሞች ይዞ ይመጣል።
ለምሳሌ የማህን በር ካንሰር ያለባት እናት አድቫንስ አድርጎ ስትመጣ ያ ካንሰር የሽንት ቧንቧዋን ይዟት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ኩላሊቷ ይጎዳል ማለት ነው " ብሏል።
በመሆኑም በማህጸን ደም ሲኖር፣ ጡት ላይ ያበጠች ነገር ስትኖር በፍጥነት ወደ ሀኪም ቤት መምጣት፣ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በህክምና ልየታ ማሰራት ያስፈልጋል ተብሏል።
የጭማሪ ቁጥሩን ለመግለጽ ዳታ ማየት ቢያሻም የካንሰር ህሙማን ቁጥር እንደጨመረ፣ ከዚህም ባሻገር የመድኃኒት እጥረት ፈተና እንደሆነበት ሆስፒታሉ ገልጿል።
ምን አለ ?
“ ሲኤምኤል የሚባል የካንሰር ህመም አለ። ይሄ ህመም እጅግ በጣም ውድ መድኃኒቶች ነው የሚፈልገው። ይሄንን መድኃኒት አንድ ሰው መግዛት አይችልም።
ሀኪሞቻችንና ተቋሙ ከሌሎች ሀገራት ሀኪሞችና ተቋሞች ጋር በመተጋገዝ መድኃኒቶች እንዲመጡ ነው የሚደረገው። ከዛ በነጻ እናሰራጫለን።
ስለዚህ ይሄን መድኃኒት ገዝተን ቢሆን ወይም በእርዳታ ባናገኘው ኖሮ ህሙማኑ አያገኙትም ማለት ነው።
ሚሎቲኒቭ የምትባል የደም ካምሰር የህክምና መድኃኒትም አለች። 120 ህመምተኞች አሉ አዚህ አገር ላይ። ለ120ዎቹ ሰዎች 22 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋቸዋል። ይሄ የመድኃኒት በጀታችን ከአንድ ሦስተኛ በላይ ነው።
22 ሚሊዮን ብር የሆነውም ጤና ሚኒስቴር 50 ፐርሰንቱን ከፍሎ ነው። እንደገና ሆስፒታሉ ሰብሲሳይድዝ ሲያደርገው ሙሉውን በነጻ ያገኛሉ። ይህን ግን በዘላቂነት ማድረግ አንችልም። ቻሌንጅ አለ። መልስ ለመስጠት ራሱ ግራ ያጋባል። ”
የካንሰር ህመምህ በጊዜ ያለበት ደረጃ ከታወቀ በህክምና ክትትል መፍትሄ የሚገኝለት ደረጃው ጨምሮ ከታወቀ ግን መጨረሻው በቀጥታ ለሞት የሚዳርግ አደገኛ ህመም ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ቴክኖ !
ታዋቂው የሆሊውዱ ትራንስፎርመር ፊልም ከቴክኖ ጋር አብሮ በመሆን ስፓርክ 30 ስልክን ይዘው ብቅ እንዳሉ ያውቃሉ?
ካላወቁ ፊልሙንም አዲሱን የስፓርክ 30 ስልኩንም በቅርበት ለማየት እሁድ ጥቅምት 3 ከ 7 ሰዓት ጀምሮ በሴንቸሪ ሲኒማ በነፃ ጋብዘነዎታል፡፡ ከልጆቾት እና ቤተሰቦት ጋር አዲሱን ስፓርክ 30 ስልክን እያዩ በተለያዩ ስጦታዎች እየተንበሸበሹ አዲሱን ትራንፎርመርስ ፊልም በኛ ግብዣ ይመልከቱ፡፡
@tecno_et @tecno_et
#ኢትዮጵያ
" በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ " - አማኑኤል ሆስፒታል
በየዓመቱ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 10 የሚከበረው " የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን " ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ " በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ጊዜው አሁን ነው " በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።
በኢትዮጵያ ጫፍ እስከ ጫፍ ያሉ የአዕምሮ ህሙማን ወገኖችን በማከም የሚታወቀው አማኑኤል ስፔላይዝድ የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታልም ህሙማኑን በስፓርታዊ ውድድሮች በማሳተፍ ጨምር በዓሉን አክብሮ መዋሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
" የበዓሉ ዋነኛ ዓላማ በዓለም ዙሪያ በአዕምሮ ጤናና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤን ለማሳደግና በአዕምሮ ጤና ክብካቤ ላይ የድጋፍ የሞብላይዜሽን ሥራዎችን ለማጠናከር ነው " ብሏል።
“በአዕምሮ ህሙማን የሚደረጉ መገለሎች አሉ። ሰብዓዊ መብታቸው ሲከበር አይታይም” ያለው ሆስፒታሉ፣ ማንም ሰው በህመሙ ላለመጠቃት ዋስትና የለውምና ህሙማኑን በሥራ ቦታ ጭምር ከማግለል እንዲቆጠብ አሳስቧል።
ይህን ያሉት የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቢይ የኔዓለም፣ ሆስፒታሉ በቀን የሚታዩ የአዕምሮ ህሙማን ብዛት በተመለከተም ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
" በቁጥር ደረጃ በአማካኝ በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ። ቁጥሩ እንደ ሁኔታዎች ይጨምራም፣ ይቀንሳልም። ለምሳሌ አሁን ላይ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎችን ብንወስድ አረመረጋጋቶች አሉ።
እነዚህ አለመረጋጋቶች ደግሞ ሰዎች ወደ ህክምና እንዳይደርሱ ያደርጓቸዋል። ስለዚህ በቅርብ አካባቢ ያሉት ናቸው ወደ ህክምና ሊመጡ የሚችሉት።
ስለዚህ በአማካኝ በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን በተመላላሽ፣ በድንገተኛ በአስተኝቶ ይታያሉ " ነው ያሉት።
መንግስትና አጋር ድርጅቶች ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ በሆስፒታሉ ያሉ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦
" ሆስፒታሉ የግንባት መሠረተ ልማት እጥረት አለበት። ጠባብ በሆነ ቦታ ነው ህክምና የሚሰጠው አስካሁን።
ያው በጤና ሚኒስቴርም በሆስፒታሉ አቅምም የተወሰኑ ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጡ የሚችሉ ውስጥ ላይ የሚሰሩ ማስፋፊያዎች አሉ። እነርሱም በቂ አይደሉም።
ስታንዳርዱን የጠበቀ ግንባታ ነው ሊኖር የሚገባው። ያም በጤና ሚኒስቴር ተይዞ ገና ሌላ ቦታ ላይ የግንባታ ሂደት እየተካሄደበት ያለበት ሁኔታ አለ።
ስለዚህ አንደኛው የመሠረተ ልማት ችግር ነው። ሌላው በስፔሻላይዜሽን ደረጃ በሥነ አዕምሮ ላይ ሰብስፔሻሊቲ ባለሙያዎችም እጥረት የሚታይበት ሁኔታ አለ።
ስለዚህ አጋር ድርጅቶችም መንግስትም ይህንን ትኩረት ሰጥተው በጋራ መረባረብ ቢቻል እንደ አገር የአዕምሮ ጤናን ተደራሽ ማድረግ ማጎልበትም ይቻላል " ሲሉ መልሰዋል።
በሆስፒታሉ ስንት የአዕምሮ ስፒሻሊስት ሀኪሞች አሉ ? ያስፈልጋል ተብሎ የሚታሰበው ምን ያክል ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሻቸው፣ " ሰባት ስፔሻሊስቶች አሉ። ግን በሬሽዎ ሲሰራ ይሄ በቂ አይደለም። በጣም አናሳ ነው። ከዚያ በላይ ነው የሚጠበቀው " የሚል ነው።
" ለአዕምሮ ጤና ክብካቤ ወይም ደህንነት ዋናውና ወሳኙ ከባቢያችን ነው። መሪ ቃሉም በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ግዜው አሁን ነው። ስለዚህ የሥራ ቦታን ደህነት፣ የሰራተኛውን ጤናማ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል " ሲሉ አስገንዝበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#WorldMentalHealthDay
"ሥራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአዕምሮ ጤና ችግር ያጋጥማቸዋል" - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
የ2024 #የዓለም_የአእምሮ_ጤና_ቀን በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል። የዘንድሮው ቀን "የአእምሮ ጤና በስራ ቦታ ላይ" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።
ከአለም ህዝብ 60 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በስራ አለም ላይ እንደሆኑ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።
በስራ ላይ ካሉት ሰራተኞች ውስጥም ግማሽ የሚሆኑት የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥማቸው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዛሬው እለት የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
የስራ አለም ላይ ያሉ ሰራተኞች በሚገጥማቸው የአእምሮ ጤና ችግርም በየአመቱ 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚጠፋ ዶ/ር ቴዎድሮስ ጠቅሰዋል።
ሰራተኞችን ለአእምሮ ጤና ችግር የሚዳርገው ምንድነው?
- ዝቅተኛ የስራ ክህሎት፣ ችሎታ እና አፈፃፀም
- ከመጠን በላይ የሆነ የሥራ ጫና፤ የሰራተኞች እጥረት፤ አድልዎ፣ መገለል፣ ጥቃትና ትንኮሳ
- ረጅም፣ ያልተገደቡ እና ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶች
- አሉታዊ ድርጊቶችን የሚደግፍ ድርጅታዊ ባህል
- ከሥራ ባልደረቦች በቂ ድጋፍ አለማግኘት
- በቂ ያልሆነ ክፍያ፣ የሚጋጩ የሥራ ፍላጎቶች
የአእምሮ ጤና እንደሚያስከትሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ስራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥመው የገለፁ ሲሆን የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ የሚደረገው ኢንቨስትመንት አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
ችግሩን ለመከላከል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ምን መደረግ አለበት አሉ ?
° አሰሪዎች የአእምሮ ጤና ችግር የሚያስከትሉ ችግሮችን በመለየት ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እንደሚገባቸው፤
° የድርጅት ኃላፊዎች ጭንቀት ያጋጠማቸውን ሰራተኞች እንዲለዩ፣ የስራ ቦታ ላይ የሚያጋጥም የአእምሮ ጤና ችግርን እንዲቀርፉ መስራት እንደሚገባቸው፤
° የስራ ከባቢን ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆን ማድረግ፤ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኞች በንቃት እንዲሰሩ የሚያስችል የስራ ከባቢ መፍጠር እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
ሰራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር በሚገጥማቸው ጊዜም ሰዎችን ማውራት፣ ባለሙያ ማማከር ወይም እራሳቸውን ማረጋጋት እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
Via @tikvahethmagazine
" መንግስትን በሃይል ለመፈንቀል የሚደረግ ሙከራ የሚወገዝና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን ይፋ አደርገናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ መስከረም 29/2017 ዓ.ም ከቢቢሲ FOCUS ON AFRICA ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት ፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በውይይት የሚፈታበት መንገድ ዝግ እንዳልሆነ አመላክተዋል።
" ሆኖም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ እየተደረጉ ያሉ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት / መንግስትን በኃል ለመፈቀል የሚደረግ ሙኩራ የሚወገዙና ተጠያቂነት የሚስከትሉ መሆናቸው ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረጋችን ልክ ነው " ብለዋል።
" ሂደቱን ተከትሎ የተጠያቂነት አስራር ተግባራዊ እንደሚሆን ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው " ሲሉ አክለዋል።
የትግራይ ህዝብ ችግሮች በተባባሱበት ወቅት ለምን አንድነታችሁ መጠበቅ አቃታችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ጌታቸው " ይህ ትልቅ ወድቀት ነው ፤ እንደ ድርጅት እና ስራ አስፈፃሚ አባል የሆንኩበት ህወሓት ወድቀዋል ፤ ቢሆንም ጥቂት አመራሮች መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነት በመረዳት ለመፍታት ስንሞክር ቀላል የማይባል ፈተና እና እንቅፋት እየገጠመን ይገኛል " ብለዋል።
ከዚህ በመመለስ ግን ፈተናውን ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
ቴክኖ !
የፊልም አድናቂ ከሆኑ ቴክኖ እና አዲሱ የሆሊውድ ፊልም ትራንስፎርመርስ ዋን በጋራ ስለተጣመሩበት ስፓርክ 30 ስልክ ሰምተዋል?
ካልሰሙ አዲሱን ስፓርክ 30 ስልክ በቅርበት እንዲሁም በቅርብ የተለቀቀውን ትራንስፎርመርስ ፊልም ከልጆት እና ቤተሰቦት ጋር እንዲኮመኩሙ ከ 7 ሰዓት ጀምሮ እሁድ ጥቅምት 3 በሴንቸሪ ሲኒማ በነፃ ጋብዘኖታል፡፡ ይሙጡ በስጦታ እየተንበሸበሹ እሁዶን ፈታ ይበሉ!
@tecno_et @tecno_et
በመሬት ናዳ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ቆርቻ እና ሻናን ዱንጎ ወረዳዎች ትላንት ማክሰኞ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሣ በተከሠተው የመሬት መናድ፣ 10 ሰዎች መሞታቸውን ወረዳዎቹ አሳውቀዋል።
የጉባ ቆርቻ ወረዳ አስተዳዳር ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም በጃርጃታ ቀበሌ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መናድ ምክንያት 4 ሰዎች ሲሞቱ በሌላ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል።
በሻናን ዱንጎ ወረዳ በሌሊስቱ ቀበሌ በዚሁ ቀን በተከሰተው ሌላ የመሬት መናድ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳር ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia
መቐለ ?
የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል።
የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ይትባረክ ኣምሃ በክብር እንዳሰናበተ ተነግሯል።
አዲሱ ' የመቐለ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል ' የተባሉት ዶ/ር ረዳኢ በርሀ በድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና በተነፈገው 14ኛ የህወሓት ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ አባላት ዝርዝር ስማቸው እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የቢሮ ፣ የኮሚሽን ፣ የኤጀንሲ እንዲሁም የዞን አመራሮችና አስተዳዳሪዎች ከሃላፊነት በማንሳት ባካሄደው ጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች " ለመተካት ወሰኛለሁ " ማለቱ ይታወሳል።
የፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አመራር ደግሞ እንቅስቃሴው የመንግስት ግልበጣ ነው ብሎ መግለጫውን በማውገዝ መግለጫውን ባወጡ የህወሓት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ላይ " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ማለቱ ይታወሳል።
በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስለ አዲሱ የመቐለ ከተማ ተሿሚ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ይህን መረጃ እስከተዘጋጀበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ምዕራባዊ ዞን ጨምሮ 6 የትግራይ ዞኖች በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተሾሙ አመራሮች የሚመሩ ሲሆን መቐለ ከተማ ዛሬ በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑ አዲስ ከንቲባ ተሹሞላታል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily
@tikvahethiopia
" አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ዛሬ ረፋድ 4 :00 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ከጎሮ ወደ ኮዬ እየተጓዘ የነበረ ኮድ 3-69867 ቱርቦ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቢስ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋ የደረሰው።
በዚህም የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው የሞቱት ሁሉም ሴቶች ናቸው። ዕድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 የሚገመቱ ናቸው።
3ቱ ሴቶች የአውቶቢስ ትኬት በመቁረጥ ላይ እያሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።
የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
#ፐርፐዝብላክ
° " ሥራ ላይ የነበሩ ሱቆችም የቤት ኪራይ መክፈል ስላልተቻለ ሊዘጉ ነው " - የፐርፐዝ ብላክ ባለአክሲዮኖች
° " በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስላለ ምንም አይነት መግለጫ አንሰጥም " - ድርጅቱ
የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ባለአክሲዮኖች፣ የድርጅቱ አካላት መታሰራቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ላይ ባላቸው ሼር ላይ ሥጋትና ቅሬታ እንዳደረባቸው፣ ለቅሬታቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠየቁ።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?
" እንደ ባለአክሲዮን ኮሚዩኒኬሽን የለንም። ስለዚህ ኮሚዩኒኬሽን እንዲኖረን መንግስትም ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። የባለአክስዮኖች እጣ ፈንታ አስጨንቆናል።
ከዚህ ቀደም ብዙ ሰው ቅሬታ አንስቶ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተናል ብለው ነበር። ግን ጥሪው መጀመሪያ ሚዲያ ላይ አልወጣምና ማንም የሰማ የለም። ቢሯቸው ብቻ ነው የተነጋገሩት። መጨረሻ ላይ ግን ‘አራዝመናል’ ብለው ደግሞ ሚዲያ ላይ አወጡ። ይሄ ሌላ ማታለያ ነው።
አሁን ትልቁ ጭንቀታችን ጠቅላላ ጉባኤም እየተጠራ ስላልሆነ የካምፓኔው እጣ ፋንታ ምንድን ነው? አርሶ አደርን ጨምሮ ሁሉም ያለውን ገንዘብ ነው የሰጠውና ገንዘቡ ተቀምጦ ምን ሊሆን ነው? የሚለው ነው።
በመጀመሪያ የድርጅቱ ኃላፊዎች ከመታሰራቸው ጋር ተያይዞ የድርጅቱ እንቅስቃሴ እንደ ከዚህ በፊቱ እየተገለጸ አይደለም።
ባለአክስዮኖች እስከሆንን ድረስ ያለበትን ሁኔታ አለማወቃችን አሳስቦናል። በሁለተኛ ደረጃ TSM አክስዮን ጋር ተያይዞ ቅሬታ አለን። በጠቅላላ ጉባኤ ለማንሳት ብንሞከርም ትኩረት አልተሰጠም።
የዚህ ፕሮጀክት አካሄዱ እንዲህ ነው፦ TSM Share የገዙ ሰዎች በውሉ መሠረት የቤት ስጦታ ያስገኛሉ፤ ከድርጅቱ ዓመታዊ ትርፍም ተካፋይ ይሆናሉ።
ነገር ግን በTSM share ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ በባንክ ዝግ ሒሳብ ቁጥር እንደተቀመጠ ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ስራዎችን የሚሰራው በመደበኛ እና በFranchise በተሰበሰበው ገንዘብ ነው።
ይህ አሰራር ደግሞ በሌላ ሰው ገንዘብ ተሰርቶ የተገኘው ትርፍ ሌላው እንዲያገኘው ያደርጋል። በምንም ቢታሰብ ምክንያታዊነት የለውም።
በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ሥራ ላይ የነበሩ ሱቆችም የቤት ኪራይ መክፈል ስላልተቻለ ሊዘጉ እንደሆነ እየሰማን ነው " ብለዋል።
ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀለበለት ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ፣ “አሁን ላይ ሁሉም ነገር በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስላለ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጥም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
የድርጅቱ አካውንቶች ጠቅላላ መዘጋታቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ፍስሃ እሸቱ (ዶ/ር) አገር ጥለው መውጣታቸው፣ ቀሪዎቹ ሥራ አስፈጻሚዎች መታሰራቸው አይዘነጋም፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የግላቸውን ጨምሮ የድርጅቱ አካውንቶች በመንግስት እንደተዘጉ፣ የተዘጉበት ምክንያት " በሬ ወለደ " አይነት እንደሆነ፣ " አካውንቶቹ የታገዱት ጽንፈኛ የ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎችን በመርዳት፣ መሳሪያ በማዘዋወር በሙስና ወንጀል፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በሚል እና በሌሎች ነው " ማለታቸው ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ቀኑን ሙሉ ፈታ እንበል! 🥳 M-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው!
በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቦታችንን : /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#SafaricomEthiopia
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
ቤንዚን እና ነጭ ናፍጣ ምን ያህል ጨመረ ?
በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደርጎ የነበረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር 2016 ዓ/ም ነበር።
በወቅቱ ቤንዚን በሊትር 82.60 ብር ፤ ነጭ ናፍጣ በሊትር 83.74 ብር በሊትር ፤ ኬሮሲን በሊትር 83.74 ብር ፤ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 65.48 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 64.22 ብር ተደርጎ ነበር።
ከዛ በኃላ ባሉት ወራት የነዳጅ ዋጋ ባለበት ቀጥሏል።
ዛሬ ግን ጭማሪ ተደርጓል።
በቤንዚን ላይ ከ8 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎ 1 ሊትር ቤንዚን 91 ብር ከ14 ሳንቲም ሆኗል።
በነጭ ናፍጣ ላይ ከ6 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎበት አሁን አንዱ ሊትር 90 ብር ከ28 ሳንቲም ገብቷል።
(ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የነዳጅ ዋጋ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
ካባ
አስቸኳይ ማስታወቂያ ለሜትር ታክሲ መኪና ባለቤቶች
ለአያት እና ሲኤምሲ አካባቢ ቅድሚያ እንሰጣለን
የተማሪዎች ሰርቪስ ለመስራት ፍላጎት ያላቹ ባለመኪኖች
ባለ 4/ 6/7 ሰው የሚይዙ አውቶሞቢል መኪኖች እንፈልጋለን፣
ድርጅታችን ለሚቀጥሉት ወራት መነሻ ከዚህ በታች በፎርሙ ላይ ለተጠቀሱት አካባቢዎች ሆኖ መዳረሻ ቦታ የተለያ አካባቢ ያሉ ት/ቤቶች ያሉበት ሲሆን ጠዋት እና ማታ የተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ መኪኖች በወርሀዊ ገቢ ማሰራት ይፈልጋል
ይህንን አገልግሎሎት መስጠት የምትፈልጉ ባለመኪኖች ወይም አሽከርካሪዎች ይህንን ፎርም ሞልታችሁ ላኩ
ፎርሙን በሞሙላት ይመዝገቡ ይህንን ይጫኑ
https://forms.gle/Wh7RMFYe5v6yBCHN7
ይደውሉ 0960007700
#MoE
በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።
በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።
በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
Via @tikvahuniversity
#Afar
በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል።
ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው።
በክልሉ ጋቢ ራሱ ዞን በሚገኘው ዱለሳ ወረዳ ሳንጋቶ ቀበሌ ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው ትናንት ሰኞ መስከረም 27/2016 ዓ.ም. ምሽት " የመሬት መንቀጥቀጥ " ከተከሰተ በኋላ እንደሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ እና ሁለት የቀበሌው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎች ምን አሉ ?
- ትናንት ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ መከሰት የጀመረው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ያህል ተደጋግሟል።
- የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሚናገሩት ካቆመ በኋላ ሌሊት 10 ሰዓት ገደማ ላይ ድምፅ ሰማን። ጠዋት ላይ ድምፅ ወደተሰማበት ቦታ ስናመራ ከመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ እየፈለቀ ተመልክተናል።
- ውሃው የወጣው የአካባቢው ማህበረሰብ በሚኖርበት ሰፈር ውስጥ ነው። ድምፅ ነበረው። ማታ ፈርተን ነው ያደርነው። በጠዋት ሄደን ሁሉንም ነገር ለማየት ችለናል።
- ውሃው በሚወጣበት የመሬት ስንጥቅ ስር ድምፅ ይሰማል። ወደላይ የሚፈናጠረው ፍል ውሃ መጠን እና የሚፈልቅበት ስንጥቅ መጠን እየጨመረ ነው።
ፍል ውሃው በወጣበት ሳንጋቶ ቀበሌ ውስጥ ፍል ውሃ ባለመኖሩ አዲሱ ክስተት ነዋሪዎች ድንጋጤ እና ስጋት ላይ ጥሏል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ ምን አሉ ?
° ከትናንት በስቲያ ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አንጻር የትናንቱ ትንሽ ያነሰ ነው።
° ከዚህ በኃላ ነው ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው።
° ሰዎች በቅርበት እዚያ አካባቢ ይኖራሉ። የእኛ አካባቢ ማህበረሰብ አርብቶ አደር ከመሆኑ አኳያ ከብቶቻቸውን ፍየሎቻቸውን የሚጠብቁበት ቦታ ነው።
° የወረዳው አስተዳደር ክስተቱን ለማጣራት ባለሙያዎችን ወደ ቀበሌው ልኳል።
° የሚፈጠረው ነገር ስለማይታወቅ ነዋሪዎች’ ከዚያ አካባቢ ለቅቀው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው። እንደዚህ አይነት ነገር ታይቶም ስለማይታወቅ ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው።
የአፋር ክልል ጋቢ ራሱ ዞን በተደጋጋሚ እያጋጠመ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ነዋሪዎች ከሰፈሩበት አካባቢ እንዲነሱ እየተደረገ ነው።
አንዱ አካባቢው ይኸው የዱለሳ ወረዳ ነው።
አጎራባቹ አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ከሁለት ሳምንት በፊት በአካባቢው በሚገኘው ከሰም ግድብ እና ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ ከ700 በላይ ሰዎችን ገላጣ ሜዳ ወደሆኑ አካባቢዎች አዘዋውሯል።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ሲሆን ፎቶና ቪድዮ የአብዶ ሀሰን፣ ሱልጣን ከሚል ነው።
@tikvahethiopia