Tassa Tassa Tassa 😭
በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾች ቀጥር ከ55 በላይ ደርሷል።
የአስከሬን ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል።
የመሬት ናዳ አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ነበር የደረሰው።
እስከ አሁን ከ55 በላይ አስከሬን ተገኝቷል።
የሟቾች ቁጥር አሁንም ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል።
ሌሊት የዘነበውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ ነው የመሬት ናዳው የደረሰው።
@tikvahethiopia
#WachemoUniversity
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ወራት ብቻ ለአንድ ሰው የ1 ሺህ 496 ቀን አበል / 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል የተከፈለበት ግቢ ነው።
የዚሁ ተቋም ፕሬዝዳንቱን እና ምክትል ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎቹ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
@tikvahethiopia
#CentralEthiopia
የ11 ዓመት እድሜ ያላትን የገዛ ልጁን የደፈረው አባት 16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።
ድርጊቱ የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል፣ በጉራጌ ዞን፣ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ነው።
ተከሳሽ ሙሂዲን ወራቄ ይባላል።
የግል ተበዳይ (ልጁ) ያለ እድሜዋ በአዲስ አበባ ከተማ በሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ ነበር።
በኃላም ፤ በቤተሰቡ መበተን ምክንያት በብቸኝነት የሚኖረዉን አባቷ ለመደገፍ ወደ ከዊሶ ወደ ተባለው መንደር ትመለሳለች።
ተከሳሽ ጋብቻ እየመሰረተ ሲፈታ ከሶስት ጊዜ በላይ ትዳር መስርቶ ፍቺ የፈፀመ ሲሆን የደረሱ ልጆቹንም ድሮ የልጅ ልጅ ለማየት በቅቷልም ነዉ የተባለዉ።
" አባቴን ትቼ የትም አልሄድም " ስትል ከወላጅ አባቷ መኖር የጀመረችዉ ታዳጊ በተደጋጋሚ በገዛ አባቷ ተደፍራለች።
አንድ ቀን በወላጅ አባቷ ጭካኔና የነዉረኝነት ባህሪ የደረሰባትን በደል ሁሉ ለወላጅ እናቷ ትናገራለች።
አንጀቷ የበገነው እናትም ወደ ወረዳዉ ሴቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት አቅንታ ሰዉየዉ ለፍርድ ይቀርብ ዘንድ እገዛ እንዲደረግልኝ ስትል አቤቱታ በማሰማቷ ክስ ሊመሰረት ችሏል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ በማለት በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
መረጃው ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው የተገኘው።
Via @tikvahethmagazine
#EAES
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ መሰጡቱን ገልጿል።
ዛሬ ፈተናቸውን ያጠናቀቁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ናቸው።
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል እየተሰጠ ያለው የመልቀቂያ ፈተና ነገ ከሰዓት በፊት ይጠናቀቃል።
@tikvahuniversity
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን
በአዲስ አበባ ከተማ ጥዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው።
ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ብሏል።
" ጥዋት ስራ መግቢያ እና ስራ መውጫ ሰዓት አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ይታያል " ያለው መ/ቤቱ " ይህንን ለመቀልበስ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥናት አስጠንቶ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የፍሰት ማሻሻያዎች አሉ " ብሏል።
ከነዛ ውስጥ አንዱ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበት እንደሆነ ገልጿል።
የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንና የሕግ ማዕቀፍም መዘጋጀቱን በጣም ከዘገየ ከ2 እስከ 3 ወር ወደ ተግባር እንደሚገባ አስረድቷል።
" ይሄ ፍሰቱን ያሻሽላል " ያለው መ/ቤቱ " ፒክ ሀወር / ስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር ተብሎ ፕሮግራም ወጥቶለት ለምሳሌ ዛሬ ሙሉ ቁጥር የሚንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ጎዶሎ ቁጥር በፈረቃ እንዲንቀሳቀስ የሕግ ማዕቀፍ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው " ሲል አሳውቋል።
የኦሮሚያ እና ፌዴራል ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺህ በላይ እንደሆኑ የተገለጸው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጥዋት እና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ብሏል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
#AddisAbaba #ኮድ2
@tikvahethiopia
ከሰማይ እንደመጣ የተነገረለት ' ድንጋይ ' ምንድነው ?
በኦሮሚያ ክልል፤ በጅማ ዞን፤ የቡ ከተማ በቅርቡ ከሰማይ እንደመጣ የተነገረለትን ድንጋይ በተመለከተ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት ማብራሪያ ሰጥቷል።
ማብራሪያው የሚከተለው ነው ፦
" አስትሮይድ (Asteroid) በህዋ ውስጥ የሚገኙ ድንጋያማ አካላት ናቸው፡፡
በዋነኛነት የስርዓተ ጸሐይ አካል በመሆን በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው ስፍራ የመቀነት ቅርጽ (Asteroid Belt) ፈጥረው ጸሐይን ይዞራሉ፡፡
እነዚህ የሰማይ አካላት ግዙፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹም በመቶ ኪሎሜትሮች የሚቆጠር ዲያሜትር ያላቸው ናቸው፡፡
በአንፃሩ ሜትሮይትስ (Meteorites) ወደ ምድር ከባቢ አየር የገቡ የአስትሮይዶች ወይም ኮሜት ቁርጥራጮች ናቸው።
በሌሊት ሰማይ ላይ የምናያቸው የብርሀን ጅራቶች ሜትሮይድ (Meteoroid)፣ ትንሽ የጠፈር አለት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገባና ሲቃጠል የሚፈጠር ነው።
የሜትዮር ሻወር (Meteor Shower) አስደናቂ የብርሃን ትዕይንት በሰማይ ላይ የሚፈጥሩ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ሜትሮይዶች ጥቃቅን እና መሬት ላይ ከመድረሳቸው በፊት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የሚጠፉ ናቸው።
በመጠን የገዘፉ እና ጠንካራ የሆኑት አለቶች ከእሳታማው መተላለፊያ እና የመሬት ከባቢ አየር ተርፈው መሬት ላይ ይደርሳሉ።
ከላይ በምስል የሚታየው አለት በጅማ ዞን በየቡ ከተማ የተገኘ ነው።
የተገኘው ድንጋይ ሜትሮይት ወይም ሌላ ዓይነት ከህዋ የተገኘ አለት መሆን አለመሆኑን ለመወሰን የላብራቶሪ ምርመራ አስፈላጊ ነው።
አሁን ባለበት ደረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም።
Meteorites ከተለመዱት የምድር አለቶች የሚጋሩት ነገር ቢኖርም በራሳቸው ደግሞ የተለየ ስሪት እና አወቃቀር ያላቸው በመሆኑ በአይን በማየት ብቻ ለመለየት አዳጋች ይሆናል፡፡
የመስኩ ተመራማሪዎች የሜትሮይትን ስብጥር ለመተንተን የረቀቁ ቴክኒኮችን እና የሳይንስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ።
ይህም የማዕድን ይዘቱን ለመመርመር ከምድር ውጭ ያሉ ንጥረ ነገሮች መኖራቸውን መለየት እና የተረጋጋ የአይሶቶፖች ምጥጥንን (isotope ratio) መለካትን ጭምር ያካትታል።
እነዚህ ትንታኔዎች የሜትሮይትን አመጣጥ እና ስለ መነሻ ምንጫቸው አስመልክቶ ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳሉ።
ሜትሮይት በምድር ላይ የሚያስከትሉት ተጽእኖ እና ጉዳት በአንፃራዊነት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡
በየዓመቱ ወደ ምድር ገጽ የሚወርዱትም በቁጥር ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኛው አካላቸው በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ሲያልፍ ተቃጥሎ ስለሚያልቅ፤ የሚያደርሱት ጉዳት ያነሰ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉልህ የሆነ ውድመት ሊያስከትሉ የሚችሉት በሚሊዮን አንዳንዴም በሺህ ዓመታት የሚከሰቱት ብቻ ናቸው፡፡
ከዚህ አኳያ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ቴሌስኮፖችን በመጠቀም ካለማቋረጥ እንቅስቃሴያቸውን በንቃት በመከታተል ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉትን አስቀድሞ በመለየት የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ።
ለምሳሌ ፦ በሀገራችን አቆጣጠር ከ5 ዓመት በኋላ ማለትም በሚያዝያ ወር 2021 ዓ.ም. አፓፊስ (Apophis) የተሰኘ 340 ሜትር ስፋት ያለው አስትሮይድ Geosynchronous ሳተላይቶች ካሉበት 35, 786 ኪ.ሜ. ከፍታ ዝቅ ብሎ ከመሬት በ31, 860 ኪ.ሜ. ከፍታ ላይ እንደሚደርስ ትንበያዎች ያሳያሉ።
የሰው ልጅ የተለያዩ መሳሪያዎችን እና ቴክኒኮችን በመጠቀም ህዋን መመርመር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህንን ያክል ግዙፍ አለት ወደ መሬት ሲጠጋ የመጀመሪያው ክስተት እንደሆነ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የአስትሮይድ እንቅስቃሴን ለመከታተል (Asteroid Tracking) የሚያስችል የቴሌስኮፕ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡ "
#SSGI
@tikvahethiopia
#ትግራይ
ባለፉት 3 ወራት በዘራፊዎች ጥቃት ለደረሰባቸው 482 ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱን መቐለ የሚገኘው የዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አስታወቀ።
በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ብርሃነ ገ/ሚካኤል ለትግራይ ሬድዮ በሰጡት ቃል፥ ከሚያዝያ እሰከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ባሉት ወራት በቢላዋ ሌሎች መሳሪዎች በዘራፊዎች ጥቃት የደረሰባቸው 482 ሰዎች በሆስፒታሉ የድንገተኛ የህክምና ክፍል ታክመዋል።
የጥቃቱ ሰለባዎች የ9 ዓመት ዕድሜ ካለው ህፃን አስከ የ70 አመት አዛውንት የሚያካትት እንደሆነ ተናግረዋል።
ከነዚሁ ተጠቂዎች 69ኙ ሴቶች ናቸው።
የሆስፒታሉ የህክምና ተገልጋዮች የመቀበያ ሰነድ እንደሚያመላክተው፦
- በሚያዝያ 183 ሰዎች
- በግንቦት 136 ሰዎች
- በሰኔ 163 ሰዎች በዘራፊዎች ጥቃት ደርሶባቸው ታክመዋል።
ሆስፒታሉ ያለው ውስን የመድሃኒት ፣ የህክምና ቁሳቁስና ባለሙያ ለእርጉዝና የሚወልዱ እናቶች እንዲሁም ለሌሎች የቆየ ህመም ላለባቸው ተገልጋዮች የቅድምያ አገልግሎት ከመስጠት ፈንታ የዘራፊዎች የጥቃት ሰለባዎች ለሆኑ ድንገተኛ ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት በመስጠት መጠመዱ ሌላ ጫና እንደፈጠረበት ተገልፀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#TigrayRadio
@tikvahethiopia
#ዛህራ_ዱቄት
ዛህራ ዱቄት ጥራት ያለውን ልዩነት ያግኙ። ዛህራ ስፔሻል ዱቄት በጥራት ተዘጋጅቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርቦሎታል። ለዳቦ፣ ለኬክ ፣ ለኩኪስ፣ ለገንፎ እነሆ ዛህራ ዱቄትን ይሞክሩት ይመሰገኑበታል ።
በባለ 5ኪሎ ፣በባለ 10ኪሎ፣ በባለ 25ኪሎ ፣ በባለ 50ኪሎ እንደፈለጉት አማራጭ ቀርቦሎታል።
ለበለጠ መረጃ ፦ በ0911073299 / 0912609914 ይደውሉልን ።
አድራሻችን ፦ሐዋሳ ኢንደስትሪ መንደር በ ፔፕሲ ፋብሪካ 200ሜትር ገባ ብሎ
ዛህራ ዱቄት ፋብሪካ ጥራት መለያችን ነው።
🔈#መልዕክት
" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ፦
- ሰላምን፣
- መረጋጋትን
- ፍቅርን
- አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
#ኢትዮጵያ🙏
@tikvahethiopia
#Ethiopia
በነዳጅ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከሉ ይታወቃል።
ይኸው ክልከላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።
ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ሳይኖር ወይም ግልጽ የሆነ ሕግ ሳይወጣ እና ሕግን የተከተለ ክልከላ ሳይኖር ' ከላይ በወረደ ወይም ተሰጠ ' በተባለ አቅጣጫ ላይ ብቻ በመመሥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችን እያተጓጎለ እንደሆነ ጠቁሟል ኮሚሽኑ።
ኮሚሽኑ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንድሂህ ብሏል ፦
- በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሕግ አግባብ ወይም ድንጋጌ የታገዘ አይደለም፡፡
- ለማንኛውም አይነት አገልግሎት የሚውሉ ከባድ የጭነት ተሽከርኮሪዎች፣ የእርሻ ትራክተሮችና ለቱሪስት ማስጎብኛ የሚያገለግሉ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡
- በግብርና ፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ፣ በሆልቲካልቸር ፣በቱሪዝም ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በግንባታ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው።
- በተለይ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ልዩ ባህሪ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል።
#ReporterNewspaper
@tikvahethiopia
#Somaliland #US
ዛሬ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ነበሩ።
አምባሳደር ሪቻርስ ሪሌይ ፤ ሶማሌላንድ ሀርጌሳ ሄደው ከሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር መክረዋል።
ከሌሎችም ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋርም መወያየታቸው ተሰምቷል።
አምባሳደሩ ፤ አሜሪካ በቀጠናው ብልጽግናን እና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለመደገፍ የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንዳላት አረጋግጠዋል።
ዲፕሎማሲያዊ እና የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ቀጠናዊ ትብብር እና ውይይትን ያበረታቱም ሲሆን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የምርጫ ጊዜን በማክበር አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።
ከግሉ ሴክተር መሪዎች ጋር በመገናኘት ከአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነት እንዴት እንደሚጠናከር መነጋገራቸው ታውቋል።
የነቃ ሲቪል ማህበረሰብ እና ነፃና ሙያዊ ስርዓቱን ያከበረ ፕሬስ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል ተብሏል።
ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂም ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን አሳውቀዋል።
በቀጠናዊ ጉዳዮች ፣ በአፍሪካ ቀንድ ትብብርን ማጎልበት ፣ በምርጫ ጉዳይ ፣ በሶማሌላንድ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በሶማሊያ፣ ሞቃዲሹ ያለው ኤምባሲ የዛሬውን የአምባሳደሩን የሀርጌሳ ጉብኝት በተመለከተ ያሰራጨውን የጽሁፍ መግለጫን አንዳንዶች ' ያልተለመደ ነው ' ብለውታል።
ሀገሪቱ " ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ፤ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት " እያለች መጥራቷ በቋንቋ አጠቃቀም ላይ የታየ ጉልህ ለውጥ ነው ያሉ አልጠፉም።
የአምባሳደሩን ሀርጌሳ ላይ መገኘትን የኮነኑም አሉ። ገለልተኛ አይደሉም ሶማሊያን ይደግፋሉ በሚል።
ሶማሊያውያን ደግሞ በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ አሜሪካን መቃወም ይዘዋል።
" መግላጫው ሶማሌላድ ስለ ተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ምንም ያለው ነገር የለም " በማለት እንዲሁም " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት እንደሆነች ሳይገለጽ መቅረቡ ሌላ ነገር ከጀርባው የያዘ ነው " በሚል ነው የተቃወሙ ያሉት።
#Somaliland
#Hargeisa
@tikvahethiopia
#Tigray
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።
ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት እየተሰጠ ነው።
በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን መስጠት ተግባራዊ ተደርጓል።
በመቐለ ፣ አኽሱም ፣ ዓዲግራት ፣ ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና አጠቃላይ ከ54,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፈተናው ከሌሎች ክልሎች ለምን ቀድሞ ጀመረ ?
ፈተናውን የሚወስዱት በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች ናቸው።
በ2012 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል የነበሩ (code 01) ብዛታቸው ከ31 ሺህ የሆኑ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 2 እስከ 5 /2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።
ከኮረም ፣ አላማጣ ፣ ዛታ ፣ ኦፍላ ፣ ራያ ጨርጨር ፣ ራያ ዓዘቦ፣ ማይፀብሪ፣ ላዕላይና ታሕታይ ፀለምቲ ሆኖው ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 3 አስከ 5 /2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 6 ና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ተጉዘው ከሀምሌ 9 እሰከ 11/2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 12 እና 13 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።
በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል የነበሩ ( Code 07) የሶሻልና የተፈጥሮ ሳይንስ ብዛታቸው ከ23 ሺህ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው ከሀምሌ 9 አስከ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 13 እና 14 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።
#TikvahEthiopia
#TigrayEducationBureau
@tikvahethiopia
አሜሪካ ምን አለች ?
" ለገንዘብ ተብሎ ተማሪዎች እና ንጹሃንን ማገት ሊቆም ይገባል " - አሜሪካ
አሜሪካ አዲስ አበባ ባሉት አምባሳደሯ ኢርቪን ማሲንጋ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ ፥ " ለገንዘብ ተብሎ ተማሪ እና ንጸሃንን ማገት ሊቆም ይገባል " ብላለች።
አምባሳደር ማሲንጋ ፦
" ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች እየተፈጸሙ ያሉ እገታዎች የተራዘመ ግጭት ወንጀለኞችን እንዳደፋፈረ ፤ የህግ የበላይነትንም እንዳዳከመው ያሳያል።
ለገንዘብ ሲባል በተማሪዎች እና ንጹሃን ላይ የሚፈጸም እገታ ሊቆም ይገባዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከ100 ተማሪዎች እና መንገደኞች ለገንዘብ ሲባል ታግተዋል። "
በባለፈው ሳምንት አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆኑ ሌሎች መንገደኞችን ጨምሮ " ገብረ ጉራቻ " ላይ መታገታቸው ይታወሳል።
#USA
#Ethiopia
@tikvahethiopia
#ስፖርት #ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ።
ቡድኑ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ፍጻሜውን እስካገኘበት የሊጉ የመጨረሻ መርሃግብር ድረስ ከመቻል የእግር ኳስ ቡድን ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ነው ሻምፒዮን የሆነው።
ዛሬ በተካሄደ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድህንን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
በዓመቱ 64 ነጥብ በመሰብሰብም ከመቻል በ1 ነጥብ በልጦ አጠናቋል።
መቻል በዓመቱ የፍጻሜ መርሃግብር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ተፋልሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም በ1 ነጥብ ተበልጦ ዋንጫውን ተነጥቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ማሳካት ችሏል።
ቲክቫህ ስፖርት👇
/channel/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport
#Update
ተማሪውን በመድፈር የተከሰሰው የዩኒቨርሲቲ መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።
ከሳምንታት በፊት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ስለተደፈረች ተማሪ እና ሂደቱም በሕግ እንደተያዘ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።
ይኸው መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።
ተከሳሽ አየለ ሀይሉ ሞላ ይባላል።
የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 9፡00 ሰዓት ላይ የሚያስተምራትን የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ " የተበላሸብሽን ዉጤት አስተካክልሻለሁ ፤ አሳይመንት ይዘሽ ኢስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነይ " ሲል ይቀጥራታል።
የግል ተበዳይ ተማሪ ነይ ወደ ተባለችበት ቦታ ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለች ተከሳሽ በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክ/ከተማ ከሚገኘዉ የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ ላይ ሆኖ የግል ተበዳይን ጠርቶ ወደ መኖሪያ ክፍሉ እንድትገባ ያደርጋታል።
ተከሳሽ የግል ተበዳይን ውጤት ለማስተካከል ሴትነቷን ለመጠቀም ያቀረበላትን ጥያቄ " አልቀበልም " ስትል በእምቢታ ትፀናለች።
ተከሳሽ ካንተ ጋር አልተኛም ስትል አሻፈረኝ ያለችውን የግል ተበዳይ በጥፊ እያላጋ ከለፈቃዷ በኃይል አስስገድዶ እንደደፈራት የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።
ተከሳሽ የተከሰሰበት ክስ የወልቂጤ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎት ቀርቦ የተነበበለት ክስ የወንጀል ድርጊቱ " አልፈፀምኩም " ሲል ክዶ ተከራክሯል።
ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀርቦ አሰምቷል። በዚህም ግለሰቡ የወንጀል ተግባሩን መፈፀሙ አረጋግጧል።
ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አስቀርቦ ቢያሰማም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።
ፍ/ቤቱ መምህሩን በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ፥ " የዚህ መምህር የቅጣት ዉሳኔ በመሰል ችግር ዉስጥ ለተዘፈቁ መምህራን የማስጠንቀቂያ ደወል ይሁን " ሲል አስጠንቅቋል።
/channel/tikvahethiopia/88052
#CentralEthiopiaPolice
@tikvahethiopia
#Gofa
ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ፤ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የወረዳው ዋና አስተዳደር ፥ እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱን አመልክቷል።
የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።
በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ተሰምቷል።
በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
መረጃው ከገዜ ጎፋ ወረዳ ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia
#Update
ሕንድ በማይናማር እንዲሁም ካምቦዲያ በሳይበር ወንጀል / የኦንላይን የማጭበርበሪያ ማዕከላት (Online Scam Centers) ውስጥ ያሉ ዜጎቿን አስወጣች።
ሀገሪቱ በማይንማር፣ ማያዋዲ ' ሽዌ ኮ ኮ ' በሚገኝ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ 11 ተጎጂ ዜጎቿን እንዳስወጣች ገልጻለች።
ሕንዳዊያኑ ከማዕከሉ እንዲወጡ የተደረገው በማይናማር ባለስልጣናት እና በአካባቢው ወጣቶችን ከቦታው እንዲወጡ በሚረዱ ሰዎች ርብርብ ነው።
አሁን ላይ እነዚህ ሕንዳዊያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሕንድ እንዲመለሱ እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአካባቢው ያገኘው መረጃ ያሳያል።
ከዚህ በተጨማሪ የሕንድ መንግሥት ከካምቦዲያ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር በሳይበር ወንጀል / ኦንላይን ማጭበርበር ማዕከላት ውስጥ እንዲሰሩ ሲደረጉ የነበሩ 14 የሕንድ ዜጎችን አስወጥቷል።
በፍጥነት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ስለመሆኑም ሰምተናል።
ሕንድ በርካታ ወጣቶቿ በማጭበርበሪያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙባት ሀገር ስትሆን ከዚህ ቀደም መሰል ዜጎቿን የማስወጣት እርምጃ የወሰደች ሲሆን አሁንም ቀጥላለች።
ሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ ተጠቂ ናቸው ያሏቸው ዜጎቻቸውን የማስወጣት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው።
በማይናማር፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ ፣ ቻይና ታይላንድ ድንበር፣ ታይላንድ ማይናማር ድንበር ባሉ የማጭበርበሪያ ማዕከላት እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ የሌሎች ሀገር ዜጎች ይገኛሉ።
አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች አሉ (ከተለያዩ ሀገራት)።
በስፍራው የሚገኙት ብዙሃኑ ወጣቶች ናቸው።
ወደዚህ ተግባር የገቡት እራሳቸው ተጭበርበረው ነው / ይህ ማለት እራሳቸውም ተጎጂዎች (ሰለባ) ናቸው።
ደላሎችና ኤጀንሲዎች ወጣቶች 'ወደ ታይላንድ / ወደ ሌላ ሀገር' ለ፦
- ሴልስ
- የማርኬቲንግ
- ለሆቴል እንግዳ ተቀባይ
- ለተቋማት ደንበኞችን ማነጋገር በሚል ነው የሚልኳቸው።
በኃላም ወደ ጎረቤት ሀገራት በመውሰድ የተደረጀ የኦንላይ ማጭበርበር ስራ ላይ እንዲሰማሩ ነው የሚደረገው።
ወጣቶቹ ከሚሰማሩባቸው ተግባራት ዋነኛው ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት በመክፈት ሰዎችን በተለይ ሴትን በወንድ / ወንድ በሴት አስመስለው በማነጋገር ገንዘብ ማጭበርበር ነው።
የታዘዙትን አድርገው ገንዘብ ካላመጡም የከፋ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል።
ወጣቶችን እንዲያጭበረብሩ የሚያሰሩ ማፊያዎቹ በቀጠናው እጃቸው ረጅም የሆነ ሰዎች ናቸው።
እጃቸው በረዘመ ማፊያዎች በሚመራው የሳይበር ወንጀል / የኦንላይን ማጭበርበር / ተግባር በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ይዘረፋል።
ስለ ማጭበርበሪያ ስልቶቹ / ሰዎችን በምን መንገድ እንደሚያጭበረብሩ በዚህ ያንብቡ ፦ /channel/tikvahethiopia/88986
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ወላጆች ልጆቻችሁን ጠብቁ !!
በክረምት የእረፍት ጊዜ ወላጆች ለልጆቻቸው በቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል አሳሰበ።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ዛሬ (ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም) ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ውሃ ባቆረ ጉድጓድ የገባ ታዳጊ ህይወቱ ማለፉን ገልጸዋል።
" ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ዋና ለመዋኘት የገባ የ13 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ አልፏል" ያሉት አቶ ንጋቱ፣ "የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊውን አስከሬን አውጥተው ለፖሊስ አስረክበዋል " ብለዋል።
" በአዲስ አበባ ታዳጊዎችና ወጣቶች በቂ የዋና ችሎታ ሳይኖራቸው ለዋና በሚል ውሃ ባቆሩ ጉድጓዶች እየገቡ ህይወታቸውን ያጣሉ " ነው ያሉት።
አሁን ትምህርት ቤቶች ዝግ ስለሆኑ ታዳጊዎችና ወጣቶች ለጨዋታ በሚል ድርጊቱን ስለሚፈጽሙ ወላጆች በቂ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው አሳስበዋል።
ኮሚሽኑ አደጋውን ለመከላከል የሚያሰችሉ በሚል በተደጋጋሚ የሚያስተላልፋቸውን የጥንቃቄ መልዕክቶች ህብረተሰቡ፣ በተለይ ወላጆች፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች እንዲተገብሩ ጠይቋል።
ችግሩ እየተደጋገመ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን፣ በዚህ አደጋ ምን ያህል ታዳጊዎች ህይወታቸውን እንዳጡ በቀጣይ የሚዳሰስ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች ለሁላችንም!
ሁሉንም ወሳኝ ጨዋታዎች ፣ ደማቅ ግጥሚያዎች ፣ የዋንጫ ፍልሚያዎች በዲኤስቲቪ!
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ ላሊጋ ፣ ሴሪአን ጨምሮ ከጨዋታ እስከ ትንታኔ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ ... ሁሉም በዲኤስቲቪ!
እንደየምርጫዎ በሁሉም ፓኬጅ ላይ ኳስ ያለው ዲኤስቲቪ!
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#DStvEthiopia
#ሁሉምያለውእኛጋርነው
#DStvSelfServiceET
🔈#የተማሪዎችድምጽ
ባለፈው ወር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከፈተናው ጋር ተያይዞ ያላቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
ተማሪዎቹ ፦
- የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እኩል ፈተናውን ወስደው፣ ውጤት ለምን በተለያየ ጊዜ ተገለፀ ?
- የመንግሥት ተፈታኞች በብዛት ሲያልፉ በርካታ የግል ተቋማት ተፈታኞች ለምን ወደቁ?
- እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ነጥብ ያላቸው መቶ ጥያቄዎች ተፈትን 37.92 አይነት ውጤት እንዴት ተመዘገበ ? የAI ስህተት ካለ ይነገረን።
- በጣም ተዘጋጅተን የተፈተንን ሰዎች በዚህ ትኩረት ሳይሰጠው በተፈተነው ፈተና ምክንያት ሞራላችን እንዲነካ እና ተስፋም እንድንቆርጥ ተደርገናል።
- ፈተናው ላይ ትልቅ ውጤትን ያመጣሉ የተባሉ ብዙ ጎበዝ ልጆች እንደተጠበቀው አልሆነም።
- ውጤታችን እንደገና ሊታይልንና የተፈተነው ጥያቄ ከነመልሱ ይፋ ሊደረግልን ይገባል።
... የሚሉ ቅሬታዎች በተፈታኞቹ ተነስቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ የሆኑትን እዮብ አየነው (ዶ/ር) ጠይቋል።
ከውጤት ነጥብ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ኃላፊው ተከታዩን ብለዋል ፦
1ኛ. የጤና ትምህርት ዘርፍ ሁለት ፈተና (ጠዋት ከ100 ከሰዓት ከ100 በድምሩ ከ200) ስለሚፈተኑና ለማለፊያ የሁለቱ ፈተናዎች ውጤት ተደምሮ አማካኝ ውጤት ስለሚያዝ ውጤታቸው በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡
2ኛ. አንዳንድ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ለምሳሌ ፦ ሒሳብ እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት በተለያዩ ምክንያቶች ተማሪዎች የተፈተኑት ጥያቄ ቁጥር ከመቶ ያነሰ ስለነበር ያገኙት ውጤት ወደ መቶ ሲቀየር በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡
" ውጤት ሲገለፅ የጊዜ መቀዳደም ካልሆነ በስተቀር በሲሰተሙ ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበረ " ኃላፊው ገልጸዋል።
የማለፍ ምጣኔን በተመለከተም ፥ " ተፈታኞቹ የተማሩባቸውን ተቋማት እንዲሁም የራሳቸውን ብቃት መመልከት " አለባቸው ብለዋል።
ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች 100% ያሳለፉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዳሉ ኃላፊው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ይህንን ምላሽ የተመለከቱ ተማሪዎች ፥ " ለቅሬታችን የተሰጠው ምላሽ ተገቢ አይደለም ፤ አሁንም ቢሆን ውጤታችን እና የሰራነው በድጋሚ ይታይ " ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ የፋርማሲ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ፥ " ከዚህ በፊት እንደነበረው የጠዋት እና የከሰአት አማካይ (Average) የሚያዝ እንደሆነ በምላሹ ላይ ሰምተናል " ብለዋል።
" ግን ፈተናውን ከጨረስን ከአንድ ቀን በኋላ ፈተናው ችግር አለበት / ተሰርቋል ተብለን በአንድ ቀን ልዩነት እንደገና ፈተና ተቀምጠናል፤ ስንቀመጥም የጠዋቱን ብቻ ነበር አንዴ የተፈተንነው እንጂ የከሰአቱን ሌላ ጊዜ ነው የተባልነው " ሲሉ አስረድተዋል።
" ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ በጠዋቱ ፈተና ብቻ ነው pass and fail የሆነው። ስለዚህ ትምህርት ሚኒስቴር ቃሉን አክብሮ የከሰአቱን ፈተና ከተፈተንን በኋላ ነው አማካይ መያዝ ያለበት " ብለዋል።
ተማሪዎቹ አለን ያሉትን ቅሬታ ይዘን የሚመለከተውን አካል የምናነጋግር ይሆናል።
Via @tikvahuniversity
🔈 #ተጠንቀቁ
ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት " ስራ ነው " በሚል ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ ወጣቶቻችን የትም ሀገር ይሁን የምትሄዱት ስራው ምን እንደሆነ እና ለደህንነታችሁም አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጡ።
" ለስራ ውጭ እንላካችሁ " የሚሉትን ደላሎችንም ሆነ ኤጀንሲዎች ፦
- ስራው ምንድነው ?
- በትክክል ድርጅቱ ያለበት ሀገር የት ነው ?
- የድርጅቱን ህጋዊነት የሚያሳይ ማስረጃ አሳዩን !
- ባለበት ሀገር ሕጋዊ ስርዓት የተመዘገበበትን ፋይል አሳዩን ! ብላችሁ ጠይቋቸው።
ከዚህ ውጭ በተድበሰበሰ ሁኔታ " ጠቀም ያለ ገንዘብ ነው የምታገኙት " በሚል ብቻ መረጃ ፤ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ የውጭ ሂደት ብታቋርጡ መልካም ነው።
አንዳንድ ስለ ገንዘብ እንጂ ፍጹም ስለ ሰው ህይወት የማያሳስባቸው ደላሎች እና ኤጀንሲዎች በርካታ ወጣቶችን እያታለሉ መጀመሪያ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ሌላ ምንም ደህንነቱ ወዳልተረጋገጠ ሀገር እየላኩ ሰዎችን በማጭበርበር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች እያስገቧቸው ነው።
በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በሚቆዩበት ወቅት በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ይፈጸምባቸዋል።
የወጣትነት ጊዜያችሁ ሳያልፍ ህይወታችሁን ለማሻሻል ብላችሁ እጅግ ተቸግራችሁ ፤ ቤተሰብም አስቸግራችሁ ብዙ ብር ከፍላችሁ ወደ ውጭ ሀገር የምትሄዱ ልጆች ስለምትሄዱበት ሀገር እና ስራ በደንብ አጣሩ አንብቡ።
ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና በስልካችሁ ላይ ገብታችሁ የምትሄዱበት ሀገር ስላለው ደህነት፣ ስላለው የስራ ሁኔታ ፣ እናተም ትስሩታላችሁ ስለሚባለው ስራ በደንብ አረጋግጡ።
በኦንላይን የማያታውቁት ሰው ወይም በማስታወቂያ " ለስራ ወጣቶችን እንፈልጋለን " ሲሉ አትመልሱላቸው።
⚠️ በቀጣይ " ጠቀም ያለ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ነው ! " እየተባለ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በብዛት ወጣቶችን በማዘዋወር አንዳንድ ድርጅቶች እያስገቡ ወጣቶችን የሚያሰሯቸውን የኦንላይን ማጭበርበር / Online Scam / ድርጊት አይነቶችን በዝርዝር እንዳስሳለን።
#TikvahEthiopiFamily
@tikvahethiopia
🔈#የነዋሪዎችድምጽ
" የምንኖረው በኮንሶና አካባቢው ነው።
የመብራት ለቀናት መጥፋት እና መቆራረጥ ከፍተኛ ችግር በስራችን እና በህይወታችን ላይ እያደረሰ ነው።
ለቀናት ሲጠፋ ችግሩን ለመንግስት እንዳንናገር ድንገት ይመጣል መጣ ስንል ደግሞ በአንድ ሰአት ውስጥ ሁለት ሶስቴ ይቆራረጣል።
አሁን ላይ ስራ መስራት አስቸጋሪ ሆኗል።
በመብራት የሚሰሩ ስራዎች በተለይም ጸጉር ቤቶች ፣ ብየዳና የማሽነሪ ስራዎች እንዲሁም የእንጨት ቤቶች ላይ የሚሰሩ ሰዎች ተስፋ ቆርጠዋል።
እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ድምጻችንን ሰሙንና ችግሩን ፍቱልን።
ሌላው መንግስት በዚህ ሀኔታ እያለን እና አቅማችን በተዳከመበት ወቅት የግብር ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑ አሳስቦናል። ነባራዊዉ ሁኔታ ካልተገናዘበና ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ ልንሆን እንችላለን " - የኮንሶና አካባቢው ማህበረሰብ
#TikvahEthiopiaFamilyKonso
@tikvahethiopia
🌍Join Africa’s Largest Hackathon in Addis Ababa!🔥
Dear university and high school students,
A2SV is hosting Africa's largest hackathon, and it's happening here in Addis Ababa! Last year, 3,709 students from 47 countries across Africa created digital solutions using AI. Now it's your turn! 🫵🏽
Register for the hackathon to enhance your skills and receive guidance from top tech mentors at companies such as Google, Meta, TikTok, Nvidia, and more. ✨
Compete for a share of $30,000 USD and make a real impact. Don’t miss your chance to shine and win!
REGISTER NOW at hackathon.a2sv.org
Let us show the world what Africa can do! 💪🏽
" ክብሯት እና ክብሯን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን ! " - ጆ ባይደን
በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዴሞክራት ፓርቲያቸውን ወክለው ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የጤናቸው ነገር አሳሳቢ ነው እየተባለ ነው።
" እርጅናም ተጫጭኗቸዋል፣ በትልልቅ መድረኮች የሚነገሯቸውን ነገሮች እየሳቱ ነው ፤ ስለዚህ ምክትላቸው ይተኳቸውና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከሩ " የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።
ባይደን ግን ከጤናቸው ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ ፥
- ፍጹም ጤናማ መሆናቸውን ፣
- እንደ ቀድሞው መንቀሳቀስ አቅቷቸው ሥራቸውን መጨረስ ካልቻሉ ብቻ እንደበቃቸው ምልክት እንደሚሆን፣
- አሁን ላይ ምንም ዓይነት የድካም ምልክት እንደሌላቸው ነው የሚመልሱት።
ትላንት በነበረ አንድ የNATO ፕሮግራም የሚዲያ መግለጫ ላይ ፥ የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪን ለንግግር ሲጋብዙ " ፕሬዝደንት ፑቲን " ብለው መጥራታቸው በሥፍራው የነበረውን ታዳሚ አስደንግጧል።
ዜሌንስኪም ክው ብለው ቀርተዋል።
ወዲያው ግን ጆ ባይደን ፥ " የፑቱን ነገር አሳስቢ ሆኖብን እዛ ላይ ብዙ ስለቆየሁ ነው ፤ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ " ሲሉ ስህተታቸውን አርመዋል።
ዜሌንስኪ " እኔ እሻላለሁ ! (ከፑቱን ማለታቸው ነው) " ሲሉ ተደምጠዋል። ባይደንም ፥ " በእርግጥም በደንብ ትሻላለህ " ሲሉ መልሰዋል።
ከዚህ ቀጥሎ በነበረ አንድ መግለጫ ላይ ደግሞ የገዛ ምክትላቸውን ካማላ ሀሪስን " ምክትል ፕሬዝዳንት ትራምፕ " ብለው ሲጠሩ በርካቶች በድንጋጤ ተመልክተዋቸዋል።
በቅርብ ከሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበረ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ክርክር ወቅት ያሳዩት አቋምም ምርጫውን ለማሸነፍ አጠያያቂ ሆኖ ነበር።
የ81 ዓመቱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ግን " ደህና ነኝ ምርጫውንም አሸንፋለሁ " ባይ ናቸው።
ክስተቶቹን የሚያሳይ ቪድዮ ከላይ ተያይዟል።
#BBC
#CNN
@tikvahethiopia
@samcomptech
እርሶ ከዘመኑ እኩል መራማድ ከሆነ ምርጫዎ ዘመኑን የዋጁ የላፕቶፕ ምርቶችን አኛ ጋር በተመጣጣኝ ዎጋ ያገኛሉ።
ለቢሮ፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን፣ ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ የተለያዩ ከዉጭ በምናስመጣቸዉ አዳዲስ ላብቶፖች እንታወቃለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114
/channel/samcomptech
ቤተሰባዊነት ፣ ተአማኒነት ፣ ገንዘቦቻችን ናቸዉ ! ይምጡ ይሸምቱ!
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ አሶሳ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠ 2 ሳምንት አልፏል።
የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ አገልግሎት ሊቆም እንደሚችል አሳውቋል።
ሆስፒታሉ በየቀኑ ከ400 እስከ 500 ከዞን ፣ ከወረዳ፣ ከአጎራባቹ ኦሮሚያ ክልል ታካሚዎችን ያስተናግዳል።
ሆስፒታሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር 24 ሰዓት ሙሉ የማይቋረጥ ኃይል ማግኘት ያለበር ቢሆንም ባለፉት ሳምንታት የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።
ኃይል ከተቋረጠበት ቀን አንስቶ ለጄኔሬተር በየቀኑ ከ180 እስከ 200 ሊትር ነዳጅ እየተጠቀመ ነው።
ሁለት ጄኔሬተሮች ያሉ ቢሆንም ሙሉ ሆስፒታሉን ኃይል እንዲያገኝ የሚያስችሉ አይደሉም።
ያለ ጊዜያቸው የሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ለማቆየት የሚሆኑ ማሽኖችን ማስነሳትም ከባድ ሆኗል።
በዚህ ማሽን ውስጥ የሚቆዩ ሕጻናት ያልተቋረጠ ኦክስጅን ማግኘት ስላለባቸው ኃይል መቋረጥ ካጋጠመ በሕጻናቱ ላይ ሞት ሊያስከትል ይችላል።
ሆስፒታሉ የተወሰኑ የሥራ ክፍሎችን የኃይል አቅርቦት እያጠፋ ነው ጄኔሬተሩ ሲነሳ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ወደ ጨቅላ ሕጻናት ማቆያ ማሽኑ የሚቀይረው። ሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ኃይሉ ሲፈለግ ደግሞ ማሽኑን ለማቋረጥ ይገደዳል።
ቀድሞም የበጀት እጥረት የሚፈተነው ሆስፒታሉ ለጄኔሬተሩ የሚውለው ነዳጅ ወጪ ከአቅም በላይ እንደሆነ የነዳጅ ማከማቻም አለመኖር ፈተና እንደሆነ ገልጿል።
ሆስፒታሉ ነዳጅ ከተለያዩ መ/ቤቶች እና ባለሃብቶች በልመና ነው ማታ ማታ እየዞረ የሚያመጣው።
ሁኔታው በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ጭምር ሊቋረጥ የሚችልበት አዝማሚያ እንዳለ አሳውቋል።
የአሶሳ ዞን ፥ በአሶሳ ከተማ እና በአካባቢው የኃይል መቋረጥ የተከሰተው በአጎራባች የኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኝ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ " በታጣቂዎች " በደረሰ ጉዳት እንደሆነ አሳውቋል።
#BBCAMHARIC
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ
በኮሪደር ስራ ምክንያት ፦
➡️ ከፊጋ መስመር ወደ ቀኝ ታጥፎ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ
➡️ ከጃክሮስ መስመር በኩል መብራቱን ተሻግሮ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ
➡️ ከኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስቴር ጫፍ ታጥፎ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ
ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አንስቶ ሙሉ ቀን እና ምሽት ለማንኛውም ተሽከርካሪ ዝግ እንደሆኑ ተገልጿል።
ሌላው ፤ ከአያት ወደ መገናኛ እና ከመገናኛ ወደ አያት ቀጥታ ማለፍ እንጂ አደባባዩን መዞርም ሆነ ማቋረጥ የተከለከለ ነው ተብሏል።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም መልዕክት ተላልፏል።
መረጃው ከአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia
#Africa
" በኮንፌዴሬሽን ለመዋሃድ ተስማምተናል " - በመንፈንቅለ መንግስት የመጡት የሶስት ሀገራት መሪዎች
ቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እንዲሁም ማሊ በኮንፌደሬሽ ለመዋሃድ ተስማሙ።
በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት የቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እና ማሊ ወታደራዊ ሁንታዎች በኮንፌደረሽን ለመዋሃድ ማስማማታቸው ተሰምቷል።
ከምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ጥምረት (ECOWAS) ፍቺ መፈጸማቸውንም ገልጸዋል።
የ3ቱም ሃገራት ወታደራዊ ሁንታዎች ስልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በተለይ ደግሞ ECOWAS ብርቱ ውትወታ እና ማዕቀብ ሲደረግባቸው ነበረ።
ጥምረቱ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚያደርግ ከገለጸ በኋላም ከሶስቱም ሃገራት ብርቱ ትችት ሲደርስበት ቆይቷል።
ሀገራቱ ECOWASን የቀድሞ ቅኝ ገዢያቸው " የፈረንሳይ ጉዳይ ፈጻሚ " በማለት ክፉኛ ሲወቅሱት ነበረ።
ይህንንም ተከትሎ ከፈረንሳይ ጋር የነበራቸውን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነትን በማቋረጥ ወደ ሩስያ አማትረዋል።
አሁን ደግሞ የስስቱም ሃገራት መሪዎች በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ ባካሄዱት ስብሰባ " የሳሕል ሃገራት ኮንፌደሬሽን መንግስት " በሚል ለመዋሃድ መስማማታቸውን እና መፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ሀገራቱ በድምሩ 72 ሚሊዮን ህዝብ ያላቸው ሲሆን 3ቱም በታጣቂ ቡድኖች በሚፈጠር አለመረጋጋት እየተፈተኑ ይገኛሉ።
አሁኑን ስምምነት ተከትሎ በጸጥታ ጉዳዮች አብረው እንደሚሰሩ የኢኮኖሚ ትስስራቸውንም እንደሚያጠናክሩ ይጠበቃል።
ECOWAS በዛሬው ዕለት ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን ይህ የኮንፌደሬሽን ምስረታ ጉዳይ ዋና የመዋያያ አጀንዳው እንደሚሆን ተዘግቧል።
መረጃው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፣ የዶቼቨለ ሬድዮ እና አናዱሉ ነው።
@tikvahethiopia
#ArbaMinch
በኢትዮጵያ ግዙፍ ነው የተባለለት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ተመረቀ።
ሆስፒታሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተመረቀው።
ስለ ሆስፒታሉ ፦
- የሆስፒታሉ ግንባታ የተጀመረው በመጋቢት 29 /2007 ዓ/ም ነው።
- ለግንባታ 1.4 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበታል።
- 25 ሺህ ካሬ ላይ ነው ያረፈው።
- አሁን ላይ እጅግ ዘመናዊ የተባሉ የሕክምና መስጫና የምርምራ ቴክኖሎጂዎች አሉት።
- 600 ደረጃቸውን የጠበቁ አልጋዎች አሉት።
- የሄሊኮፕተር አምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ አለው።
- የውስጥ ደዌ ፣ የቀዶ ጥገና ፣ የሕጻናትና እናቶች ፣ የማህጸን ጽንስ ፣ ከአንገት በላይ፣ የአጥንትና የስነ አእምሮ ... ሌሎችም ህክምናዎች ይሰጡበታል።
- ኦክሲጅን የሚመረትበት ክፍል / ኦክሲጅኑም በየክፍሉ የሚያዳርስ መስመር ፣ የዲጅታል ኤክስሬይ ማሽን ፣ ሲቲ ስካን ፣ ኤም አር አይ ፣ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ ማሽኖች አሉት።
- በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 100 ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞች አገልግሎት ይሰጡበታል።
- ከ7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአካባቢውና የአጎራባች ክልሎች፣ ዞኖች ነዋሪዎች በአጠቃላይና በስፔሻሊቲ ደረጃ አገልግሎት ይሰጣል።
#SouthEthiopiaRegion
#ArbaMinch
Photo Credit - PM Dr. Abiy Ahmed
@tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ ነገ ለምን ተዘግቶ ይውላል ?
በአዲስ አበባ የአሜሪካ አሜባሲ ነገ ሀሙስ ሙሉ ቀን ተዘግቶ ይውላል።
የሚከፈተውም በነጋታው አርብ ዕለት ነው።
ኤምባሲው ተዘግቶ የሚውለው የሀገሪቱን የነጻነት ቀን ለማክበር ነው።
አሜሪካ በየአመቱ እኤአ ሃምሌ 4 ላይ የነጻነት ቀኗን ታከብራለች።
ሀገሪቱ እኤአ በ1776 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ በ1769 ዓ.ም ነው ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷዋን ያወጀችው።
@tikvahethiopia