የ12ኛ ክፍል ውጤት እንዴት ማየት ይቻላል ?
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።
ውጤት እንዴት ማየት እንደሚቻል በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል።
እኛም ተፈታኞች እንዴት ነው ውጤታቸውን ማየት የሚችሉት ? ስንል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡
" ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይን የሚያዩበትን አማራጭ አድራሻዎች ማምሻውን አገልገሎቱ ይፋ ያደርጋል " ሲሉ ከፍተኛ አመራሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት በድረ-ገፅ፣ በአጭር የፅሑፍ መልዕክት እና በቴሌግራም ቦት ይፋ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል።
አገልግሎቱ አማራጭ አድራሻዎቹን ይፋ እንዳደረገ ወደናንተ እናደርሳለን።
Via @tikvahuniversity
#ውጤት
የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #1
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል።
የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል።
ይጠብቁ !
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#Update
ፍ/ቤት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ።
" የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ፤ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል " ተብለው የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱ ተሰማ።
የፌደራል መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ቡድን፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ማጣሪያ ስራ አጠናቆ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።
የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በችሎት ተሰይሞ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም መረከቡን ጠቅሶ፤ ማስረጃ ተመልክቶ ክስ ለማቅረብ እንዲያስችለው ክስ ለመመስረቻ ጊዜ 5 ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል።
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች " ዐቃቤ ህግ ምርመራውን ሲመራ ቆይቶ እንደአዲስ መዝገቡን ተመልክቼ ክስ ለመመስረት፣ ለመወሰን እንዲያስችለኝ የክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ " ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
ጠበቆቻቸው ደንበኞቻቸው ተጨማሪ ጊዜ በእስር ሊቆዩ እንደማይገባ ገልጸው፤ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።
የግራ ቀኝ ክርክሩን የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መፍቀድ ስነ ስርዓታዊ መሆኑን በማመን የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለዐቃቤ ህግ የ5 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
በዚህም መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ/ም ክስ ይመሰረታል።
@tikvahethiopia
#ጠለምት🚨
“ ናዳው ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 25 ነው ” - ወረዳው
የመሬት መንሸራተት አደጋው መቀጠሉ የተነገረለት ሰሜን ጎንደር ዞን በተለይ ጠለምት ወረዳ የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የተከተው ይሄው አደጋ የብዙዎችን ሕይወት መቀጠፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይ በጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ከመሬት መንሸራተቱ በተጨማሪ በሌሎች ቀበሌዎችም “ የህድሞ ” ቤት ናዳ አደጋ መከሰቱን ወረዳው ከሳምንት በፊት ገልጾልን ነበር፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ፣ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ደግሞ የሟቾች ቁጥር በ15 መጨመሩን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
“ ናዳው ቀጥሏል፡፡ በጠለምት ወረዳ የሟቾች ቁጠር 25 ደርሷል ” ነው ያሉት፡፡
አስተዳዳሪው በዝርዝር ምን አሉ ?
“ በወረዳው በሚገኙ ቀበሌዎች በናዳና የጎርፍ አደጋ ምክንያት በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡
ከነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ብቻ አራት ወንዶች፣ 11 ሴቶች በአጠቃላይ 15 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡
ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በድምሩ አራት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 29 ቀን ድረስ በአጠቃላይ በወረዳው የሞቱ ሰዎች ብዛት 25 ደርሷል፡፡
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ብዛት ደግሞ 10 ደርሷል፡፡ 456 ሰዎች የእርሻ መሬት ተጎድቶባቸዋል፡፡ 476.5 ሄክታር ሰብል ተጎድቷል፡፡
2911 እንስሳት ሞተዋል፡፡ 28 መኖሪያ ቤቶችና 236 የንብ ቀፎዎች ወድመዋል” ብለዋል፡፡
የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ድጋፎችን እንዳደረጉ የገለጸው ወረዳው፣ አደጋውና መፈናቀሉ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመሆኑ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል፡፡
አደጋው የተከሰተው በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ሲሆን፣ በተለይም ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት መቆም እንዳልቻለ መገለጹ ይታወሳል፡፡
በዞኑ በሚገኙ ሌሎች ወረዳዎች አደጋው በምን ደረጃ እንደሚገኝ በቀጣይ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡
ፎቶ ፦ ፋይል
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።
የፕሮፌሰር እንድሪያስ የቀብር ሥነሥርዓት የተፈፀመው በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነው።
በቀብር ሥነሥርዓቱ ላይም ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ የሀይማኖት አባቶች የፕሮፌሰር እንድርያስ ወዳጅ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ከቀብር ሥነሥርዓቱ አስቀድሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፊት ለፊት በተጣለ ድንኳን የሽኝት ሥነሥርዓት ተካሄዷል።
በዚያ የስንብት ዝግጅት ላይ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የክልል ፕሬዚዳንቶች ፣የፕሮፌሰር እንድሪያስ ወዳጆችና ቤተሰቦች ተገኝተው እንደነበር ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
ፕሮፌሰሩ በመምህርነታቸው ፣ በፍልስፍናቸው ይታወቁ ነበር።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ሆነው ለ9 ዓመታት አገግለዋል። የየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አማካሪም ሆነው ሰርተዋል።
በተወለዱ 79 ዓመታቸው ነሀሴ 23/2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ የአሉላ አንድሪያስ ወላጅ አባት ናቸው።
Photo Credit : Sheger FM, Abel G/Egziabeher, Addis Admas Newspaper
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
🌼 አዲስ ዓመት ደስ ይላል… እንደ አዲስ እናቅዳለን ፣ እናልማለን 🌼
የስራ ውጣ ውረዱን ፣ የኑሮ አባጣ ጎርባጣውን ፣ ደስታና ሐዘኑን ስናስተውል… በየቀኑ የምንተውነው ድራማ አጃኢብ ያስብላል… እንዲያውም የእያንዳንዳችን ሕይወት ቢፃፍ ምርጥ ፊልም ይወጣዋል!
ሕይወት ፊልም ናት!
ድራማውን በአቦል እዩት! በወር በ350 ብር ብቻ!
መልካም አዲስ ዓመት!
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው
" የመመዝገቢያ ቀናት ከጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ ነው " - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
አንጋፋዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ /ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ለመቀበል መዘጋጀቱን አሳውቆናል።
ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ገልጾልናል።
ከማክሰኞ ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም የመመዝገቢያ ቀናት እንደሆኑ ይፋ አድርጓል።
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ወደፊት በራሱ በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ ይገለጸል።
www.aau.edu.et
@tikvahethiopia
#MoE
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።
የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
" የተፈጠረው ልዩነት ያለ ግጭት እንዲፈታ እንሰራለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ያሉት ልዩነቶች ያለ ግጭት እንዲፈቱ እንሰራለን " ብለዋል።
ይህን ያሉት ዛሬ ማይጨው ከተማ ህዝባዊ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
አቶ ጌታቸው የሚመሩትና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የከፍተኛ አመራሮች ቡድን ከሰሞኑን በትግራይ እየተንቀሳቀሰ ህዝባዊ ውይይት እያደረገ ነው።
ከቀናት በፊትም በዓዲግራት ውይይት አድርጎ ነበር።
ዛሬ ደግሞ በማይጨው ከተማ ህዝባዊ ውይይት አድርጓል።
አመራሮቹ ወደ ማይጨው ባደረጉት ጉዞ በየመንገዱ ህዝቡ እየወጣ ተቀብሏቸዋል ፤ ማይጨው ላይም ከፍተኛ የሰው ቁጥር በአጀብ ተቀብሏቸዋል።
ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተው ነበር።
ነዋሪዎች ምን አሉ ?
- በአመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ህዝቡን ይከፋፍላል ስለዚህ በአስቸኳይ መቆም አለበት።
- በአመራሮች መካከል የተፈጠረው እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቀል ዓይነት አካሄድ ይቁም።
- በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ ፤ የተመለሱት ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸው።
- አመራሮች ሰላም ቀዳሚ የህዝብ ምርጫ መሆኑ ሊረዱና ሊያስቀጥሉ ይገባል።
- በዲፕሎማሲ እንጂ በአፈሙዝ አይመራም።
- የትግራይ ሉግዛት የማስከበር ጉዳይ ችላ መባል የለበትም።
- የሚታዩ የፀጥታ ስጋቶች የሚቀርፍ ቀጣይ ስራ ይሰራ።
- ፍትህ እየተጓደለ ነው ፤ በፍርድ ቤቶች ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ይሰራል።
- በሴቶች የሚደርሰው ጥቃት ይቁም።
- የሰማእታት ቤተሰቦች ትኩረት ይደረግላቸው።
- አቅም ያላቸው ሰዎች ወደ አመራር ይወጡ። - ተጀምረው የተቋረጡ መሰረተ ልማቶች ይቀጥሉ።
- ህገወጥ የወጣቶች ፍልሰት የሚከላከል መንግስታዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ተግባራዊ ይሁን።
- ከአግባብ ውጭ በሙስናና ህገ-ወጥ መንገድ ለኢንቨስትመንት ማስፋፍያ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ይቁም ... ሲሉ አሳስበዋል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ የህወሓት ህጋዊነት ለህዝብ በሚመጥንና የፕሪቶሪያ ውል በሚያስከብር መልኩ ለመመለስ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
እርሳቸው በሚመሩትና በዶ/ር ደብረፀዮን በሚመራው ህወሓት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ያለ ግጭት እንዲፈታ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
" ከዚህ ውጭ የፕሪቶሪያ ውል ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ጦርነትን መጥራት መሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
" የተፈጠረው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ከማድረግ ጎን ለጎን ተፈናቃዮች በአጭር ጊዜ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እናደርጋለን " ሲሉ አክለዋል።
ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ
@tikvahethiopia
#NGAT
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለፈተና ማዕከልነት የመረጡ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) ፈተናውን ለመውሰድ ያመለከቱ በሙሉ፣ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡
Via @tikvahuniversity
#EthiopianAirlines
ወደ አስመራ የሚያደርገው በረራ ከነገ ጀምሮ ይቋረጣል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ በረራውን የሚያቋርጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር እንደሆነ ገልጿል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።
" የትኬት ገንዘብ ይመለስልን " የሚሉ ካሉም ለቲኬታቸው ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደረግ ገልጿል።
በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።
@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹
" #ኢትዮጵያ ሶማሊያ እንደ አገር ትቆም ዘንድ ብዙ መስዋዕትነትን ከፍላለች፡፡ ብዙ ሺሕ የሚቆጣጠሩ ወንዶችና ሴቶች መስዕዋት አድርገናል ገብረናል፡፡
የቆጠብነው ነገር የለም ሕይወት ሰጥተናል፣ ደም ሰጥተናል፣ ላብ ሰጥተናል፣ ጉልበት ሰጥተናል፡፡ ነገር ግን በሶማሊያ በኩል ይህንን አስተዋጽኦ ከቁብ ላለመቁጠርና ውለታ ለማስቀረት የሚደረግ መግለጫ መስማት እንደ ኢትዮጵያዊ ይኮሰኩሳል።
እንደ አፍሪካዊና ሰላም ወዳድ እንደሆነው የሶማሊያ ሕዝብ ደግሞ ያማል።
በሶማሊያ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያደረገውን ተጋድሎ በማንኳሰስ፣ የወሬያቸውና የንግግራቸው ሁሉ ማዋዣ ብቻ ሳይሆን ማዕከል እያደረጉት ነው ፤ ይህ ነውር ነው !!
ኢትዮጵያ ለዘመናት ያደረገችውን አስተዋጽኦ እና የከፈለችውን ዋጋ በማጣጣል፣ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚፃረሩ ኃይሎችን ሶማሊያ መጋበዟን ልታቆም ይገባል።
ኢትዮጵያ የደኅንነት ሥጋት የሚፈጥርባትን አካል ዝም ብላ አትመለከትም። " - አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)
#Ethiopia #Reporter
@tikvahethiopia
#AddisAbaba #ባጃጅ
በአዲስ አበባ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት በሂደት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ አይቀሬ እንደሆነ ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ የባለሶስት እና አራት እግር ተሽከርካሪ ወይም ባጃጅ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የአሰራር ፣ የአጀረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የዲሲፒሊን ቁጥጥር አፈጻጸም መመሪያ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጎ ነበር።
በውይይቱ ላይ ፦
- የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
- የትራፊክ ማናጅመንት ፣
- የትራንስፖርት ቢሮ
- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማዕከልና የክ/ከተሞች ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
በአፈፃፀም መመሪያው የባለ ሶስትና አራት እግር ተሽከርካሪ ወይም ባጃጅ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ካሁን ቀደም ሲያጋጥሙ የነበሩ የሕግ ጥሰቶችንና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል ሲባል አገልግሎት ሰጪዎቹ ፦
☑ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ፣
☑ የአዲስ አበባ የሠሌዳ ቁጥር
☑ በማህበር መደራጀት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል።
" በአዲስ አበባ፣ የከተማ አስተዳደሩን ታርጋ ለጥፈውና የአዲስ አበባ መታወቂያ ይዘው ከሚሰሩት ይልቅ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ አሽከርካሪዎች መበራከት የፀጥታ ችግር ሆነው ቆይተዋል " ተብሏል።
ይህ ደግሞ በተለይ በወንጀል ድርጊት ላይ ተሳትፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ አዳጋች እንደነበር ተገልጿል።
በዚሁ መድረክ ላይ " የባጃጅ ትራንስፖርት የከተማዋን ዘመናዊ እሳቤ የሚመጥን ስላልሆነ በሂደት ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ የሚቋረጥ ይሆናል " ተብሏል።
" እስከዚያ ጊዜ ድረስ የባለሶስት እግር አሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ መታወቂያ፣ ታርጋ እና በማህበር መደራጀት ይኖርባቸዋል " ነው የተባለው።
አሁን ላይ በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ሰፊ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት በመኖሩ በነዚህ አካባቢ ያለው ፍላጎት በሌላ አማራጮች እስኪተካ ድረስ አገልግሎቱ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉባቸው እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ሰፈሮች ዜጎች ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን / ባጃጅ ለትራንስፖርት ይጠቀማሉ።
እጅግ በርካታ ዜጎችም በተለይ በተለይ ወጣቶች በዚሁ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ገቢ ያገኛሉ ቤተሰባቸውንም ያስተዳድራሉ።
ከዚህ ቀደም ባጃጆች በተለይ በከተማው ዳርዳር ከዋና ዋና የሚባሉ መንገዶች ወጥተው ውስጥ ለውስጥ ብቻ እንዲሰሩ መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።
#AddisAbaba
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
❤️
ከአሜሪካ ሃገር በመጡ ሐኪሞች የልብ ሕክምና ተልዕኮ (Mission) አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የልብ ማዕከል-ኢትዮጵያ ውስጥ " ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ' በተሰኘ በአሜሪካን ሃገር በሚገኝ በዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶ/ር ኦብሲኔት መርዕድ የተመሰረተ የግብረ ሰናይ ድርጅት የነጻ የልብ ሕክምና ተልዕኮ አገልግሎት ከነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እየሰጠ ነው።
ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የሕክምና ተልዕኮ መርሐግብር ነው።
የሕክምና አገልግሎቱ ከማዕከሉ በተጨማሪም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ100 በላይ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ታካሚዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያቀደ ነው።
የሕክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከ17 በላይ የልብ ሕክምና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የጤና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ነው።
ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኦብሲኔት ፥ " በዚህ ዙር ደረት ሳይከፈት ከሚሰሩ ሕክምናዎች በተጨማሪ የልብ ቀዶ ሕክምና እና የልብ ምት ችግር ላለባቸው ሕሙማን የሚሰጡ ሕክምናዎች ተካተዋል " ብለዋል።
ድርጅቱ ለሕክምና ተልዕኮው ከ1.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሰባስቦ ነው ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነው የጠቆሙት።
ወደፊት ተጨማሪ ተልዕኮዎችን እንደሚያካሂድ አመልክተዋል።
የልብ ማዕከል ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኅሩይ ዓሊ ፥ " በዚህ የሕክምና ተልዕኮ ላይ በርካታ ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሕሙማን ተጠቃሚ ናቸው። " ያሉ ሲሆን " ተልዕኮው ስኬታማ እንዲሆን ማዕከሉ ከዝግጅት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ ሥራዎችን ሲሰራ ነበር ቆይቷል " ነው ያሉት።
#Ethiopia
@tikvahethiopia @thechfe
👆የቀጠለ
የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Oromia : በመሬት ናዳ የሦስት እህትማማቾች ሕይወት አለፈ።
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የነበሩ 3 እህትማማቾች መሞታቸውን የዞኑ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ኑራ መሐመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ህይወት የጠፋው በአንድ አባወራ መኖሪያ ቤት አፈር ተደርምሶ ነው።
የእናት እና አባት ህይወት ሲተርፍ ሶስቱ ልጆቻቸው ሞተዋል።
አደጋው የተከሰተው ጷጉሜ 2 ሌሊት ስምንት ሰዓት ላይ ሲሆን አስክሬናቸውን የአካባቢው ማህበረሰብ በነጋታው በማውጣት የቀብር ስነ ስርዓታቸው እንዲፈጸም መደረጉን የዞኑ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት ገልጾልናል።
አደጋው በተከሰተባቸው አኮ ጅሩ፣ኢሉ ኩታዬ እና ኡነይ ቀበሌዎች ከሰው ህይወት ህልፈት በተጨማሪ በሰብል የተሸፈነ 20 ሄክታር ማሳ መውደሙ ተነግሯል።
በተጨማሪም ከጅማ ሆሮ ወደ ጊዳሚ የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተቱ መዘጋቱን እና ለማስከፈት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ሃላፊው አክለዋል።
ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ ተጨማሪ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ 10 ቤቶች ላይ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማንሳት ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍሩ እየተሰራ ነው ተብሏል።
Via @tikvahethmagazine
#Tigray
ባጋጠመ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከ10 በላይ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ተቀጠፈ።
የትራፊክ አደጋው ዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት አከባቢ የተከሰተ ሲሆን የሰሌዳ ቁጥር TG - 04539 የሆነ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከዓድዋ ወደ መቐለ ሲጓዝ ወርዒ ልዩ ቦታ እንዳፈላሲ ቁልቁለት ሲወርድ ወደ ገደል በመግባቱ ነው አደጋው ያጋጠመው።
በውስጥ ከተሳፈሩ ሰዎች ከ10 በላይ ወድያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ 5 ሰዎች በፅኑ ተጎድተዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመላክተው 48 ሰዎች የመጫን አቅም ያለው መለስተኛ አውቶቡስ በአጋጣሚ 20 ሰዎች ብቻ አሳፍሮ መጓዙ ለሟችና ቁስለኞች መቀነስ ምክንያት ሆኗል።
የአደጋው ምክንያት ገና በመጣራት ላይ ነው።
ይህ ወር በርካታ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ ይኖራል ፤ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አይለያችሁ።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia
ዘንድሮስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ?
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይገለጻል።
ትምህርት ሚኒስቴር በፈተናው ውጤት ዙሪያ ነገ ከሰዓት ማብራሪያ ይሰጣል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያውን ተከታትሎ ያቀርባል።
ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መረጃ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701,749 ተማሪዎች መካከል 684,205 ተማሪዎች ወይም 97.5 በመቶዎቹ ፈተናውን ወስደዋል።
ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶችና ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን አልወሰዱም።
ከተፈታኞቹ ውስጥ 29,718 የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የኦንላይን ፈተና አማካኝነት ፈተናቸውን የወሰዱ ናቸው።
የብሔራዊ ፈተናው ውስጤት ነገ ሰኞ ጳጉሜን 4/2016 ዓ/ም ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፉት ዓመታት በተለይም ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲ) አስገብቶ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት / በብዛት ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት የማያስመዘግቡበት መሆኑ ይታወቃል።
ለአብነት በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ 845,099 ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አምጥተው ማለፍ የቻሉት 27,267 / 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።
ከዛ በፊት በ2014ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው 50 በመቶና በላይ አምጥተው ያለፉት 30,034 / 3.3 በመቶ ብቻ ናቸው።
ትምህርት ሚኒስቴር በቀጥታ የሚያልፉ ተማሪዎች ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ የሬሜዲያል ፕሮግራም በመስጠት ያን ያለፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።
ይህ ስራ " ለአንድ ጊዜ ብቻ " ተብሎ የነበረ ሲሆን በ2015 ቀጥታ ያለፉ ተፈታኞች ውስን በመሆናቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ቃላቸውን ስላጠፉ በይፋ ይቅርታ ጠይቀው የሬሜዲያል ፕሮግራሙ እንዲቀጥል አድርገው ነበር።
° ዘንድሮውስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ?
° ምን ያህል ተማሪ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘግባል ?
ሁሉንም አብረን የምናየው ይሆናል።
ነገ ከሰዓት የፈተናው ውጤት በትምህርት ሚኒስቴር ይገለጻል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ ተከታትሎ ያደርሳችኋል።
#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#ትንሳኤ70እንደርታ
" የመቐለ ከተማ አስተዳደር የፈቀድልን ህዝባዊ ስብሰባ ተከለከልን " ሲል ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን አሰማ።
የፓርቲው ሊቀመንበር ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃል ፥ _ እሁድ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር ግቢ በሚገኘው አግኣዚ የስብሰባ አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቕዶልን አባልና ደጋፊዎቻችን ጠርተን ስናበቃ አዳራሽ እንዳንገባ በታጣቂዎች ተከልክለናል " ብለዋል።
" በህጋዊ መንገድ የተፈቀደ ህዝባዊ ውይይት መከልከልና ታዳሚዎች ማንገላታት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው " ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር በተግባሩ ማዘናቸው በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተናግረዋል።
" የመቐለ ከተማ ፀጥታ ፅ/ቤት በፃፈልን ደብዳቤ መሰረት ስብሰባውን የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ ፓሊስ መድቦ በቦታው የተገኙ ሲሆን ማንነታቸውና ተጠሪነታቸው የማይታወቁ ሌሎች ሃይሎች ተሳብሳቢው ወደ ግቢ እንዳናሰግባ የአዳራሹ ሰራተኞች ሳይቀር እንዳይገቡ በር ላይ ለነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት ስብሰባው ሳይደረግ ቀርተዋል " ሲሉ አስረድተዋል።
" እንደምክንያት ያቀረቡትም የከንቲባ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ለጋስ ማርያም ' እኔ ካልደወልኩኝ እንዳይገቡ ብለዋል ' የሚል ሲሆን ግለሰብዋ በደብዳቤ የፈቀዱትን ስብሰባ በዚህ መንገድ የከለከሉበት ምክንያት ለመጠየቅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸውን በመዝጋታቸው ምክንያት ልናገኛቸው አልቻልንም " በማለት ገልጸዋል።
የመቐለ ከተማ ፀጥታ ዘርፍና ፓሊስ መንግስታዊ ሃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት መሞከሩን አመልክተው " ምስጋና ይገባዋል " ብለዋል።
የመቐለ ከተማ አስተዳደርና ፓሊስ እስከ አሁን ሰዓት ስለ ክልከላው የሰጠው ይፋዊ ማብራርያም ሆነ መግለጫ የለም።
ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአንድ ዓመት በፊት ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ለማካሄድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ መመስረቱ ይታወቃል።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia
#KABBA_TRANSPORT🚌
Safety is our priority !
ካባ በት/ቤቶች ውስጥ የተማሪ ሰርቪስ አገልግሎትን ለሚሰጡ አካላት በስልጠና እና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ደህንነቱ የጠበቀ እና ቁጥጥር ያለው የተማሪዎች ትራንስፖርት ሰርቪስ አቅርቦት ለመፍጠር ከት/ቤቶች፣ወላጅ ኮሚቴ እና ወላጆች ጋር መስራት ይፈልጋል፡፡
አብረውን ሁለት አመታት የሰሩ ት/ቤቶች ምስክር ናቸው፡፡
የትምህርት ዘመን ከመከፈቱ በፊት ቀጠሮ ያስይዙ 0960009900 አዲስ ተመዝጋቢ ወላጆች መተግበሪያውን በማውረድ ይመዝገቡ👇 https://linktr.ee/Kabbatransport
ስልክ ፡ +2519 60 00 99 00
ካባ ትራንስፖርት
🔈 #የሰራተኞችድምጽ
" ክፍያችን ከኑሮ ውድነት አንጻር በጣም የወረደ በመሆኑ ህይወት አስቸጋሪ ሆኖብናል " - በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ሰራተኞች
" በ1000 ብር ደሞዝ ኑሮን መቋቋም አቃተን " ያሉ የሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ሰራተኞች የሚከፈለን ገንዘብ ከቤት ኪራይ የማያልፍ በመሆኑ በረሀብ እየተሰቃየን ነው በማለት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
የረከሰ ቤት ፍለጋ ከከተማ ወጣ ያሉ ሰፈሮች በመምረጥ ሶስት አራት ሆነዉ እንደሚከራዩና ጠዋት አንድ ሰአት ለመድረስ ከአስራ ሁለት ሰአት በፊት ተነስተዉ ያውም በባዶ ሆድና በእግር እንደሚመጡ የሚናገሩት ሰራተኞቹ " አሁን ግን ኑሮ ጣሪያ በመንካቱ በዚህ መልክ እንኳን መቀጠል አልቻልንም " ብለዋል።
" ምንም እንኳን የምሳ ድጋፍ ቢደረግልንም በአንድ ከተማ በአንድ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያለዉ ልዩነት ያሳዝናል " በማለት በፓርኩ ውስጥ እንኳን ልዩነት መኖሩን ይገልጻሉ።
አንዳንድ ሼዶች የትራንስፖርት አገልግሎትን ጨምሮ የትርፍ ሰአት ስራ የሚያመቻቹ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ ከአንድ ሽህ ብር ደሞዝ ውጭ ምንም ትርፍ ነገር አይሰጡም።
" በዚህም ኑሮን መግፋት ተራራ ሆኖብናል " በማለት ያሉበትን የስቃይ ህይወት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ሰራተኞቹ " በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አይደለም የቤት ኪራይ ከፍለንና የምግብ ወጭ ሸፍነን ለመኖር ይቅርና ሰርተዉ ይረዱናል ብለዉ በማሰብ ወደላኩን ቤተሰቦቻችን ለመመለስ እንኳን አስቸጋሪ ሆኖብናል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን የሰራተኞች እሮሮ ይዞ ምላሽ ለማግኘት የሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክን ደጋግሞ ቢያናንኳኳም ለጊዜዉ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
ይሁንና በቅርቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚው አቶ ዘመን ጁነዲን " የሰራተኛውን ምቹ ከባቢ መፍጠር የኛም ፕራይወሪቲ ነው " ብለው ነበር።
አሁን ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት በተለይም ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገርሩ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘመን ከክፍያ በተጨማሪ ትራንስፖርት ምግብና መሰል ድጎማዎች እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
#Tigray
አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል።
ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል።
ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ሳይካሄድ በመቅረቱ ይቅርታ ጠይቋል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ያጋጠማቸው የጤና እክል ቀላል ይሁን ከባድ በመግለጫው የተጠቀሰ የለም ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
ከሰሞኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የአመራሮች ቡድን በየከተማው ህዝባዊ ምክክር እያደረገ እንደነበር ይታወቃል።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia
#Telegram❤
የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቨል ድሮቭ ፓሪስ ውስጥ ታስሮ በዋስ ከተለቀቀ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ አስተያየት ሰጥቷል።
ዱሮቭ ምን አለ ?
አብረውት ለነበሩትና ለደገፉትና ፍቅራቸውን ላሳዩት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል።
ባለፈው ወር ፓሪስ በደረሰ ወቅት 4 ጊዜ በፖሊስ ኢንተርቪው ተደርጎ እንደነበር ገልጿል።
በዚህ ወቅት የፈረንሳይ ባለስልጣናት ከቴሌግራም ምላሾችን ስላላገኙ ምናልባትም ለሌሎች ሰዎች ህገወጥ የቴሌግራም አጠቃቀም በግል ዱሮቭ ተጠያቂ እንደሚሆን እንደተነገረው አመልክቷል።
ይህ ግን በብዙ ምክንያቶች አስገራሚ እንደነበር አስረድቷል።
- ቴሌግራም የአውሮፓ ህብረት ጥያቄዎችን የሚቀበል እና የሚመልስ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ኦፊሴላዊ ተወካይ አለው። ይፋዊ ኢሜልም አለው።
- የፈረንሳይ ባለስልጣናት እርዳታ ለመጠየቅ ዱሮቭን ለማግኘት ብዙ መንገዶች ነበሯቸው። እንደ አንድ የፈረንሳይ ዜጋ በዱባይ በሚገኘው የፈረንሳይ ቆንስላ ተደጋጋሚ እንግዳም ነበር። ከጥቂት ጊዜ በፊት ደግሞ በግሉ በፈረንሳይ ያለውን የሽብርተኝነት ስጋት ለማስወገድ ከቴሌግራም ጋር የስልክ መስመር እንዲፈጥሩ ረድቷቸዋል።
- አንድ ሀገር በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ደስተኛ ካልሆነ በራሱ በአገልግሎቱ ላይ ህጋዊ እርምጃ መጀመር ነው። ከቅድመ ስማርት ስልክ በፊት የነበረ ህግ አምጥቶ በመተግበሪያው ላይ በሶስተኛ ወገኖች ለሚሰራ ወንጀል የድርጅት ስራ አስፈጻሚን ተጠያቂ ማደረግ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም። ቴክኖሎጂን መገንባት በራሱ ከባድ ነገር ነው። ማንም ኢኖቬተር ሌሎች አላግባብ ለሚጠቀሙት አጠቃቀም እሱ በግሉ እንደሚጠየቅ ካወቀ አዲስ ነገር አይፈጥርም።
በግላዊ መረጃ እና በደህንነት መካከል ትክክለኛውን ሚዛን መፍጠር እንዲሁ ቀላል እንዳልሆነ ዱሮቭ ገልጿል።
አንዳንድ ጊዜ ይህን ሚዛን በመጠበቅ ጉዳይ ከሀገራት ተቆጣጣሪዎች ጋር መግባባት ሳይፈጠር ሲቀር ቴሌግራም ሀገራቱን ለቆ እንደሚወጣ አመልክቷል። ይህንን ብዙ ጊዜ እንዳደረገ ገልጿል።
ለአብነት ፦ ሩስያ ለስለላ " የኢንክሪፕሽን ቁልፎችን " መጠየቋን ተከክሎ ቴሌግራም አልሰጥም በማለቱ ሩስያ ውስጥ ቴሌግራም ታግዷል።
ኢራን የሰላማዊ ሰልፎችን ቻናሎች ብሎክ እንዲደረግላት ጠይቃ ቴሌግራም " አላደርገውም አይቻልም " በማለቱ ኢራን ውስጥ ታግዷል።
ዱሮቭ ምስራዎች የሚሰሩት ለገንዘብ ባለመሆነ ከቴሌግራም መርህ ጋር የማይሄድን ገበያ ለቆ ለመውጣት ሁሌም ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ሁሉ ማለት ግን ቴሌግራም ፍጹም ነው ማለት እንዳልሆነ ዱሮቭ አመልክቷል።
የመንግሥት አካላት / ባለስልጣናት ጥያቄያቸውን የት መላክ እንዳለባቸው ግራ ይግባሉ ይህንን ማስተካከል አለብን ብሏል።
ነገር ግን በአንዳንድ ሚዲያዎች ቴሌግራም የስርዓት አልበኞች መፈንጫ ተደርጎ የሚቀርበው ፍጹም ሀሰተኛ ነው ሲል ገልጿል።
" በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጎጂ ፖስቶችን እና ቻናሎችን እናስወግዳለን " ያለው ዱሮቭ በየዕለቱ ግልጽነት መፍጠሪያ ሪፖርቶችም እንልካለን ብሏል።
መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ጋር አስቸኳይ የሞደሬሽን ጥያቄዎችን በፍጥነት ለማስተናገድም የቀጥታ ስልክ መስመሮችም አሉን ሲል አክሏል።
" ሆኖም ግን ይህ በቂ አይደለም የሚሉ ድምፆችን እንሰማለን " ያለው ዱሮቭ " የተጠቃሚዎች ብዛት ወደ 950 ሚሊዮን መድረስ ወንጀለኞች የእኛን መድረክ አላግባብ ለመጠቀም ቀላል አድርጎላቸዋል። በዚህ ረገድ ያሉ ነገሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል የግል ግቤ አድርጊያለሁ " ብሏል።
ይህ ሂደት በውስጥ በኩል መጀመሩን ጠቁሞ በቀጣይ ስላለው ሁኔታ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ አሳውቋል።
ያለፈው ወር ክስተት ቴሌግራም እና የማህበራዊ አውታረመረብ ኢንዱስትሪን በጠቅላላ ደህንነቱ የተጠበቀና ጠንካራ እንደሚያደርገው ተስፋ እንዳለው ዱሮቭ ገልጿል።
#TikvahEthiopia
#Telegram
@tikvahethiopia
መታወቂያ መስጠት መቼ ይጀመራል ?
" አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል " - CRRSA
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክልል ከተሞች መሸኛ ለሚያመጡ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት መቼ እንደሚጀምር ጠይቀነው የሰጠንን ምላሽ በተደጋጋሚ አድርሰናችሁ ነበር።
ኤጀንሲውን ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ መቼ ይጀመራል ? ብለን ጠይቀን በሰጠን ምላሽ፣ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጾ ነበር።
ከቆይታ በኋላ ላቀረብንለት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀሰጠው ምላሽ፣ " የትምህርት ቤት ምዝገባ ሲጠናቀቅ አገልግሎቱን መስጠት እንጀምራለን " ነበር ያለው።
የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ መቼ መሰጠት እንደሚጀመር በወቅቱ ስንጠይቅም፤ ከነሐሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም በኋላ እንደሚሰጥ መግለጹ አይዘነጋም።
አሁንስ አገልግሎቱ መሰጠት ተጀመረ ?
አሁንስ አገልግሎቱን መስጠት ተጀምሯል ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የኤጀንሲው አካል፣ " ገና ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ የሚጀመር ይመስለኛል፡፡ ግን ገና ነው " ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ አገልግሎቱን እንደምትሰጡ ገልጻችሁ ነበር ብለን አስታውናቸዋል።
እኝሁ አካልም፣ " አዎ። አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል፡፡ ገና መስጠት አልተጀመረም " ነው ያሉት።
አሁንስ መቼ መሰጠት ይጀምራል ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ፣ እሳቸው ትክክለኛ ቀኑን እንደማያውቁት አስረድተዋል።
አክለውም፣ " መቼ ቀን እንደሚጀመር እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በቅርብ ጊዜ ሊጀምር እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#BRICS+
የNATO አባል ሀገሯ ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።
ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን በይፋ ማመልከቻ ማቅረቧን የቱርክ ገዥ ፓርቲ ቃል አቀባይ ኦመር ሴሊክ አረጋግጠዋል።
ቃል አቀባዩ " ፕሬዝደንታችን የBRICS አባል መሆን እንደምንፈልግ ደጋግመው ተናግረዋል። ጉዳዩ በሂደት ላይ ነው " ብለዋል።
" በአባልነት ሂደት ላይ ያለውን እምርታ ለህዝብ እናሳውቃለን " ሲሉም ተናግረዋል።
ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም የBRICS+ ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።
ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።
#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#AAU
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን አስተዋወቀ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫው ተከታትሏል።
ዩኒቨርስቲው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል በዚሁ መግለጫ አስታውቋል።
የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕረዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፥ ራስ-ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ የተቋቋመው ዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ነጻነት፤ አስተዳዳሪዊ ነጻነት፤ የፋይናንስ ነጻነት እና አካዳሚክ ነጻነት ማግኘቱን ገልጸዋል።
" ይህም መምህራኑን ሆነ ተማሪዎችን የመምረጥ መብት ይሰጠዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
አዲስ ይተገበራል በተባለው የቅበላ አሰራር በ2014፤ 2015 እና 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የሚወጣውን መስፈርት ታሳቢ አድርገው በዩኒቨርሲቲው ፖርታል https://portal.aau.edu.et መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።
መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው ?
ዶ/ር ሳሙኤል ፥ አንዱ መስፈርት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 50 በመቶ በላይ ማምጣት እንደሆነ ገልጸዋል።
ይህ ግን የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ 60 ወይም 70 በመቶ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል።
በመቀጠልም ዩኒቨርስቲው በራሱ የሚያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና (Undergraduate Admission Test) የሚኖረው ሲሆን ይህንን ፈተና ማለፍም ሌላው ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠው መስፈርት ነው ብለዋል።
ፈተናው ምን መልክ ይኖረዋል ?
በዩኒቨርስቲው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚቀርበው የፈተና ይዘት ምን መልክ አለው በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ሳሙኤል ፈተናው የአፕቲቲውድ (Apptitude) መልክ የሚኖረው እንደሆነ ጠቅሰው የተማሪዎችን የቋንቋ፤ የማመዛዘን እንዲሁም የቀመር አቅማቸውን የሚለካ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ፈተናው ከሌሎች የመግቢያ ፈተና ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው እንደሚችል ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ሆኖም የሚወጣው ፈተና ሙሉ በሙሉ የዩኒቨርስቲው እንደሚሆን አስረድተዋል።
የክፍያ እና የስኮላር ሺፕ ሁኔታ በተመለከተ ምን ተባለ ?
በዩኒቨርስቲው ለመማር ጥያቄ የሚያቀርቡ ተማሪዎች በሁለት አይነት መንገድ እንደሚስተናገዱ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
አንደኛው መስፈርቱን አሟልተው እና ሙሉ ክፍያ ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ ሌላው መንግስት ስፖንሰር ሺፕ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ተማሪዎች ናቸው።
ይህን በተመለከተ የተቀመጠ ኮታ እንደሌለ የገለጹት ዶ/ር ሳሙኤል እንደ እቅዳቸው ግን 50 በመቶ በመንግስት 50 በመቶ በግል ወጪያቸው የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች ለመቀበል እንደሆነ ገልጸው ካልሆነም ቁጥሩ በተወሰነ መልኩ ልዩነት ሊኖረው እንደሚችልም ጠቁመዋል።
መንግስት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለሀገር በሚፈለጉ የስልጠና መስኮች ወጪን ጭምር በመሽፈን የሚያስተናግድበት ሥርዓት እንደሚኖር እና ለሴቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ከታዳጊ ክልል ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ተመላክቷል።
ተማሪዎች በሚያመለክቱበት ወቅት ብዙ ቅጾችን እንደሚሞሉ ፤ ስኮላርሺፕ የሚጠይቁ ተማሪዎች ከፍለው መማር እንደማይችሉ የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው እና የሚያስገቡት መረጃ ትክክለኛነቱ እንደሚጣራና ሐሰተኛ ሆኖ ከተገኘ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ጭምር አንስተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ዩኒቨርስቲው በተከታታይ እንደሚሰጥ አረጋግጧል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#MoE
" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " - ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ " ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ! " በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።
ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " ብለዋል ሚኒስትሩ።
" ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር " ገልፀዋል።
" የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል " ብለዋል።
Via @tikvahuniversity
#ዕለታዊ_ምንዛሬ
የዶላር ዋጋ ባለፉት ተከታታይ ቀናት ከነበረው ዛሬ ጭማሪ አሳይቷል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 7 ቀናት ጭማሪ ሳይታይ ወጥ ሊባል የሚችል የምንዛሬ ዋጋ ነበር።
በዛሬው ዕለት ዶላር መግዣው ወደ 105.4304 ከፍ ሲል መሸጫው ወደ 117.0277 ጨምሯል።
ፓውንድ መግዣው 132.5631 ፤ መሸጫው 147.8322 ገብቷል።
ዩሮ 116.7747 መግዣው ሲሆን 129.6199 መሸጫው ነው።
በግል ባንኮች አንዱ ዶላር መግዣው ከ104 ብር አንስቶ እስከ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።
(በተለያዩ የግል ባንኮች ያለው የምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Urgent🚨
በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጠለምት ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።
በርካቶችም ችግር ላይ ወድቀዋል፤ ተፈናቅለዋል።
ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል።
ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወረዳው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል።
የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ቃል ፦
“ አካባቢው ከዚህ ቀደም በድርቅ የተጠቃ ነው፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች ደግሞ ከ14, 400 በላይ እህል ያስፈልገናል።
የእርዳታ ምግብ ድጋፍ ፤ 480 ድንኳን / ሸራ ፣ እንደ ብረት ድስት፣ ሳፋ አይነት የቤት ቁሳቁሶች በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ ናቸው። ”
#TikvahEthiopiaFamyAA
@tikvahethiopia