#አስቸኳይ
“ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት
በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
የታጋቹ እናት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እባካችሁ ልጄን ታደጉኝ ” ሲሉ እያለቀሱ ጠይቀዋል።
“ በሄደ በ17 ቀኑ ከሊቢያ ስልክ በጓደኛው አማካኝነት ተደወለልኝ። ስልኩን ሳነሳ ‘ሊቢያ ላይ ተይዟልና 950 ሺሕ ብር ተጠይቋል’ ብሎ ጓደኛው ነገረኝ ” ያሉት የታጋቹ እናት፣ “ ከዚያ ወዲያውኑ ደግሞ ሊቢያዎቹ እየገረፉት ምስል ላኩልኝ። አካውንትም ላኩልኝ ‘ገንዘብ ላኪ’ ብለው ” ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም፣ “ እንደገና ለ3ኛ ጊዜ መደኃኒት ሰጥተውት እንደ እብድ እያደረገው ቪዲዮ ላኩልኝ። እንደገና ለ4ኛ ጊዜ ደግሞ ወደ ታች #ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ከዚያ ‘ተሽጧል 1.7 ሚሊዮን ብር አምጭ’ ብለው ደወሉ። ቪዲዮ እያሳዩም ‘1.7 ሚሊዮን ብር ታመጫለሽ አታመጭም?’ አሉኝ ” ብለዋል።
በዚህም “ እኔ የለኝም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉልበቴ ስለሆነ ለምኘ፣ እርዳታ አሰባስቤም እከፍላለሁ አልኳቸው። ለ5ኛ ጊዜ እንደገና #ፀጉሩን ላጭተው የሆነ #ውሻ አስመስለው ምስል ላኩልኝ። ከዚያ በኋላ በቃ ‘የጨመረሻ ቀን ብለው’ ደወሉ። ልጄም በጣም #እያለቀሰ ‘አስለቅቂኝ’ አለኝ። እነርሱም ‘ነገ #አርብ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን በፊት ለፊትሽ ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን ” አሉኝ ሲሉ አንብተዋል።
አጋቾቹ ‘ብር ላኪ’ ሲሏቸው ባለማወቅ የመፍትሄ መንገድ መስሏቸው የላኩትን አካውንት በሕግ እንዳሳገዱ፣ በዚህም አጋቾቹ የወጣቱን ስቃይ እንዳበዙት፣ ከታገተ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው፣ ገንዘቡ እስኪሟላ ተጨማሪ ቀን መጠየቃቸውን የገለጹት እናት፤ “ ፌደራልም ሊቢያና ሱዳን ድንበር ላይ የሊቢያ መግቢያ ላይ ነው የታገተው ብለው ነገሩኝ ” ብለዋል።
ወ/ሮ ገነት፣ ምርመራውን ይዞታል የተባሉ የፌደራል ፓሊስ አባል የአጋቹን አካል ቢደርሱበትም በሕግ በኩልም መፍትሄ እንዳላገኙ አስረድተዋል።
ያላቸው አሁናዊ የምርመራ ሂደትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው መርማሪው የፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ “ መልስ መሰጠት የሚችለው እንደ ተቋም ስለሆነ በተቋሙ በኩል ኦፊሻል ደብዳቤ ይዘው በአካል መጥተው አመራሮችን ማነጋገር ይችላሉ ” ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ሆኖም ስለጉዳዩ በደብዳቤ ጠይቀን ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።
እናት አጋቾቹ ከጠየቁት ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው ወደ 350 ሺሕ ብር ብቻ እንደሆነ አስረድተው “ ሀዘን ላይ ነኝ። በቅርቡ ልጄ ሞቶብኛል። አሁን ደግሞ ይሄ ደረሰልኝ ብዬ፣ አሁን እንደዚህ ሆነብኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ረድቶኝ ልጄን እንዲያስለቅቅልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል።
ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000523577402 ሲሆን ሌሎችም የሂሳብ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል።
በስልክ ልታገኟቸው የምትፈልጉ 0916848184፣ 0911720985 ደውሉላቸው።
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል መቋረጡን ያስታወቀው ተቋሙ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።
የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፥ ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙ ተመልሶ እስኪገናኝ ድረስ በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል።
#NB: ተቋሙ ይህንን መረጃ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ከደቂቃዎች በፊት ያወጣው ሲሆን አሁን ላይ በአንዳንድ አከባቢዎች የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል መመለሱን ማረጋገጥ ችለናል።
@tikvahethiopia
" 11 ንፁሃን ነው የተገደሉት " - የዶዶላ ከተማ አስተዳደር
በዶዶላ ባለፈው ሰኞ ዕለት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በተፈፀመ ጥቃት 11 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል አረጋግጧል።
የከተማው አስተዳደር ለሬድው ጣቢያው " በዕለቱ በድንገት በተፈፀመ ጥቃት 11 ሰዎች ሞተዋል። በጥይት ተመተው የተጎዱም አሉ። ከጥቃቱ ጀርባ በገደብ አሳሳ ፣ አዳባ፣ በክልል ደረጃም ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ቡድን አለ የሚል መላምት አለ ግን ምርመራ እየተካሄደ ነው " ብሏል።
ይህ ሁሉ ሰው #ሲገደል የፀጥታ ኃይሉ ለምን በስፍራው አልደረሰም ? ለሚለው ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ ፤ " ጥቃቱ የተፈፀመው በደነባ ክ/ከተማ ደብረ ቅዱሳን ጻድቁ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ነው። ይህ ሆን ብሎ የሃይማኖት አባትን እና ልጆቻቸውን የገደለው እርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ነው ብለን እንገምታለን። በጣም ታስቦበት የተፈፀመ ግድያ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ንፁሃኑ ግድያው የተፈፀመባቸው በቤታቸው እያሉ #በጥይት ተተኩሶባቸው እንደሆነና መንግሥት ግድያውን እንደሚያወግዝ የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።
ለመሆኑ የጥቃቱ ፈፃሚዎች ተይዘዋል ? ለሚለው ጥያቄ ፥ የዶዶላ ከተማ አስተዳደር " ክትትል እየተደረገ ነው " የሚል ምላሽ ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥቷል።
ይህ የአስተዳደሩ ምላሽም አንድም የተያዘ ሰው እንደሌለ የሚጠቁም ነው።
በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ 2 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪና የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
ነዋሪው ፤ አንድ መሪጌታ ከእነባለቤቱ እና ከሁለቱ ልጆቹ ጋ፣ አንድ ዲያቆን ከእነባለቤቱና እህቱ ጋር መገደላቸውን ፤ የመርጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ መቅረቱን ገልጸው ነበር።
@tikvahethiopia
🔥ደማቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወደ ሜዳ ሊመለስ ነው🔥
አንድ ቡድን መርተው ቢያውቁም ፔፕ ጋርዲዮላ እና ሚካኤል አርቴታ ባላንጣ ሆነው ሊሰለፉ ግድ ሆኗል
🏆አስተማሪው ከ ተማሪው ጋርለዓመቱ የመጨረሻ ጊዜ ይገናኛሉ!
🎉ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃትእስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
🎉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ደንበኝነትዎን ሲያሳድጉ... እኛም ቀጣዩን ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET #StepUp
" ... ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ እንመክራለን " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት
የአማራ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ " ሲል #አስጠነቀቀ።
የክልሉ መንግሥት ፥ በአሁን ሰዓት የወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ ለረጅም ዓመታት በ " ህወሓት " በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረው የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተመለሰበት እንደሆነ ጠቁሟል።
ህዝቡም እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል ነው ብሏል።
" የፕሪቶሪያው የሠላም #ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም #በትምህርቱም_መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል " ሲል ገልጿል።
ክልሉ ፤ እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማር መብታቸው እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ገልጿል።
የትምህርት ስርዓቱን ሰበብ በማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ እንዳወጣ ጠቁሟል።
ይህም " ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም " ሲል ተችቷል።
የአማራ ክልል መንግሥት ፥ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሀገራችንን እና ሁለቱን ክልሎች ወደ #ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን " ብሏል።
ሙሉ መግለጫ ፦ /channel/tikvahethiopia/86444
@tikvahethiopia
" እየመጣችሁ ላላስፈላጊ እንግልት እንዳትዳረጉ " - የቤቶች ልማት እና አስተዳደር
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው እየጠበቁ ያሉ ነዋሪዎች ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ #በቲክቶክ እየተለቀቀ ባለ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ወደ ቢሮ መጥተው እንዳይንገላቱ ጥሪ አቀረበ።
ቢሮው ፥ " ' የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ ' በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ ነው " ብሏል።
ተመዝግበው እየተጠባበቁ የምትገኙ ነዋሪዎችም ላተፈለገ እንግልት እንዳይዳረጉ ጥሪ አቅርቧል።
" ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ " ብሏል።
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 21 2016 ዓ.ም 7ኛ ዙር የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ (Computer Programming) ስልጠና ይጀምራል።
👉 100 % በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርትን አካቶ የሚሰጥ
👉 C++, Java እና Python ፕሮግራሞች ከፍ ባለ ደረጃ (Advanced Level) በጋራ የሚሰጡበት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute
#Update
ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጦችን ሲያስተናግዱ በቆዩት በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ውስጥ ካለፉት 3 ቀናት ወዲህ አንጻራዊ የሚባል #ሰላም መኖሩን የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ የአጣዬ ከተማ አስተያየት ሰጭዎች ፣ በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አመልክተዋል። ለደኅንነታቸው ሲሉ ወደ አጎራባች ቀበሌዎች የተፈናቀሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን በአሳሳቢ ችግር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
አልፎ አልፎ ግን የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተዋል፡፡
አንድ የሰንበቴ ከተማ ነዋሪ ፥ " መንገድ ዝግ ነው መንቀሳቀስ አልቻልንም። የጅሌ ጥሙጋና የአርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች ተቆራርጠናል። ተረጋግቷል የሚባለው በሁለቱም ወረዳዎች መንግሥት ሰላም አስፍኖ መንገዶች ሲከፈቱ ነው። አሁን መንገድ አልተከፈተም ሰውም ችግር ውስጥ ነው " ብለዋል።
ነዋሪዎች ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ የፌደራል መንግሥቱ መፍትሔ እንዲያፈላልግ ነዋሪዎቹ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ጥሪ አቅርበዋል።
ሰሞኑን በነበረው የተኩስ ልውውጥ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ ንብረት ወድሟል።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ #ኢፍጧር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።
Photo Credit : Abel Gashaw
#ኢፍጧር #ረመዷን
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ስርዓተ ቀብር ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ተፈጽሟል።
ስርዓተ ቀብሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው።
ተጫዋቹ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቹ አርባ ምንጭ ከተማ በሄደበት ነው ትላንት ለሊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።
Credit - Haleluya Chalata
@tikvahethiopia
ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ
በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል
በቪዲዮው ውስጥ የሚገኙትን ሁለት ጥያቄዎች በመመለስ ተሸላሚ ይሁኑ፡፡ የሚያሸልም ጥያቄ የያዘውን ቪዲዮ ለመመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ https://youtu.be/dN4fLYgAiVA
የጥያቄውን ትክክለኛ ምላሽ ለሚያገኙ 3 የዩቲዩብ ተከታዮቻችን የ#300 ብር የካርድ ስጦታ እናበረክታለን፡፡
👉ምላሹን በዩቲዩብ የሃሳብ መስጫ ሳጥን ብቻ ያስቀምጡ
👉የሽልማት ዕጣው ውስጥ ለመካተት ሁለቱንም ጥያቄዎች በትክክል መመለስ ይጠበቅባችኋል
👉ለሽማቱ እጩ ለመሆን እባክዎ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ ያድርጉ
ተሸላሚዎችን የምንለየው #በዕጣ ይሆናል፡፡
ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከአሁን ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ ትኬቶችን (ህትመት) ሙሉ በሙሉ በአዲስ እንደሚለወጥ አሳውቋል።
ይህ አዲሱ ትኬት (ህትመት) ከነገ ሀሙስ ጀምሮ አገልግሎት ላይ ይውላል።
ትኬቶቹ ከአሁን ቀደም ከነበሩት ፦
* በዋጋ ወጥነታቸው ፣
* በቀለማቸው
* በሚስጥራዊነታቸው የተለዩ ናቸው ተብሏል።
ለአገልግሎት የሚውሉ ህትመቶች (ትኬቶች) ባለ 5 ፣ ባለ 10 ፣ ባለ 15 ፣ ባለ 20ና ባለ 25 የዋጋ ተመን (ብር) ያላቸው ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ፦
- የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት እና
- የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ተዋህደው በአዋጅ ቁጥር 74/2014 የተቋቋመ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸውን ያለሆነ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወስደው በከፊል የመለሱ ወይም ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ያላደረጉትን 5,166 ግለሰቦች ስም ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ግለሰቦቹ ቀሪ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ወደ ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚገባ ገልጿል።
ስማቸውን ከፎቷቸው ጋር በማድረግ ህገወጥ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን ለህግ አካላትና ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
@tikvahethiopia
የ3 አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር #ገድሎ ተሰውሮ የነበረ ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ።
ቢሊሱማ መሃመድ የተባለችን የ3 አመት ህጻን የእንጀራ ልጁን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የሟቿ ህጻን እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል ባለመቻላቸው ምክንያት ከተለያዩ በኃላ ወደ ሀሮማያ ከተማ በመሄድ ሌላ ባል አግብታ ህጻኗም ከእናቷ እና እንጀራ አባቷ ጋር ትኖር ነበር፡፡
ተከሳሹ የእንጀራ አባቷ ግለሰብ ለ15 ቀን በትዳር ከቆየ በኃላ ገና ምንም ነፍስ እንኳን ያላወቀችውን ህጻን አስገድዶ ደፍሮ መግደሉ ተገልጿል።
ለ11 ወራት ያህል ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተጠቁሟል።
ግለሰቡ ለምን ይችን ገና ነፍስ እንኳን ያላወቀች፣ ክፉ ደጉን የማትለይ ህፃን አስገድዶ እንደደፈረና እንደገደለ ሲጠየቅ " ሰይጣን አሳስቶኝ ነው " ማለቱን ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Via @TikvahethMagazine
ልዮ የኪነ-ጥበብ ምሽት
" አብሮነት ኢትዮጵያዊነት " የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት አ/አ ካዛንቺስ በሚገኘው በኢንተርኮኒቲኔታል ሌግዤሪ አዲስ ሆቴል ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከ9 ሰዓት ጀምሮ በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት ይቀርባል።
በእለቱ ፦
- መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ፣
- አባሣደር ዲና ሙፍቲ፣
- ዲያቆን መምህር ዳንኤል ሠይፈሚካኤል
- ደራሲ ገጣሚ ፀሀፊ ተውኔትና ባለ ቅኔ አያልነህ ሙላቱ፣
- ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ ፣
- ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣
- ዶ/ር ዮናስ ዘዉዴ
- አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣
- ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ
- አርቲስት ተስፋዬ ሲማ በእለቱ ግጥም ወግ መነባንብ ዳስኩር በሻሎም የባህል ባንድ ታጅበዉ ያቀርባሉ።
መግቢያ 500 ብር
የመግቢያ ትኬቱን
~ ለገሃር በጃፋር ቤተ መፅሀፍት
~ ብሔራዊ አይናለም ቤተ መፅሀፍት
~ በካዛንቺዝ ኢንተር ኮንትኔንታል ሌግዠሪ አዲስ ሆቴል ያገኙታል።
0930470847 ወይም 0912374014
#Update
ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ መገናኘት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
አብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍል እና የተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች መልሰው ኃይል ማግኘት እንደቻሉ ተገልጿል።
የተቀሩትን አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ጥረቱ መቀጠሉ ተነግሯል።
@tikvahwthiopia
#እናት
እናት ፓርቲ ፥ " መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችንና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆም ከደሙ ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል።
ይህን ያለው ከሰሞነኛው የዶዶላው ግድያ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው።
" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ባለፋት ሶስት አስርት ዓመታት እጅግ በጣም አሰቃቂ ጥቃት ደርሶባቸዋል " ያለው ፓርቲው " በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት በቤተክርስቲያኗ እና ምእመናኗ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ግፍ እና አሰቃቂ ግድያዎች ክፉኛ ተጠናክረው ቀጥለዋል " ሲል ገልጿል።
ፓርቲው ፥ በዶዶላ ከተማ ባለፈው ሰኞ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ መርጌታ፣ 2 ልጆቻቸው እና ባለቤታቸውን ጨምሮ ከ2 ወራት በፊት ሥርዓተ ጋብቻቸውን የፈጸሙ ሙሽሮች (አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ታላቅ እህቱ ጋር) በአጠቃላይ 7 ንጹሐን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸውን አመልክቷል።
በተጨማሪም በቀን ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ 4 ንጹሐን ዜጎችም በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ገልጿል።
ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 7 ሰዎችም በዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቁሟል።
ፓርቲው ፤ " ከዚህ ማብቂያ ካጣው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆምና መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከእነዚህ ንጹሐን ደም ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል።
@tikvahethiopia
ኮንሰርት፣ ባዛር ሲያዘጋጁ
ፊልም/ቲያትር ሲያቀርቡ
የሚታይ የሚጎበኝ ሲኖርዎት
የመግቢያውን ትኬት
እኛ እንሽጥልዎት!
https://www.facebook.com/combanketh
/channel/combankethofficial
**********
በሲቢኢ ብር መተግበሪያ የትኬት ሽያጭ አገልግሎት
በቀላሉ ሚሊዮኖች ጋር ይደርሳሉ!
#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#እንድታውቁት
አዲስ አበባ ከተማ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፍጹም መቆም የሚከለክሉ የትራፊክ ምልክቶች ተተክለዋል።
በስራ መግቢያ እና ከስራ መውጪያ ሰዓትም በአካባቢው ላይ በመንገድ መዘጋጋት ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።
በዚሁ መሰረት ፤ " ፍጹም መቆም የሚከለክሉ " ምልክት የተተከለባቸው ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ መታሰቢያ የሚወስድ ዋና መንገድ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ አድዋ ሙዚዬም ዙሪያ እና ማዘጋጃ ዙሪያ ከዛሬ መጋቢት 19/2016 ጀምሮ ጥብቅ ቁጥጥር ይጀመራል ተብሏል።
በአካባቢው በግዜያዊነት ለተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚውል የአድዋ ሙዚዬም "ሰርፌስ ፓርኪንግ" አገልግሎት መስጠት ስለጀመረ አሽከርካሪዎች እንደ አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ ፦
- ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
- ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ፣ አማራጭ መንገድ ከአራት ኪሎ-አባድር
- ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
- ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዘበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ለመቅረፍ ፤ አማራጭ #ማስተንፈሻ የሚሆን መንገድ በተለምዶ ከቀይባሕር ኮንደሚንየም ወደ ደጎል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዛሬ ከሰዓት ለተሽከርካሪዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።
መረጃው የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ።
* " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል
የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል " ብሏል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ስርዓትን በማጣቀስ " የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል " ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ ነው ሲል ገልጿል።
#በትናንትናው እለት ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል ሲል የአማራ ክልል ከሷል።
(ሙሉው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114
https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
" ቲክቶክ እንዲታገድ ለካቢኔው ጥያቄ አቅርቢያለሁ " - የኢራቅ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር
የኢራቅ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሂያም አል-ያስሪ ' ቲክቶክ ' የተሰኘው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ መተግበሪያ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ካቢኔ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናገሩ።
" የኢራቅን የማህበራዊ ህይወት ትስስር እየሸረሸረው ነው " ያሉት ሚኒስትሯ የእግድ ጥያቄውን በቅርቡ ካቢኔው እንደሚያየውና እንደሚነጋገርበት ገልጸዋል።
" መተግበሪያው ማህበረሰቡን የሚጠቅም የረባ ትምህርታዊ ጠቀሜታ የለውም ሙሉ በሙሉ መዝናኛ ላይ ያተኮረ ከምንም በላይ የኢራቅን ህዝብ ባህል፣ እሴት አጠቃላይ ትስስርን የሚሸረሽሩ ይዘቶች የሚሰራጩበት ነው " ብለዋል።
የኢራቅ ፓርላማ እንዲህ ያለው መተግበሪያ እንዲታገድ ድጋፍና ትብብር ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።
@tikvahethiopia
#Update #ራያ
° “ ከያዙት ቦታ የሚገኘውን ኮስም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረቱ ዘርፈው ጭነውታል። አፍሪካ ህብረት ሁሉንም ታዝቧል ” - የአላማጣና አካባቢው አመራር
° “ ጉዳቱ በጣም ከፍ ያለ ነው። አጥንቱ ደቋል ” - የተጎጂ ቤተሰብ
በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ተቀሰቀሰ የተባለውን ተኩስ በተመለከተ በአማራ ክልል በኩል ሆነው ቃላቸውን የሰጡ አንድ የአካባቢ ከፍተኛ አመራር ከትላንት ወዲህ ያለውን ሁኔታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አብራርተዋል።
እኚሁ አመራር ፤ “ ዛሬ አፍሪካ ህብረት መጥተው ማን ስምምነቱ እንደጣሰ ተመልክተዋል። አፍሪካ ህብረት እያንዳንዱን ችግር አይተውታል ” ብለዋል።
“ ዛሬ ተኩስ የለም። የያዙት ቦታ አሁንም አለቀቁም። ከያዙት ቦታ የሚገኘውን ኮስም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረቱ ዘርፈው ጭነውታል። አፍሪካ ህብረት ሁሉንም ታዝቧል። መከላከያ ያለውን እውነታ አስረድቷቸዋል ” ሲሉ አክለዋል።
“ የሞተውን ዛሬ በክብር ቀብረነዋል። ማቹ ተፈራ ፍቃዱ ይባላል። የሁልግዜ ለምለም ቀበሌ ነዋሪ ነው። ቀብሩም ከቀኑ 7፡00 በጎልአጆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። ሪፈር የተላኩ አልተመለሱም ” ሲሉ ተናግረዋል።
በተኩሱ ጉዳት ደርሶባቸው ሪፈር ተጽፎላቸዋል ከተባሉት ሁለት ቁስለኞች መካከል የአንዱ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ጉዳቱ በጣም ከፍ ያለ ነው። አጥንቱ ደቋል። በአላማጣ አዋሳኝ በኩል ድንበር ላይ ቆሞ እያለ ነው በእነርሱ (በህወሓት) በኩል ጥቃት የደሰበት” ብለዋል።
“ በጣም ከፍተኛ ጉዳት አለው ሁለቱም እጆቹ ከኋላውም ቀላል ጉዳት ደርሷል። ግን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሁለቱ እጆቹ ላይ ነው። ወደ ደሴ ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎለት እንደገና ደሙ አልቆም ሲል ወልዲያ ሆስፒታል ከትላንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ (መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ/ም) 7፡00 ገብቶ ነበር። ከዚያ በኋላም ወደ ግል ክሊኒክ ገብቷል። ሁለቱም እጆቹ ላይ ስለሆነ በጣም ስቃይ አለው ” ሲሉ አክለዋል።
" በድንበራችን ላይ መጥተው ነው ጥቃህት ያደረሱት" ብለው፣ መንግሥት ለጉዳዩ ትከረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
የትግራይ እና የአማራ ክልል አዋሣኝ ቦታ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች በራያ በተፈጠረው ጉዳይ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ።
በትግራይ ክልል በኩል ያሉ አመራሮች ሰሞነኛውን ተኩስ የከፈቱት የአማራ ክልል ታጣቂዎች እንደሆኑ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ግጭቱም ሆን ተብሎ ፦
- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ
- የትግራይ ማህበረሰብ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉት ውይይትና የአማራ እና የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንቶች በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ዙሪያ የፈጠሩት መድረክን ተከትሎ 'ውሉ ተግባራዊ ይሆናል' የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው ነው " ብለዋል።
" አሁንም የአማራ ክልል ታጣቂዎች ለቀጣይ ትንኮሳ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ደርሰንበታል " ብለዋል።
የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ውል እንዲከበርና የአማራ ክልል ታጣቂዎች በኃይል ከያዟቸው የትግራይ አካባቢዎች እንዲወጡ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
እስካሁን ድረስ በሁለቱም በኩል በክልል ደረጃ ስለ ጉዳዩ ያወጡት መግለጫ የለም። የፌዴራል መንግሥትም ያለው ነገር የለም።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia
#Update #ራይ
" ግጭቱ ከ20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም፤ በግጭቱ የሞተ ሰውም የለም " - በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ግደይ ካልኣዩ
" የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲያስቆመው ተደርጓል " - የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም
የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባናል ጥያቄ በሚያነሱበት የራያ አላማጣ አካባቢ ግጭት መነሳቱን አንድ የራያ አላማጣ እና አካባቢው አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለፃቸው ይታወሳል።
አመራሩ ፥ " ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ ጦርነት ከፍቷል፤ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የተኩሱ መነሻ በራያ እና ወልቃይት በትምህርት ስርዓቱ ካርታ ላይ ተካተዋል የሚል ነው " ብለው ነበር።
በትግራይ በኩል ምን ምላሽ ተሰጠ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ካልኣዩ ግደይና የክልሉን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ጠይቋል።
አቶ ካልኣዩ ግደይ በፅሁፍ በሰጡት ምላሽ ፥ " ግጭቱ የተከሰተው መጋቢት 17 /2016 ዓ.ም ቀን ነው። በር ተኽላይና ዶዶታ በተባለ አከባቢ ነው። ቶክሱን የጀመሩት የአማራ ታጣቃዎች ሲሆኑ በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ላይ ቶክስ የከፈቱት በአለማጣ ከንቲባ አቶ አበራ ሃይሉ ጥሪ የተደረገላቸው የአማራ ክልል ታጣቂዎች ናቸው " ብለዋል።
ግጭቱ 20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም ያሉት አስተዳዳሪው በግጭቱ የሞተ ሰው የለም ብለዋል።
" ግጭቱ ሆን ተብሎ ፦
- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ
- የትግራይ ማህበረሰብ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉት ውይይትና የአማራና የትግራይ ፕሬዚዳንቶች በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ዙሪያ የፈጠሩት መድረክን ተከትሎ 'ውሉ ተግባራዊ ይሆናል' የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው ነው " ብለዋል።
አቶ ካልኣዩ አክለው " የአማራ ክልል ታጣቂዎች ለቀጣይ ትንኮሳ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ደርሰንበታል " ብለዋል።
የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የራያ ጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ በፅሁፍ የሰጡት መረጃ እንዲያረጋግጡለት ፤ የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም አግኝቶዋቸዋል።
አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፥ የራያ ጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ መረጃ ' ልክ ነው ' ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር ፤ " የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲያስቆመው ተደርጓል " ሲሉ ተናግረዋል።
" የፌደራል መንግስት በትግራይ ግዛት ውስጥ በመግባት ተደጋጋሚ ግጭት በመፍጠር ላይ የሚገኙ የአማራ ክልል ታጣቃዊች በዘላቂነት እንዲያስታግስ እና በሃይል ከያዙት ግዛት ለቀው እንዲወጡ የሚያስገደደው የፕሪቶሪያ የሰላም ውል እንዲተገብር ደግመን ደጋግመን እንጠይቃለን " ብለዋል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ #ኢፍጧር " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " በሚል መሪ ቃል ህዝበ ሙስሊሙ ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የመጅሊሱ አመራሮች ፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ፣ የመንግስት ኃላፊዎች ፣ የእምነት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ምዕመናን በፕሮግራሙ ለመታደም በቦታው እየተገኙ ይገኛሉ።
Credit - Ustaz Abubaker Ahmed
@tikvahethiopia
የምስራች ከሳፋሪኮም !
የሳፋሪኮም የቀን፣ የሳምንት እና የወር እንደልብ ጥቅሎችን እየገዛን በፈጣኑ የሳፋሪኮም 4G ኢንተርኔት እንንበሽበሽ!።
በM-PESA APP ተጠቅመው የእንደልብ ጥቅሎችን በመግዛት ጊዜያችንን ያለሃሳብ ዘና ፈታ እያልን እናሳልፍ!
ያልተገደበ ወርሃዊ በ999ብር ብቻ
ያልተገደበ ሳምንታዊ በ350 ብር ብቻ
ያልተገደበ ዕለታዊ በ60ብር ብቻ
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
👉Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
👉Telegram: /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
👉Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
👉Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
👉 YouTube: safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm" rel="nofollow">https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm
#CBE
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ገንዘቡን እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር።
በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መልሰዋል ብሏል።
5166 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ ከወሰቡትን ገንዘብ በከፊል ተመላሽ ያደረጉ ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ ቀሪውን ገንዘብ አልመለሱም ሲል ገልጿል።
ባንኩ ወደ ቀጣዩ #ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ቀሪውን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ገንዘቡን የማይመልሱ ከሆነ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል።
እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን #የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ፦
- ሙሉ ስማቸው
- ፎቷቸው
- በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት ይገለጻል ለሕዝብም ይፋ ይደረጋል ብሏል።
ከሕግ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ #የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔር እና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎችም እንደሚወሰዱ በጥብቅ አስጠንቅቋል።
ስም ዝርዝሩን በዚህ መልከቱ ፦ /channel/tikvahethiopia/86375
@tikvahethiopia
ራያ ላይ ምን እየሆነ ነው ?
“ ህወሓት የፕሪቶርያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” - የአላማጣና አካባቢው አመራር
የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱበት አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ አካባቢ ትላንትና " ህወሓት " ተኩስ መክፈቱን፣ በዚህም በሰው ሕይወት ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ሙድረሱን አካባቢውን ከሚያስተዳድሩ አመራሮች (ባለስልጣን) አንደኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ የአካባቢው አመራር (ባለስልጣን) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ራያ ላይ አዲስ ነገር አለ። ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” ብለዋል።
“ ቀን ላይ አንድ ሰው ሕይወቱ አልፏል። ሁለት ቆስለው ወደ ደሴ ሪፈር ተብለዋል። ደንበሩን በማለፍ የራያ አላማጣ ወረዳ አዳዲስ ቀበሌዎች ተቆጣጥሯል ” ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጦርነቱ የተከፈተው በምን ሰዓት ነው ? በዬት በኩል ነው የተከፈተው ? አሁን ተኩስ አለ ? በቁጥጥር ስር የሆኑት ቀበሌዎች እነማን ናቸው ? ከሰሞኑን ለጦርነት አመላካች ጉዳዮች ነበሩ ? ሲል ለአመራሩ ጥየቄ አቅርቧል።
አመራሩም ፣ “ ጦርነቱን የጀመሩት ሰኞ ሌሊት 6:00 አከባቢ ሲሆን፣ እስከ ቀን 6:30 ድረስ ነበር። መከላከያ ለራያ ምሊሻ ‘ወደ ኋላ ተመለሱ እነርሱም ይመለሳሉ’ በማለቱ ምክንያት ጦርነቱ ቁሞ የራያ ምሊሻ ወደ ኋላ ቢልም TDF መልሶ ቦታውን ተቆጣጥሮታል ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ተኩሱ የተጀመረበትን ልዩ ቦታ በተመለተ በሰጡት ምላሽም ፣ “ የተጀመረበት ቦታው ‘ጮጓራ’ ይባላል። የራያ አላማጣ ቦታ ነው። አሁንም እሱን በማለፍ ወደ ‘ኮስም’ የሚባል አከባቢ እየተጠጉ ነው። ተጨማሪ ኃይልም እያስጠጉ ይገኛሉ ” ብለዋል።
የአካባቢው አመራር የተኩሱን መነሻ በገለጹበት አውድ ፣ “ የዚህ ዋናው መንስኤ አማራ ክልል #ወልቃይት እና #ራያ በስርዓተ ትምህርቱ ካርታ ላይ ተካተዋል በሚል በወጣው መግለጫ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።
“ የራያ ህዝብ የዘመናት ትግሉ በህጋዊ መንገድ ፍትህ ማግኘት እንጂ ጦርነት አይፈልግም። እነሱ እየተከተሉ ደጋግመው እያቆሰሉት ነው ” ሲሉም አክለዋል።
በህወሓት ተከፈተ ስለተባለው ተኩስ በትግራይ ክልል በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ አስታዳዳሪዎችን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ስብሰባ ላይ እንደሆኑና ወደ በኃላ ማብራሪያ እንደሚሰጡን ገልጸዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፣ “ የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ማለቱ አይዘነጋም።
አስተዳደሩ ፤ በአማራ ክልል መንግሥት በኩል በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እና በደል ሲፈፀም እንደቆየ አሁንም እንደቀጠለ ገልጾ ክልሉ የሰላም ስምምነቱን የሚያናጋ ጠብ አጫሪ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሆነ ከሶ ነበር።
የፌደራል መንግስት በካርታው ላይ ምንም አይነት እርማት እንዳልሰጠ ፣ የአማራ ሕዝብም ሆነ ሌለው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ ግን የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቆ ነበር።
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ እረፍት ለመውሰድ ወደ ቤተሰቦቹ አርባ ምንጭ ከተማ በሄደበት በድንገት ህይወቱ እንዳለፈ ተነግሯል።
ህይወቱ ያለፈው ለሊት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።
ወደ አርባምንጭ የሄደው ያጋጠመውን መጠነኛ ጉዳት ተከትሎ እረፍት ለመውሰድ ነበር።
የህልፈቱ ምክንያት " ድንገተኛ " ተብሎ ከተገለፀው ውጭ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።
ተጫዋቹ ባለትዳር ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር በስርዓተ ቁርባን ጋብቻውን የፈፀመው።
የአለልኝ አዘነ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መጋቢት 18 በትውልድ ከተማው አርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ታውቋል።
Via @tikvahethsport
@tikvahethiopia
#ራታዝ_ብራንድ
ራታዝBrand ጥራት ያላቸው ጫማዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በፈለጉት መጠን እኛ ጋር ያገኛሉ፤ እንዲሁም በየግዜው እቃ ስናስገባ እንዲደርሶ በቴሌግራም ገጻችን ቤተሰብ ሆነው ይከታተለሉ🔽
/channel/+OpJ4wNqSEqZhNTA8
አድራሻ ፦ አ.አ ቦሌ መ/ም አደባባይ ራክሲም ፕላዛ 3ኛ ፎቅ ሱ.ቁ 03። Free delivery
📱0911799616 ✉️@properties6
RATAZ:-thrive with us you will get greater value!