ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ
ፋዌ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እድሚያቸው ከ 15 እስክ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴት እና የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡
ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ኮርሶች ነው፡፡
ምዝገባው የሚካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን አመልካቾች በ2014፣2015 ወይም 2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ እና የ2017ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ውጤት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
የማመልከቻ ቀናት ከጥቅምት 22-29/2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0911330024 / 0902662688
አዳማ በ 0911383055
ባህርዳር በ 0913042043
ሀዋሳ በ 0965679139 በመደወል ወይም በድረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር ነው!
ምዝግባዉም ሆነ የመረጣው ሂደተ ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃልን
#US
ነገ በአሜሪካ ከሚደረገው ኦፊሴላዊ የድምፅ መስጫ በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች " ለሀገራችን ይሆናታል ፣ ይበጃታል " ያሉትን መርጠዋል።
አሜሪካ እና ዜጎቿ በዓለም ከሚታወቁባቸው ጉዳዮች አንዱ የምርጫ ስርዓታቸው ነው።
የሀገሪቱ ዜጎች በምርጫ ጉዳይ ቀልድና ፌዝ አያውቁም ምክንያቱም የነገ ዕጣፋንታቸው የሚወስነበት ስለሆነ።
ለዚህ ነው በነቂስ እየተሳተፉ " ይሆነናል ፣ ለሀገራችን ይጠቅማል " የሚሉትን ተመራጭ የሚመርጡት።
በዘንድሮው ምርጫ ካማላ እና ትራምፕ አንገት ለአንገት የሚተናነቁበት እጅግ ብርቱ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
" ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ነው " - ቅዱስነታቸው
ዛሬ የሰላም ሚኒስቴር አንድ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህ መድረክ ላይም የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አዱዓለም ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ፣ የመንግሥት ባለስልጣናት ፣ አባሳደሮች ጭምር ተገኝተው ነበር።
በመድረኩ ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?
(ከመልዕክታቸው የተወሰደ)
" ሰላም የሰው ልጆች ፍላጎት፣ የብዙ ምንዱባን የየዕለት ናፍቆት ነው። የበርካታ ዘመናት ቅርሶች፤ ጊዜ፣ ገንዘብ እና የሰው ጉልበት የፈሰሰባቸው ግንባታዎች በሰላም ማጣት በቅጽበት ይፈርሳሉ።
ሰላም ካለ የዓለም ሀብት ለሁሉም በቂ ነው። ሰላም ማጣት ግን ብዙ ሠራዊት፣ ብዙ የጦር መሳሪያ እንዲዘጋጅ እያደረገ ሀብትን ያወድማል።
ጦርነት ማለት ሀብትና ሕይወትን ወደሚነድ እሳት ውስጥ መጣል ነው።
የአንደኛና የሁለተኛ ዓለም ጦርነት፣ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ጠባሳው አሁንም የዓለምን መልክ አበላሽቶታል።
ሰላም በውስጥዋ ገራምነት፣ ትዕግሥት፣ ታዛዥነትና በትህትና ዝቅ ማለት ስለሚገኙ መራራ ትመስላለች፤ በውጤቷ ግን ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከመከራ ማትረፍ የሚቻል በመሆኑ ዋጋዋ ከፍ ያለ ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፦
° ሰላም የሆነው ክርስቶስ የሚሰበክባት፣
° የሰላም መልእክተኞች በውስጥዋ የሚመላለሱባት፣
° በግብረ ኃጢአት የወደቁት በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁባት የሰላም ድልድይ ስለሆነች በሥርዓተ ቅዳሴዋ ሰላምን ደጋግማ ታውጃለች፤ በጸሎቷ ለመላው ዓለም ሰላምን ትለምናለች፤ በጉልላትዋ ላይ የሰቀለችው መስቀልም ሰላምን የሚሰብክ ነው፤ የመስቀሉ ቅርፅ ወደ ላይና ወደ ጎን መሆኑም ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ሰላም መሆን እንዳለብን የሚያስገነዝበን ነው።
ታሪካችን እንደሚነግረን ወንድማማቾች ሲጋደሉ፣ በሕዝብ መካከል መተላለቅ ሲመጣ ቤተ ክርስቲያን ታቦት አክብራ፣ በእሳት መካከል ገብታ ሰላምን ስታወርድ የኖረች ናት።
በሀገር ውስጥ ግጭቶች በተፈጠሩበት ጊዜም የሰላም ጥሪን ያላስተላለፈችበት ቀንና ሰዓት አይገኝም፡፡
ሰላምን የመወያያ ርእስ አድርገን ስንሰባስብ በጦርነት መካከል የተጨነቁ ሕዝቦች፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እና ምን እየተደረገ እንዳለ በውል የማይገነዘቡ ደካሞች ተስፋ ያደርጉናል።
ስለዚህ ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ስለሆነ ይህ ጉባኤ ከውይይት ባሻገር በተግባር ጭምር የሰላም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው ለማሳሰብ እንወዳለን። "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Customs
በኤርፖርት ጉምሩክ አንዲት የአረብ ሀገር ተመላሽ ባጋጠማት ጉዳይ ቤተሰቦቿ አንድ መልዕክት ልከዋል።
ግለሰቧ አሁን ላይ በእስር ላይ የምትገኝም ሲሆን ከቀናት በፊት የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባት እያተጠባበቀች ነው።
ያንብቡ 👇
tikethiopia/GycVvbDJpme" rel="nofollow">https://teletype.in/@tikethiopia/GycVvbDJpme
@tikvahethiopia
" ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይመስላል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን 4ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ትላንት እሁድ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።
ጉባኤው ትኩረቱን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት እና ስራ ከጀመረነት ጌዜ አንስቶ ምን ምን አብይ ጉዳዮችን አከናወነ ? ምን እንቅፋቶች ገጠሙት? ለእንቅፋቶቹስ ምን መፍትሄ ሰጠ የሚለውን ዋና የመወያያ አንጀዳ አድርጎ ነበር።
በዚሁ መድረክ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።
ዳንኤል (ዶ/ር) ፤ " ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ ? የሚለው ነው " ብለዋል።
መንግስትም ሲጠየቅ " ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ " ይላል።
ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ " እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው " ይላሉ።
ስለዚህ ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሉ ገልጸዋል።
" ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም " ብለዋል።
ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን አንስተዋል።
" ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" የተዓማኒነት ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ችግር ባይሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም ነው " ያሉት።
" አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ነው " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ " ከችግሩ ክብደት አንጻር ላይገርም ይችላል ነገር ግን ብዙ ነገሮች እየመጡ ሲያልፉ አይተናል አሁን ያለውም ችግር ከኢትዮጵያውያኖች አቅም በላይ ነው ብዬ አላስብም " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaAddisAbaba
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
" በሽጉጥ አስፈራርተው ነው መኪናውን ይዘው የተሰወሩት " - ቤተሰቦች
ሶስት የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የሜትር ታክሲ አሽርከርካሪን በሽጉጥ አስፈራርተው መኪናውን ይዘው መሰዋራቸውን ቤተሰቦች አሳውቁ።
ድርጊቱ የተፈጸመው እሮብ በቀን 20 /2/2017 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 6:30 አካባቢ ነው።
አዲስ አበባ ከኢምፔሪያል ሆቴል ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ጋር ከአትላስ ሆቴል ሦስት ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን አሳፍሮ ሲጎዝ የነበረው የሜትር ታክሲ ሹፌር ገርጂ ኖክ ማደያ አካባቢ በሽጉጥ አስፈራርተው መኪናውን ይዘው እንደተሰወሩ የአሽከርካሪው ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የመኪናው አይነት yaris compact ከለሩ ነጭ የሆነና ታርጋ ቁጥር code 3 B14395 እንደሆነ ጠቁመዋል።
ስርቆቱ ሲፈፅም የኃላው መስታወት ሙሉ ለሙሉ የተሰበረ እንደሆነም አክለዋል።
ተሽከርካሪውን ያየ ማንኛውም አካል በስልክ ቁጥሮች በ0912274400 ፣ 0913518744 ወይም ደግሞ አካባቢው ላይ ላለ ማንኛውም የፖሊስ አካል ጥቆማ እንዲሰጥላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
💫ከዳር እስከ ዳር በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት! እንገናኝ!✨ የተመቸንን ሼር እናድርግ!👍ከወደድነው ጋር እንደልብ እንገናኝ!
አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ !
ፋዌ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እድሚያቸው ከ 15 እስክ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴት እና የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡
ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ኮርሶች ነው፡፡
ምዝገባው የሚካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን አመልካቾች በ2014፣2015 ወይም 2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ እና የ2017ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ውጤት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
የማመልከቻ ቀናት ከጥቅምት 22-29/2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0911330024 / 0902662688
አዳማ በ 0911383055
ባህርዳር በ 0913042043
ሀዋሳ በ 0965679139 በመደወል ወይም በድረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር ነው!
ምዝግባዉም ሆነ የመረጣው ሂደተ ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃልን
#DStvEthiopia
አዲስ አሰልጣኝ ፣ አዲስ ድራማ ? ማን ዩናይትድ የድል መንገዱን ይቀጥል ይሆን? ድሉ የማን ነው?
Man United vs Chelsea ዛሬ ጥቅምት 24 ከምሽቱ 1፡30
👉 ይህንን ደማቅ ፍልሚያ ለማየት ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#Earthquake
ከለሊቱ 6:04 ላይ አፋር ክልል፣ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ ተሰምቷል።
በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል።
አርብ ምሽት 3:55 ላይ እንዲሁም ለሊት በዚህ ሰዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር።
በአዋሽ የሚገኝ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " አላህ ክፉን ሁሉ ያርቀው ፤ እጅግ በጣም ያስፈራ ነበር " ሲሉ የዛሬ ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
#ቦትስዋና
" የሀገራችንን የሰላም እሴቶች እናስቀጥል ፤ ... እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋግጥላችኋለሁ " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ
ዱማ ቦኮ የቦትስዋና ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ።
ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫው ተሸንፈዋል።
ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል። ፓርቲውን ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ሸንፈትን ተከናብቧል።
ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ በከፍተኛ ብልጫ አሸንፏል።
ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ፤ ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ቢፈልጉም በሰላማዊ ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለዋል።
በሀገራቸው የዲሞክራሲ ሂደት ግን እጅግ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ገለል ብለው በሽግግሩ ላይ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።
ለተመራጩ ፕሬዜዳንትም ስልክ ደውለውላቸው በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው " እንኳን ደስ አለህ " ብለውታል።
መላው ህዝብም በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም በጋራ የሀገሪቱን #የሰላም እሴቶች እንዲያስቀጥል ፤ እንዲያስከብር ጥሪ አቅበዋል።
እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አረጋግጠዋል።
ሀገሪቱን ለማገልገል ለተሰጣቸው እድልም ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት አመስግነዋል።
ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
" አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 ሚሊዮን ብር ከፍለን ሌላውን እየፈለግን ነበር ግን ቀድመው ጀናዛቸውን ላኩልን " - ቤተሰቦች
በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር መገደላቸው ተሰምቷል።
የዛሬ ወር ገደማ ሸይኹ የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር እሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የአንድ አካባቢ ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸው የተገለጸው።
በወቅቱ ከታገቱት ሰዎች በተጨማሪ ከ80 በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውም ተገልጿል።
በተደረገው የገንዘብ ድርድር ከታገቱት ሰዎች መካከል የሸይኹ እናትና ባለቤታቸው ጨምሮ ጥቂት ሰዎች የተለቀቁ ቢሆንም ሼይኽ ሙሀመድ መኪንን ጨምሮ 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተገድለዋል።
አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 የሚሆነው ከፍለው ቀሪውን እየፈለጉ እንደነበር የተገለፁት ቤተሰቦች " ነገር ግን ቀድመው ጀናዛ ላኩልን የተፈፀመብንን ከባድ ግፍ ነው ያጣነው ታላቅ አሊም፣ አስታራቂ ሽማግሌ የነበሩ ሰው ነበር ያለምንም ምክንያት ነው በግፍ የተገደሉት " ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሀሩን ሚዲያ ነው።
@tikvahethiopia
#አፋር #ትግራይ
የትግራይ እና የዓፋር አጎራባች ዞኖች አመራሮች ዛሬ ጥቅምት ለሁለተኛ ጊዜ በዓፋርዋ የአብዓላ ከተማ ተገናኝተዋል።
ለግማሽ ቀን በተካሄደው የሁለቱ ክልል አጎራባች ዞኖች አመራሮች ግንኙነት ፦
- የሁለቱም ክልል ህዝቦች የፊት ለፊት ግንኙነት እንዲጀመር፤
- የተከለከሉ መንገዶች ተከፈትው ነፃ የህዝቦች ግንኙነት እንዲቀጥል፤
- ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ክልል ህዝቦች የሰላም እና የልማት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡
- ሁለቱም ክልሎች ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ፤
- ሁለቱም ክልሎች የሰላምና የፀጥታ እቅድ በማውጣት በየወሩ እየገመገሙ እንዲጓዙ፤
ተወያይተው መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ግንኙነቱ በማስመልከት አስተያየት የሰጡት የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላምና ልማት መሰረት እንዲይዝ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የላቀ ዝግጁነት አለው " ብሏል።
በያዝነው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ዓፋር ሰመራ ድረስ በመጓዝ ከርእሰ መስተዳደር ሃጂ ኣወል ኣርባ ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማካሄዳቸው መዘገባችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
Photo Credit - Tigrai Television
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
ይሄኔ እኮ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህን አልሰሙም ፤ 5% ተመላሽ አለን ፤ መቼ ? የሃገር ዉስጥ በረራችንን በM-PESA ስናደርግ ! ይህን አጋጣሚማ እፍስ ነው እንጂ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether
#Awash🚨
ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።
አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።
ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም ከነዋሪዎች የሚመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።
እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር።
በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።
ዝርዝር መረጃ ከባለሞያዎችን እንደሰማን የምናቀርብ ይሆናል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#ቦትስዋና👏
ከሰሞኑን በቦትስዋና በተካሄደው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን ያመኑት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዜዳንት ዱማ ቦኮ በይፋ በሰላም ፤ አቅፈዋቸውን ስልጣናቸውን አስረክበዋል።
ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ' የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ' ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ከባድ ሽንፈት አስተናግዶ መሪነቱን ተነጥቋል።
ይህ ፓርቲ አፍሪካ ውስጥ ረጅም ዓመታትን በግዢነት የቆየ ነው።
ተቃዋሚ ፓርቲ የነበረው ' አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ' በከፍተኛ ብልጫ በማሸነፍ ፕሬዜዳንታዊ ስልጣኑን ተቆጣጥሯል።
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት በምርጫ መሸነፋቸውን ካመኑ በኃላ መላው ህዝብ በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።
#ዴሞክራሲ #ምርጫ
@tikvahethiopia
#አሜሪካ
አሜሪካውያን ነገ ፕሬዝዳንታቸውን ይመርጣሉ።
በዴሞክራቷ ተወካይ ካማላ ሃሪስ እና በሪፐብሊካኑ ተወካይ ዶናልድ ትራምፕ መካከል እጅግ ብርቱ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 " Ethiopia land of origins " የሚል ስያሜ የተሰጠውን የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ከኤር ባስ የአውሮፕላን ኩባንያ ተረክቧል።
አውሮፕላኑ ከፈረንሣይ ቱሉስ ተነስቶ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ጥቅምት 26/ 2017 ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚያርፍ ይጠበቃል።
Photo Credit - ENA
@tikvahethiopia
የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።
ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et
➡️ በቴሌግራም : /channel/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።
@tikvahethiopia
#NBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ እንዳነሳ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።
ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።
የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል ተብሏል።
መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።
የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ፥ የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎችና በመሰራጨት ላይ የሚገኝ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ከላይ ተያዟል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከነዳጅ ጋር በተያያዘ የተገልጋችን እንግልት ለመቀነስ ሲባል በየዕለቱ ነዳጅ ያለባቸውን ማደያዎች ይፋ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል።
ዛሬ በአንዳንድ ማደያዎች ረዘም ያለ ሰልፍ መኖሩን ተዘዋውረን ለማየት ችለናል።
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
ስለ ብርሃን ስኩልፔይ (school pay) በጥቂቱ፤
#ለወላጆች ወይም #ለተማሪዎች የትኛውም ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም የትምህርት ክፍያዎችን መክፈል፤ የክፍያ ማረጋገጫዎችን፤ የክፍያ ሪፖርቶችን እና ተያያዥ መረጃዎችን በእጅዎ ባለው ስልክዎ በቀላሉ ማግኘት ያስችልዎታል፡፡
#ለትምህርት_ቤቶች ደግሞ ክፍያ ሲፈጸም ደረሰኝ ይዞ መሄድ ሳያስፈልግ ት/ቤቱ ሁሉንም ክፍያዎች በስኩልፔይ ሲስተም ማየት እና በቀላሉ መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ሙሉ የሆነ የተማሪዎችን መረጃ በመያዝ ምቹ አሰራርን ይፈጥራል፡፡
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
" ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ ተረጋግቶ ሊቀርም ወይም ወደ መሬት ላይ ሊፈስም ይችላል። ይህንን በሂደት የምናየው ነው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር)
በአፋር ክልል፣ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።
አደጋው ትላንት ምሽት ከለሊቱ 6:04 ላይ በዚሁ አካበቢ የተከተሰተ ሲሆን፣ ንዝረቱም አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱ ታውቋል።
ስለትላንቱ ርእደ መሬትና መንስኤው ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትን ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር)ን ጠይቀናል።
እሳቸውም፣ " የየቀን ተግባራችንን እያከናወንን ክስተቱ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በንቃት ሁኔታወን ቢከታተሉ ጥሩ ነው " ብለዋል።
በዝርዝር ምን አሉ ?
" ይሄ በአሁኑ ወቅት በፈንታሌ አካባቢ እየተከሰተ ያለው ርዕደ መሬት፤ ቅልጥ አለት (ማግማ) መሬት ውስጥ ከሚያደርገው እንቅስቃሴዎችና ተዛማጅ ሁኔታዎች ጋር የተገናኘ እንደሆነ ቀደም ሲልም አስታውቀናል።
ቅልጥ አለቱ መሬት ውስጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የቀነሰ ቢመስልም አልተቋረጠም።
እዚህ ሰሞኑን ከሚሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተያይዞ ፤ በወፍ በረር 130 ኪ.ሜ ላይ የሚገኘው ፈንታሌ አካባቢ እየተከሰተ ያለው የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ግን ወዴት እንደሚያመራ አናውቅም።
ይህ ቅልጥ አለት በመሬት ውስጥ ተረጋግቶ ሊቀርም ወይም ወደ መሬት ላይ ሊፈስ ይችላል። ይህንን በሂደት የምናየው ነው።
ተቋማችን ባለው አቅም እንዲሁም በሀገር ውስጥና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ አብረውን ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር ግንኙነቶችን በማድረግ ሳይንስ የደረሰበት የእውቀት ደረጃን በሙሉ ለመተግበር የሚገባውን በማድረግ ላይ እንገኛለን።
የእኛ ተቋም የምርምር ተቋም በመሆኑ የሚያከናውነው ይህ ርዕደ መሬት የት ተከሰተ? መጠኑ ስንት ነው? መንስኤው ምንድነው ? የቅልጥ ዓለቱስ እንቅስቃሴ ወዴት ሊያመራ ይችላል ? እና የመሳሰሉ ሃሳቦች ላይ መመራመር ሲሆን፤ ይህንን የምርምር ውጤትም ግብአት አድርገው ባለድርሻ አካላት ከዚህ በኋል መሰራት ያለባቸውን ሥራዎች ይሰራሉ። "
ምናልባት የቴክኖሎጂ እጥረት ይኖር ይሆን ? አደጋውን መቆጣጠር የሚቻልበት የተለዬ ሁኔታስ የለም ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ኤልያስ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
" እየተከሰተ ያለውን ርእደ መሬትም ሆነ የቅልጥ አለት እንቅሰቃሴን ሂደት በቅርብ መከታተል የሚቻል ሲሆን፤ ማቆምም ሆነ መቆጣጠር ግን አይቻልም።
እኛ ብቻ አይደለንም በዓለም ላይ ያሉ ማናቸውም ባለሙያዎች መቆጣጠርና ማቆም አይችሉም። በፈንታሌ አካባቢ ያለውን ሁኔታ እኛ ብቻችን ሳይሆን፤ ሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ተባባሪ ባለሙያዎች ጋር በቅርብ ምክክር በማድረግ እየሰራን ነው።
የእኛ ዩኒቨርሲቲም ሆነ ኢንስቲትዩታችን በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችና ለዚህ ተግባር የሚያገለግሉ ዘመናዊ የሆኑ መሳሪያዎች ያሉት ቢሆንም፣ ዓለም የደረሰበት ሁሉም ዓይነት መሰሪያዎች ግን አሉን ማለት አይደለም።
ለምሳሌ የርቀት ዳሰሳ ወይም ሪሞት ሴንሲንግ የሳተላይት መረጃዎችን የሚያሰባስቡ ሳተላይቶች ስለሌሉን ከዓለም ዓቀፍ ማዕላት መረጃ በመቀበል፣ በመተንተንና ከተባባሪዎቻችን ጋር ሆነን በመቀመር እንሰራለን።
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች መረጃ እንዲያሰባስቡ የተከልናቸው የርእደ መሬትና የGNSS መረጃ ማጠናቀሪያ ጣቢያዎች በዓለም ላይ ደረጃቸውን የጠበቁ ሲሆኑ፤ ብዛታቸውን ግን አሁን ካለው በላይ ማስፋፋት ይጠበቃል።
ይህ ደግሞ መጠነ ሰፊ መዕዋለ ንዋይን ማፍሰስ ይፈልጋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ አሁን ከተጠቀምንበት ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ ስለሆነ ባለን ለመስራት እየተጋን ነው።
ምንም እንኳን ተጨማሪ ጣቢያዎች ያስፈልጉናል ቢባልም፣ ፈጣሪ ይመስገንና በዓለም ደረጃ ስመጥር በሆኑ ባለሙያዎቻችን የማያሰልስ ጥረትና ችሎታ ትክክለኛውን መረጃ ከማንም ባላነሰ መልኩ እያቀረብን እንገኛለን።
አሁን የሚጠበቀው ይህንን መረጃ ወስዶ በተቀናጀ መልኩ ምናልባት ሊፈጠር ከሚችል አደጋ ለመከላከል ዝግጁ መሆን ነው። እኛ የአንድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከል ነን። ከዚህ ውጭ ያለው ሥራ ግን የሌላ ብዙ ባለድርሻ አካላትን መቀናጀትን ይጠይቃል።
አሁን እያደረግን ካለው ውጭ የማድረግ ማንዴቱም የለንም ተልእኳችንም አይደለም። ይህም ሆኖ ግን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የሚቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው " ብለዋል።
አደጋውን በተመለከተ መደረግ ስላበት የጥንቃቄ ሥራ ባስተላለፉት መልዕክት ደግም፣ " እንዳንዘናጋ ! የእለት ከእለት ተግባራችንን እያከናወንን በንቃት ሂደቱን እንከታተል " ሲሉ አስገንዝበዋል።
" የስምጥ ሸለቆዎች ባሉበት ሀገር ስለሆነ የምንኖረው ክስተቱ በታየበት ሰሞን ብቻ ሳይሆን፣ አኗራራችን፣ ግንባታዎቻችን፣ አስተሳሰባችን፣ የትምህርት ካሪክለሞቻችን ባጠቃላይ ዝግጁነታችን በዚሁ የተቃኘ መሆን አለበት " ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update #Earthquake
በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።
ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።
@tikvahethiopia
" ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ያደረጉት የፊት ለፊት ግንኙነት ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት እንደሌለው ተናገረ።
የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ዛሬ ምሽት አጭር መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ፥ " በብፁአን አበው የተዘጋጀው ፊት ለፊት የማገናኘት መርሃ ግብር ልዩነቶች በህግ ፣ ተቋማዊ ስርዓት ማእከል በማድረግ ህዝብን ከአደጋ መታደግ በሚችል የሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችን እንድንፈታ ያለመ የምክርና የተግሳፅ መድረክ ነበር " ብሏል።
" መድረኩን ተከትሎ የተለያዩ ውዥንብሮች መፈጠራቸው ለመረዳት ችለናል " ያለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፥ "ብፁአን አበው ላቀረቡልን ምክርና ተግሳፅ ያለን ክብር እና ድጋፍ ገልፀናል ፤ ከዚህ በዘለለ የተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' በማለት የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " ሲል ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " - ቤተሰቦች
በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ የታገቱት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ የሕክምና አገልግሎት በመዘጋቱ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ነቀምት ሄደው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።
ታጋቾቹ አዳሙ ደስታ እና ውበቱ ሞላ የሚባሉ ሲሆኑ የምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።
በአካባቢው ህክምና ስለሌለ " ከመሞት ሕክምና ለመሞከር " ብለው ወደ ነቀምት ሄደው ሲመለሱ ነው ኮኮፌ አካባቢ ኤጄሬ የምትባል ከተማ ላይ ነው በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው የገለጹት።
እግታው በአካባቢው ታጥቆ በሚንቀሳቀሰው ' ሸኔ ' የተፈጸመ ነው ብለዋል።
ታጋቾች እንዲለቀቁ 300,000 ብር እንደተጠየቀ አመልክተዋል።
" ይህም ተከፍሎ ከተለቀቁ ነው " ሲሉ ቤተሰቦች በሃዘን ስሜት አስረድተዋል።
በቀጠናው ባለው የፀጥታ ችግር ላለፉት 4 አመታት የመንገድ ፣ የኤሌክትሪክ ፣የኔትወርክ ፣ የጤና፣ የትምህርት ችግር በመኖሩ ህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ ላይ ነው።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉ ተገልጿል።
1. መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ
ከመገናኛ - ቃሊቲ
ከመገናኛ - ሳሪስ
ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች
በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
2. ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው
ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ)
3. ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች
ከመገናኛ - ገርጂ
ከመገናኛ-ጎሮ
ከመገናኛ - አያት እና
ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ ተዘዋውሮ በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።
@tikvahethiopia
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው በርካታ ሽልማቶች ውስጥ የመጀመርያው ቮልስ ዋገን አይዲ4 (VW ID4) የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በሐዋሳ ከተማ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡
ዕድለኛው አሸናፊ አቶ ኤርሚያስ ብርሃኑ፣ ሽልማታቸውን ጥቅምት 23 ቀን 2017ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ኮተቤ 04 አካባቢ የቢዋይዲ ኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ለባለዕድለኛ መውጣቱ ይታወሳል፡፡
አሁንም በርካታ ሽልማቶች ተረኛ ዕድለኛቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ የፔፕሲን ምርቶች እያጣጣምን ዕድላችን እንሞክር - እናሸንፍ! ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕ ይጥማሉ - ያስሸልማሉ!
ንጉስ !
አፍ ላይ ቀለል ብሎ የሚጠጣ ፣ ልብን በደስታ የሚሞላ ፣ ልዩ ጣዕም!
ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ /channel/Negus_Malt
#ደስደስበንጉስ #nonalcoholic #ከአልኮልነፃ
#ቦትስዋና 👏 #ዴሞክራሲ
" ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " - ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ
በአህጉራችን አፍሪካ የተረጋጋ የዲሞክራሲ ስርዓት ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደሟ ቦትስዋና ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች።
በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ለ58 ዓመታት ስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዢ ፓርቲ ድምጻቸውን ነፍገውታል።
ፓርቲው አስደንጋጭ ነው የተባለ ሽንፈትን ተከናንቧል።
የፓርቲው መሪና የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል።
ምንም እንኳን እስካሁን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ሽንፈትን አስተናግዷል።
ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ ከፍተኛ ድምጽ አግኝቷል።
የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ቦትስዋና ፕሬዝደንት ለመሆን ተቃርበዋል።
ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለተቀናቃኛቸው ቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን ነግረዋቸዋል።
" በዲሞክራሲ ሂደቱ እጅግ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " ብለዋል ፕሬዜዳንት ማሲሲ።
ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ማሲሲ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ሂደት ደስ እንደተሰኙ ገልጸው " የህዝቡን ፍላጎት እና ምርጫ አከብራለሁ " ብለዋል።
ደጋፊዎቻቸውን ረጋ እንዳሉ በእርጋታቸው እንዲቀጥሉና ከአዲሱ የሀገሪቱ መንግስት ጀርባ ተሰልፈው እንዲደግፉ በይፋ ጥሪ አቅርበዋል።
ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደም ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ ማግኘቱን ይገልጻል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia