#SafaricomEthiopia
ምን እየጠበቅን ነው? ቲክቶክ ላይ የሙዚቃች ችሎታችንን እያሳየን እስከ 400,000 ብር ድረስ እንሸለም እንጂ!
የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!
መልካም ዕድል!
#1Wedefit
#Update
" ለሚፈጠረው ችግር እኛ ተጠያቂ አይደለንም " - የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን
የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ ባወጣው ባለ 3 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፥ " ጤናማ ያልሆነ ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው " ብሏል።
" ጤናማነት ሂደት የሌለው ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር አይችልም " ብሎ በማመን ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱን ማግለሉን አሳውቋል።
" በቡድናዊ ማን አለበኝነት የሚካሄድ " ብሎ የጠራውን ጉባኤ ተከትሎ በሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ተጠያቂ አለመሆኑ አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ፤ የህወሓት ህጋዊ እውቅና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት መመለስ ሲገባው ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ እውቅና መሰጠቱ እንደማይቀበለው ገልጿል።
በህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መካከል እና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግባባት ያልተደረሰበት በእልህ የሚካሄደው ጉባኤን እንደሚቃወምም የገለጸው የቁጥጥር ኮሚሽኑ ፤ " ጉባኤው ተከትሎ በትግራይ ህዝብና በህወሓት የሚፈጠረው አደጋ ተጠያቂው በማንአለበኝነትና በእኔነት ስሜት በመጓዝ ላይ ያለው ቡድን ነው " ብሏል።
" በህወሓት የተፈጠረው ችግር መፍትሄው የቡድን ፉክክር ፣ እኔነትና እልህ አይደለም " ያለው ኮሚሽኑ " ደርጅቱ የሚድነው በስርአታዊና ተቋማዊ ትግል ነው " ሲል ገልጿል።
የህወሓት የፅ/ቤት ሃላፊና የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብሄር ትላንት የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በጉባኤ እንዲሳተፉ በፃፉት ደብዳቤ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ በመቐለ የሰማእታት ሓወልት አዳራሽ ይካሄዳል " ብለዋል።
ኮሚሽኑ ግራ ራሱን ከጉባኤው አግልሏል።
ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ ደግሞ ህወሓት በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ነገ ለሚጀምረው ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ አባላት ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ መቐለ እየተጓዙ እንደሆኑ እያሳወቀ ነው።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia
#Bangladesh
ተማሪዎች በቀሰቀሱትና በኃላም ሌላውም ዜጋ በተቀላቀለው የመንግሥት የስራ ኮታ ተቃውሞ ምክንያት ስልጣናቸውን ለቀው ከሀገር ወጥተው የሄዱት የቀድሞ የባንግላዴሽ ጠ/ሚኒስትር ሼኪህ ሀሲና ከስልጣን እንዲወርዱ " የአሜሪካም እጅ አለበት " ማለታቸውን ' ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ' አስነብቧል።
ልጃቸው ግን " ውሸት ነው " ሲል አጣጥሏል።
ሀሲና አሁን ላይ ሀገራቸውን ጥለው ህንድ ነው ያሉት።
እሳቸው ናቸው የተናገሩት ብሎ ' ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ' እንዳስነበበው ሀሲና ፤ " የደም መፋሰስ እንዳይፈጠርና እሱን ላለማየት ስልንነው ስልጣን የለቀቅኩት " ብለዋል።
" በተማሪዎች እሬሳ ላይ ተረማምደው ስልጣን መያዝ ፈልገው ነበር ግን እኔ ያንን አልፈቀድኩም፤ በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣኔን ለቅቂያለሁ " ሲሉ መግለጻቸውን አስነብቧል።
ሀሲና " የሴንት ማርቲን ደሴትን ሉዓላዊነት አሳልፌ ብሰጥና ፤ አሜሪካ የቤይ ኦፍ ቤንጋልን እድትቆጣጠር ብፈቅድ ኖሮ በስልጣን ላይ እቆይ ነበር " ማለታቸውን ገልጿል።
አሜሪካ ተቃውሞ ማቀናበሯንና ይህን ያደረገችው የአገዛዝ ለውጥ አድርጋ ፍላጎቷን ለማሟላት እንደሆነ እንደጠቆሙ ነው ' ታይም ኦፍ ኢንዲያ ' ያስነብበው።
አሁን ላይ አሜሪካ የሚኖረው ልጃቸው ሳጂብ ዋዜድ ፤ " እናቴ ከስልጣን መልቀቋን በተመለከተ የሰጠችው መግለጫ ተብሎ በጋዜጣ ታትሞ የወጣው ሙሉ በሙሉ ውሸትና የተቀናበረ ነው፤ ከራሷ እንዳረጋገጥኩት ዳካን ከመልቀቋ በፊትና በኃላ ምንም መግለጫ እንዳልሰጠች ነው " ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ሀሲና ባንግላዴሽ ፓርላማ " አሜሪካ በሀገሪቱ የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ እየሞከረች ነው " በማለት አሜሪካንን ወንጅለው ነበር።
ሴንት ማርቲን ደሴት ከ1971 (እ.አ.አ) አንስቶ በባንግላዴሽን ፖለቲካ ትልቅ ተጽእኖ ያላት ትንሽዬ ግን በጣም ወሳኝ ደሴት ናት።
ቦታው ከቤይ ኦፍ ቤንጋል ያለው ርቀት እንዲሁም ከማይናማር ጋር ያለው የባህር ወሰን በስፍራው ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ፍላጎት እንዲኖር አድርጓል።
' ቤይ ኦፍ ቤንጋል ' ን ለመቆጣጠር እንዲሁም የህንድ ውቂያኖስ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ጭምር ለመከታተል ፤ ስትራቴጂክ የሆነ ስፍራ ነው።
በዚህም በቀጠናው ኃይሏን ለማጠናከር የተሟላ ቁጥጥር እንዲኖራትና በቻይና ላይም የበላይነት ለመውሰድ አሜሪካ ወታደራዊ ቤዟን ለማቋቋም እንደምትፈልግ ይናገራል።
አሜሪካ ግን ከበርካታ ዓመታት በፊት ይህንን ቦታ እንደማትፈልገው እና በስፍራው ወታደራዊ ቤዝ እንዲኖርት እቅድ እንደሌላት አሳውቃ ነበር።
#TikvahEthiopia #TimesofIndia
@tikvahethiopia
የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ👏
የጀመርኩትን አላቋርጥም ያለችው አትሌት መነጋገሪያ ሆናለች።
ሀገሯ ቡታንን በመወከል የሮጠችው ኪንዛንግ ላሃሞ የተባለች አትሌት በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ከ1 ከሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ በመግባት ውድድሯን አጠናቃለች።
አትሌቷ ውድድሯን ስትጨርስ በቦታው የነበረው ታዳሚ እጅግ በጋለ ሞራል ተቀብሏታል።
የመጨረሻ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌቷ በፍጹም የጀመርኩትን ውድድር አላቋርጥም ብላ የውድድሩ የወርቅ አሸናፊ ከታወቀ ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ ገብታለች።
80ኛ ደረጃ የወጣችው አትሌቷ ውድድሯን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ52 ደቂቃ / 4 ሰዓት ደገማ ወስዶበታል።
በዚህ ሁሉ ፥ የቴሌቪዥን ስርጭት ያልተቋረጠ ሲሆን እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ሲያሳይ ነበር ፤ በስፍራው የነበረው ተመልካችም የትም ሳይሄድ በክብርና በትልቅ ሞራል ተቀብሏታል።
የቡታኗ አትሌት የጀመረችውን ውድድር እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ማቋረጥ ተፋልማ በመጨረሷ በበርካቶች " የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ " ተደርጋ ተወስዳለች።
ሁላችንም በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን የጀመርነውን መጨረስ፣ ለቆምንለት ዓላማ እስከመጨረሻው መሄድ እንዳለብን ያስተማረ ነው።
" እኔ አልችልም " ብሎ ፣ ተስፋም ቆርጦ አለመቆም እንጂ በተንቀሳቀስን ቁጥር ግባችን ጋር መድረሳችን የማይቀር ነው።
#TikvahEthiopia
ቪድዮ፦ ከሱፐር ስፖርት
@tikvahethiopia
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል።
@tikvahethiopia
የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ይፋ ተደርጓል ?
አጭር መልስ ፦ ሀሰት ነው ! ምንም ይፋ የተደረገ ነገር የለም።
እስካሁን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ እየተዘዋወረ ያለው " የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ " የሚለው መረጃ ምንም ምንጩ የማይታወቅ ነው።
የተሰራጨው የደመወዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ፤ የፅሁፍ ስህተቶች ጎልተው የሚታዩበት፣ የአጻጻፉ ግድፈት ያለበት፣ የድምር ጭምር ግልጽ እና ቀላል ስህተት ያለበት ነው።
ሌላው ማን ይፋ እንዳደረገው አይታወቀም።
ማህተም አላፈረበትም ፤ መረጃውንም ያወጣው መ/ቤትም አይታወቅም።
እስካሁን በይፋ ለህዝብ የተሰራጨ የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝር መረጃ የለም።
በመሆኑንም እየተዘዋወረ ያለው የደመወዝ ጭማሪ ሰንጠረዥም ሆነ የደመወዝ ጭማሪ መረጃ ሀሰተኛ ነው።
መንግሥት በቅርቡ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Ethiopia የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነዋል።
የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ለ2 ወር በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ።
የበጀት ዓመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዳኞች ለተከታታይ 2 ወራት ማለት ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ እንዲያርፉ በአዋጅ ቁጥር " 1234/2013 አንቀጽ 38 " በመደንገጉ ነው ፍ/ቤቶች በከፊል ዝግ የሆኑት።
ሆኖም ፍ/ቤቶቹ በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያቶች በተረኛ ችሎቶች ለአስተቸኳይ ጉዳዮች ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ/ም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚቀጥል ይሆናል።
እነዚህ ጉዳዮችም በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ በዜጎች መብትና በአገር ልማት ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚያሳድሩትን አቤቱታዎች የሚመለከቱ ሲሆን በእነዚህ ተረኛ ችሎቶች ላይ የሚታዩት ፦
° ከእግድ፤
° መፈቻ፤
° ቀለብና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች
° ዋስትና፤
° አካል ነፃ ማውጣት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይነታቸዉ በችሎቱ የሚወሰኑ መሰል ጉዳዮችን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
የሰበር አጣሪ ችሎቶች በመደበኛ ጊዜ የሚሰሯቸዉን አጣርተው ዉሳኔ የመስጠት ስራቸውን ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በመደበኛነት የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ፡፡
@tikvahethiopia
🔈#የነዋሪዎችድምጽ
" ተስፋ ቆርጠናል " - ቆጣቢዎች
በአዲስ አበባ የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት በሚል መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም የኮንዶሚንየም ቤት ምዝገባን በ1997 እና 2005 ያደረገ ሲሆን እጣው የዘገየባቸው ነዋሪዎች " ተስፋ ቆርጠናል " ሲሉ ገለጹ።
ነዋሪዎቹ ቃላቸውን የሰጡት #ለአሃዱ ነው።
ከተመዘገቡ 19 እና 11 ዓመታት እንዳለፋቸው የተናገሩት ተመዝጋቢዎች " ከወደ መንግስትም ምንም አይነት መረጃ እየወጣ አለመሆኑ ጥያቄ ፈጥሮብናል " ብለዋል።
" የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን " የሚሉት ተመዝጋቢዎቹ " በመንግስት በኩል ቅድሚያ እየተሰጣቸው ያሉ ነገሮች ተመዝጋቢዎቹ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋን።
ለአብነትም ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን 3 ሺህ የሚሆኑ ቤቶችን በመግንባት ለሽያጭ ማቅረቡን በማስታወስ " ለምን እንዲህ ይደረጋል ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ አልነበረም " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምን አለ ?
ኮርፖሬሽኑ " አትቆጥቡ ያለ አካል የለም ከመንግስት በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግንባታዎች እየተካሄዱ ነው " ብሏል።
" ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ " ሲልም ጠይቋል።
ለኮንዶሚኒየም ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች የት ቦታ ምን እየተሰራ እንደሆነ መግለጽ ከተቻለ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እየተሰራ መሆኑን መግለጽ በቂ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮንዶሚንየም ተመዝጋቢዎች ምን ስራዎችን እየከወነ ይገኛል ? በሚል ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ጽ/ቤቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
ሁለት አስርት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ወራት የቀረው ተመዝጋቢ ለሌሎች ዓመታት በትዕግስት እንዲጠብቅ ተገልጾለታል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሃዱ ነው።
#AddisAbaba #AhaduRadioFM
@tikvahethiopia
#ዕለታዊ : ንግድ ባንክ ምዛሬውን በትላንትናው ተመን ሲያስቀጥል በግል ባንኮችም ዛሬ ያን ያህል ለውጥ የለም።
በንግድ ባንክ ዛሬ ዶላር እንደትላንቱ መግዣው 95.6931 ሲሆን መሸጫው 101.4347 ነው።
የሌሎችም ሀገራት ምንዛሬ በትላንቱ ቀጥሏል።
ባንኩ ከቅዳሜ አንስቶ ተመሳሳይ የምንዛሬ ተመን እየተጠቀመ ነው።
እስካሁን ድረስ ዕለታዊ ምዛሬያቸውን ይፋ ያደረጉ የግል ባንኮችም ቢሆኑ የአብዛኞቹ ምንዛሬያቸው ከትላንት ብዙ የሚለይ አይደለም።
(የዛሬ ሐምሌ 30/2016 ዓ/ም የባንኮች ዕለታዊ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
🔈#መምህራን
" ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም !! " - የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር
በተለያየ ጊዜ በብሔራቸው አማካኝነትያ ከተለያዩ ክልሎች የተፈናቀሉ መምህራን በሥራ አጥነት ሳቢያ የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር (ኢመማ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለልጿል።
የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " ትግራይ ክልል ዝግ ሆኖ የቆዬ አካባቢ ነው፡፡ ከዚያ አንጻር የተፈናቀሉ መምህራን አሉ " ብለዋል፡፡
" የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሥራ ፈትተው የተቀመጡ መምህራን አሉ። የትግራይ ክልል መምህራን ሆነው ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያሉም አሉ " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡
" ኮይሃ የሚባል አካባቢም የትግራይ ክልል ተወላጆች ሆነው ግን አፋር ክልል ይሰሩ የነበሩ ተፈናቅለው ሥራ ፈትተው የተቀመጡ መምህራን አሉ " ሲሉ አክለዋል።
" በትግራይ ክልል ይሰሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጅ መምህራንም ቢሆኑ ተፈናቅለው ጎንደር የተቀመጡ አሉ " ያሉት አቶ ሽመልስ፣ መምህራን የትም አካባቢ ሂደው መስራት እንዳለባቸው ቢታመንም ችግሮች ግን ጎልተው እየተስተዋሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም እንዲሁ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ለመውጣት የተገደዱ መምህራን እንደነበሩ አስታውሰው፣ " ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም " ብለዋል፡፡
" በተለያዩ ጊዜያት ችግራቸው እንዲፈታ፣ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳውቀናል" ሲሉ ማኅበሩ ያደረገውን ጥረት አስረድተዋል፡፡
" ለትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቀናል፡፡ ትግራይ ክልልም የሰው ኃይል እጥረት አለና ቀጥራችሁ አሰሯቸው የሚል ሃሳብ ነው እያነሳን ያለነው " ብለዋል፡፡
መምህራን ያለምንም ፈቃዳቸው በተለያየ መንገድ ደመወዝ እንደሚቆረጥባቸው ፣ የደረጃ እድገት እየተሰራላቸው እንዳልሆነ ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።
ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር።
ነገ ማለትም #ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው።
ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት ዩሮ ነው ዛሬ 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መግዣ ፤ መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም ሆነ ነበር የዋለው።
በነገው ምንዛሬ ግን የአንዱ ዩሮ መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም ፤ መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም ሆኖ ይውላል።
ብዙም የምይነገርለት #የኩዌይት_ዳናር ደግሞ የአንዱ መሸጫ ከ315 ብር አልፏል።
በነገ ምንዛሬ አንዱ ዲናር በ298 ብር ከ8463 ሳንቲም እየተገዛ በ316 ብር ከ7771 ሳንቲም ይሸጣል ተብሏል።
ይህ መረጃ በ ' ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ' ያለውን ምንዛሬ የሚያሳይ ሲሆን የግል ባንኮች ደግሞ ምን ይዘው እንደሚመጡ ጥዋት ይታያል።
#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate
@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ : ክረምቱ እየበረታ ነው።
አሽከርካሪዎች ስታሽከረክሩ እየተጠነቀቃችሁ ይሁን።
ከቤት ሳትወጡ የመኪናችሁን ደህንነት በተለይ የዝናብ መጥረጊያ፣ ጎማ ሌሎችንም ነገሮች ሁሌም ማረጋገጥ እንዳትረሱ
የምትሄዱበትን መንገድ እየተጠነቃቃችሁ።
ወላጆችም ልጆቻችሁን ጠብቁ።
በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ክረምት በጣም ቁጥር እጅግ በጣም የሚሰቃዩት ሠራተኞች ናቸው በተለይም በስራ የመግቢያ እና የመውጫ ሰዓት ፥ ይኸው አመታት አልፈዋል ስለ ትራንስፖርት ችግር ሲጮህ ሲጮህ ምንም የተለየ መፍትሄ አልመጣም።
ዛሬም ሠራተኞች / ዜጎች ስራ ለመግባት እና ከስራ ወጥተው ወደ ቤት ለመሄድ፣ ለሌላም ጉዳይ ረጅም ሰዓት በብርድ እና በዝናብ ሰልፍ ላይ ያሳልፋሉ። መቼ ነው መፍትሄ የሚገኘው ?
ለሁሉም ግን ስትንቀሳቀሱ ጥንቃቄ አይለያችሁ።
በክልሎችም በዚህ ክረምት ወቅት ላይ ጉሙ ለመኪና መንገድ አስቸጋሪ ነውና ሹፌሮች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ።
ሰላም ወጣችሁ ሰላም ግቡ !
ክፉ አያግኛችሁ !
ቪድዮ ፦ ዛሬ ሐምሌ 26/2016 ዓ/ም አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
#Ethiopia : የውጭ ምንዛሬ ገደብ !
" የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ነው " - ገንዘብ ሚኒስቴር
መንግስት ከዚህ ቀደም ባሳለፈው ውሳኔ በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል፡፡
አሁንም ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ነው ብሏል።
በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ግን ከነማሻሻያው ከሐምሌ 21 ቀን 2016 ጀምሮ የተሻረ መሆኑን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ፦
- ለብሔራዊ ባንክ
- ለገቢዎች ሚኒስቴር
- ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ሴኩላር ነው።
ትላንትና ብሔራዊ ባንክ በነዳጅ የሚሰሩ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ያሉበት 38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱን አሳውቆ ነበር።
ብሔራዊ ባንክ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ እንደሆነ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ መሆኑንም ነበር የገለጸው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Sidama
በሲዳማ ክልል፣ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የውሀ ሙላት አደጋ የሞቱ ዜጎች 11 መሆኑን የሲዳማ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበራ ዊላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥ ዘጠኙ የሁለት አባወራ ቤተሰቦች ሲሆኑ አንዱ 5 አንዱ ደግሞ 3 ቤተሰቦቻቸዉን ማጣታቸውን ገልጸዋል።
አንድ ግለሰብ ከገበያ ሲመለስ ከተራራ የወረደ ናዳ ላዩ ላይ በማረፉ ለህልፈት እንደዳረገው ገልጸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ በቡራ ወረዳ ወንዝ ሞልቶ ከአቅጣጫው ውጭ በመፍሰስ በአካባቢዉ ያለ ቤት ውስጥ በመግባት 2 ልጆችን ህይወት መቅጠፉን ተናግረዋል።
ከአካባቢው ተራራማነትና ያለማቋረጥ ከዘነበው ዝናብ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ተጨማሪ አደጋዎች ይከሰታሉ ተብሎ ስጋት አለ።
ይህንንም ተከትሎ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ ፣ የጤና ቢሮና ሌሎች ተቋማት የተወጣጣ ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደስራ ተገብቷል ብለዋል።
" ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው " ተብለው ከተለዩ ስድስት ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎችን የማውጣት ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል።
ከቀያቸዉ ከተነሱትን ራቅ ያለ ቦታ ዘመድ ያለው ወደዛ ሲሄድ ሌሎች በት/ቤቶች ፣ በቤተእምነቶችና መሰል ቦታዎች እየተጠለሉ መሆኑን ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaHW
@tikvahethiopia
Hey Mobile !
•Playstaion 5 Slim, 76,000 Birr
•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 42,000 Birr
•Meta Quest 2, 45,000 Birr
•Meta Quest 3, 78,000 Birr
Contact
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
@heyonlinemarket
#Infinix_Note40_Pro_Plus
ኢንፊኒክስ አዲሱን የኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልኩን እጅግ ደማቅ በሆነ የጌሚኒንግ እና የሙዘቃ ዝግጅት በቃና ስቱዲዮ ለተጠቃሚዎች አስተዋውቋል!
በተለይም ለጌመሮች እና ለሙዚቃ አድናቂዎች የተለየ ነገርን ይዞ የመጣው አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ ነሀሴ 4 በቃና ስቱዲዮ በአይነቱ ለየት ባለ ዘግጅት አዲሱን ስልኩን አንዲሁም የኢንፊኒክስ ቲቪ፣ ላፕ ቶፕ ፣ ስፒከሮች፣ ስማርት ዋች እና ኤር ፖዶችን ለተጠቃሚዎች አስተዋውቋል፡፡ አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ የኔትወርክ ቴክኖሊጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን በጌመሮች እና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ስራዎችን በስልካቸው በሚከውኑ ስዎች ተመራጭ የሆነውን የ Mediatek Dimesnty 7020 ፕሮሰሰርን የተገጠመለት ፈጣን ስልክ ነው፡፡
#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
#FederalGovernment #TPLF
" አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " - የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን
የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በህወሓት ጉዳይ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህ መግለጫ ፦
- ህወሓት እንዴት ሕጋዊ ሰውነቱን ሊያጣ እንደቻለ ወደኃላ መለስብሎ አስታውሷል ፤
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈጸም የፌዴራል መንግሥት በስምምነቱ የገባው ግዴታ የህወሓት የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሣ ሂደቱን የማሣለጥ ኃላፊነት (የስምምነቱ አንቀጽ 7 (2) (C)) እንደሆነ ፤
- የፌዴራል መንግሥት የህወሓትን የሕግ ሰውነት እና የምዝገባ ጉዳይ በተመለከተ በፕሪቶሪያ ስምምነት ውስጥ የወሰደው የተለየ ኃላፊነት ወይም ግዴታ እንዳልነበር፤
- ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት እንቀጽ 7 (1) (A) መሠረት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት፣ ሕጎች፣ የፌዴራል ተቋማትን እና ሌሎች ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ሥልጣን የማክበር ግዴታ መግባቱም ፤ ስለዚህ ሕወሐት የሀገሪቱን የፖለቲካ ፖርቲዎች የምዝገባ ሕግ እና የምርጫ ቦርድን ሥልጣን በማክበር የመሥራት ግዴታ እንዳለበት ... ገልጿል።
የፌዴራል መንግሥት በመግለጫው ፤ ህወሓት ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት ስለተኬደባቸው መንገዶች ፣ ውይይቶች ፤ በህወሓት እና ምርጫ ቦርድ በኩል ስለተነሱት ልዩነቶች አብራርቷል።
ድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና እንዲኖረው ለቦርዱ የትብብር ጥያቄ ስለማቅረቡም አስታውሷል።
እንዲሁም አዋጅ እስከማሻሻል በደረሰ እርምጃ ድርጅቱ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገባ ለማድረግ የተኬደበትን ርቀት ገልጿል።
ይህን ተከትሎ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና ለማግኘት የሚጠበቅበት የፓርቲ ሰነዶቹን ማለትም የፓርቲውን ፕሮግራም እና ሕገ ደንብ፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቅረብ በተሻሻለው አዋጅ መሠረት ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት እንዳገኘ አሳውቋል።
በመሆኑም " የምዝገባ እና የህግ ሰውነትን ጉዳይ በዚህ በመቋጨት፤ የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ሰላምን በማጽናት፣ በመልሶ ግንባታ እና በልማት አጀንዳ ላይ ሊሆን ይገባል " ብሏል።
ፌዴራል መንግሥት" አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Ethiopia
አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ነው።
የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው።
በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል።
ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም።
የሚያስፈልገው ሁሉም የአትሌቲክሱ ቤተሰብ ቁጭ ብሎ በእርጋታ መክሮ ፤ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው።
ሁሉም ዜጋ በየፊናው የተሰማውን ብስጭት፣ ንዴት እየገለጸ ነው። ይህ የሚጠበቅ ነው። ምክንያት ? ሀገሩ ነው፣ ክብሩ ነው። የሚጠብቀውን ሳያገኝ ሲቀር ህዝቡ ያዝናል ፣ይበሳጫል።
እውነትም " ለሀገራችን ክብርና ፍቅር አለን " የሚሉ የአትሌቲክሱ አካላት በእርጋታ ፣ በንግግር ችግሮች እንዲፈቱ ያድርጉ።
ይህም በመሪዎች እና አመራሮች ደረጃ " ለጠፋው ውጤት ፣ ዝቅ ላለው የህዝባችን ክብር ኃላፊነት እንወስዳለን ፤ ይህ የመጣው ስላልሰራን ነው " ብሎ ቦታ መልቀቅን ፤ ለሌላው እድል መስጠትን ያካትታል።
በአትሌቶች ዘንድም የውጤታችን መጥፋት እንዴት እንደተከሰተ ፤ ምናልባት የተሻሉ አትሌቶችም ካሉ ለነሱ ቦታ እያስረከቡ መሄድም እንዲቻል በጥልቀት መገምገም ይገባል።
በአትሌቶች እና አሰልጣኞች መካከልም ተግባብቶ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ በቡድን አለመስራት ችግርም ካለ መፈተሽ አለበት።
ከምንም በላይ ግን ዘርፉን የሚመሩትን አካላት እና እዛ አካባቢ ያሉትን በሙሉ በጥልቀት መገምገም ይገባል።
በአጠቃላይ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።
ህዝቡ የሚፈልገው ክብሩ እንዲመለስለት ብቻ ነው ፤ ሙያውን የሚያውቅ በቦታው ተገኝቶ ለውጥ አምጥቶ በሀገሩ ውጤት ተደስቶ ማየት ነው።
የሚዲያ ምልልስ ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ በዚህ መሃል ደግሞ የሚፈጠር የውጤት ውድቀት ህዝብን ፍጹም አይመጥንም።
ጉዳዩ ሙያዊነውና ለባለሙያዎቹ እንተወው ፤ እውነት ግን " የሀገራችን ክብር ይመለከተናል " የሚሉ የሀገር ጉዳይ ብቻ አላማቸው ከሆነ ሌላ ፍላጎት ከሌላቸው ጭቅጭቅ እና ንትርክ ትተው ቁጭ ብለው መነጋገር አለባቸው። ኃላፊነት መውሰድም አለባቸው።
በአሁኑ ውጤት ያልተበሳጨ፣ ያላዘነ ፣ አንጀቱ ያላረረ ዜጋ የለም በዚህም ደግሞ በስሜታዊነት አስተያየቱን እየሰጠ ነው። ለውጥ እንዲመጣ ወደ ክብራችን እንድንመለስ ጥያቄ እያቀረበ ነው።
ነገር ግን አንዳንድ አስተያየቶችም ጥንቃቄ ይፈልጋሉ የአትሌቶችን ስነልቦና እንዳይጎዳ።
ባለፈው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና " ያለእናተ ሰው የለም ፤ ጀግኖች " እያልን ያወደስናቸውን ልጆች ዛሬ ውጤት በመጥፋቱ በብስጭት እና ሀዘን ስሜት ያልተገባ ቃል እንዳንናገር መጠንቀቅ ይገባል።
ዳግም ህዝቡ በሚኮራበት #አትሌቲክስ እንዳያዝን እና እንዳይበሳጭ ተነጋግሮ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።
ህዝቡ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ክብሩ እንዲመለስለት ይፈልጋል፤ አራት ነጥብ !
ስር ነቀል ለውጥ ለኢትዮጵያ 🇪🇹 አትሌቲክስ !
#የሐሳብ_መድረክ @nousethiopia
@tikvahethiopia
#TPLF
ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።
ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።
" በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል " ሲል ገልጿል።
ይህን ተከትሎ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርበናል " ብሏል።
ሆኖም " ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎችና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ' በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ' መልሷል " ሲል ገልጿል።
ይህን ተከትሎ ህወሓት " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆኗል " በማለት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበልም " ሲል አሳውቋል።
" በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ካቀረብነው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው " ሲልም አክሏል።
" የቦርዱ ውሳኔ ህጋዊ ሰውነቴን ወደነበረበት እንዲመለስ የቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ ፤ የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች የሚጭንብን በመሆኑ አልተቀበልኩትም " ያለው ህወሓት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድልን መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እናከናውናለን " ብሏል።
የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ፦
- TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ አዋጅ መሻሻሉ፤
- አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ የነበረበትን ማለትም ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው፤
- የአስፈጻሚውን ስራ 100% መሰራቱን፤
- ፓርቲ ለፓርቲ ፤ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠ፤
- TPLF ምርጫ ቦርድ ሄዶ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ፤ ይህን ባያደርግ ምርጫ ቦርድም ካልተቀበለው፤ TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
➡ በምርጫ ሊሳተፍ እንደማይችል ፤
➡ መንግሥትም ሊሆን እንደማይችል ይህ ደግሞ ተመልሶ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነ፤
- ተመልሶ ጦርነት ውስጥ ከመግባት በተበጀው ሕግ ፤ በተደረሰው ስምምነት ህወሓት የቀረውን ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ እንዳለበት መግለጻቸው ይታወሳል።
#Ethiopia #TPLF #TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Tigray #TPLF
"ሊካሄድ በታቀደው ጉባኤ አልሳተፍም ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ዓርብ ነሀሴ 3/2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ለድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ተኽለብርሃን ኣርኣያ በፃፉት ደብዳቤ በጉባኤው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል።
ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ በጣሰው ጉባኤና የምዝገባ ሂደት እንደማይሳተፉ በመግለፅ " ህወሓት መዳን የሚችለው አባላቱና አመራሩ በሚያካሂዱት ጤናማ እንቅሰቃሴ ነው " ሲሉ አስታውቀዋል።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia
#Ethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል ጀመረ።
ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ጀምሮ ሥራ ላይ በዋለው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁ.01/2016 መሠረት የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመከፈት የሚፈልጉ የሥራ ፈቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ጥሪ አቅርቧል።
በገበያ ላይ ተመሥርተው የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መሸጥና መግዛት የሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲቋቋሙ በተፈቀደው መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ እንዲሁም የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ ቢሮ መስፈርቱን አሟልተው ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ሲያገኙ መክፈት ይችላሉ፡፡
የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት የሚያስፈልገው የካፒታል መጠን እንዲሁም ሌሎች ለሥራው የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ከላይ ተያይዟል።
ካፒታልን በተመለከተ በመመሪያው ላይ የሰፈረው ይህ ነው ፦
➡ Fulfills the minimum capital requirement of Birr 15 million and is able to provide a Security Deposit of Birr 30 million to be placed in a blocked account (which can be interest-earning) at any bank:
ባንኩ " የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች መቋቋም የውጭ ምንዛሪ ገበያን መሠረት ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚሹ ደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት እንደሚረዳ እሙን ነው " ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ፣ " የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ የሥራ ፈቃድ መስጠታችን የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመክፈትና ዘርፉን በቀጣይ ዓመታት ከዓለም ምርጥ ተሞክሮዎችና አሠራሮች ጋር የተመጣጣነ እና ተወዳዳሪ የሆነ ለማድረግ የጀመርነውን አዲስ ምዕራፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጀመረውን ስትራቴጂካዊ የሆነ ለውጥ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት መነሣሣቱን የሚያመለከት ነው " ብለውታል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#ትግራይ
" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ፅ/ቤቱ
በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ወረዳ የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።
የመሬት መደርመስ አደጋው በሰው ህይወት ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም የእህል አዝርእት ሙሉ በሙሉ አውድሟል።
የመሬት የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው ሀምሌ 29/2016 ዓ.ም በዓድዋ ወረዳ በታሪካዊትዋ የይሓ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።
የወረዳው የቁጠባ ዘርፍ ፅ/ ቤት ፤ " በአደጋው የ21 አርሶ አደሮች የተዘራ እህል ሙሉ በሙ ወድሟል " ብሏል።
' ደምባፍሮም ' በተባለች መንደር የተዘራው ስንዴ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተመላክቷል።
" ከአሁን በፊት በትግራይ ያልተለመደ የመሬት የመደርመስ አደጋ አሁን አሁን መታየት ጀምሯል " ያለው ፅ/ቤቱ " አርሶ አደሩ የክረምቱን ሀያልነት ከግምት ያስገባ ሁሉን አቀፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ " ሲል አሳስቧል።
ዘንድሮ በትግራይ ክልል ያለው ኃይለኛ ክረምት በንብረትና በእንስሳት አደጋ በማደረስ ላይ ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት በክልሉ የራያ ጨርጨር ወረዳ ዝናብ ያስከተለው ኃይለኛ ጎርፍ በ106 የቤት እንስሳትና በ11 ሄክታር የእርሻ መሬት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
በጎርፉ 91 እንስሳት ሲወሰዱ ፣ 15 ቱ የአካል ጉዳት ደርሷቸዋል። በ11 ሄክታር የተዘራ እህል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
#TikvahEthiopiaFamilyMK
@tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።
የነሀሴ ወር 2016 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።
የነዳጅ ማደያዎችም ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንደታዘዙ አመልክተዋል።
@tikvahethiopia
ዓለም ወደለየለት ቀውስ ውስጥ ትገባ ይሆን ?
የፍልስጤም እና እስራኤል ጦርነት መቆሚያ ማጣቱን ተከትሎ በየጊዜው አዳዲስ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ፤ መካከለኛው ምስራቅ እየታመሰ ነው።
ምንም ሰላማዊ መፍትሄ በመጥፋቱ አሁንም በጦርነቱ ሰዎች እያለቁ ነው።
" ፍልስጤምን አትንኳት " የሚሉና ሃማስን የሚደግፉ ኃይሎችም እስራኤልን በሮኬት / ሚሳኤል መደብደብ አላቋረጡም።
ከሰሞኑን ግን በኢራን ቴህራን ውስጥ ለአዲሱ የኢራን ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት የተገኙት የሐማስ የፖለቲካ ኃላፊ እስማኤል ሃኒያ እንዲሁም ከዛ ቀድሞ የሊባኖሱ ሂዝቦላ ቡድን ከፍተኛ አዛዥ ፉአድ ሽኩር መገደላቸውን ተከትሎ የለየለት ውጥረት አይሏል።
እስራኤል የሐማሱን ሃኒያን ግድያ ስለመፈጸም ወይም አለመፈጸሟን በይፋ ያለቸው ነገር የለም።
ኢራን ግን እስራኤል ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃት ዝታለች።
እስራኤልን ክፉኛ ሳትቀጣት አርፋ እንደማትቀመጥ አሳውቃለች።
የእስራኤል ባለልስጣናትም የማይቀር ጥቃት ከኢራን እና ከሂዝቦላህ እንዳለ በመናገር መዘጋጀታቸውን እያሳውቁ ነው።
አሜሪካም ፤ እስራኤልም በቀጣዮቹ ሰዓታት የኢራን ጥቃት ሊኖር ይችላል የሚል ግምገማ አላቸው።
" እስራኤልን ፍጹም አትንኩብኝ " የምትለው አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ እና አካባቢው የተሰማራውን መከላከያዋን ለማጠናከር የጦር መርከቦች እና ተዋጊ ጄቶችን ልካለች።
የተላያዩ ሀገራት ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው። የሚመጣው ነገር ያስፈራልና ከሊባኖስ ለቃችሁ ውጡ እያሉ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ለጊዜው ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዳይሄዱና አርፈው እንዲቀመጡ እያስጠነቀቁ ናቸው።
በአጠቃላይ ያሉት ሁኔታዎች ከባለፈውም ጊዜ በባሰ መልኩ አስፈሪ ናቸው።
አንዳንድ ሀገራት ኢራንን " እባክሽ አረጋጊው ! " ብለው ቢማጸኗትም " ቅጣቱ የማይቀር ነው " የሚል አቋም እንደያዘችና ጥቃቱም ከፍተኛ እንደሚሆን እየተነገረ ነው።
በሌላ በኩል ፥ ፍልሥጤም ውስጥ በየዕለቱ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን እስካሁን በ10 ወራት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 583 መሻገሩን በጋዛ የሚገኘው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። - @thiqaheth
@tikvahethiopia
#Tigray : በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በተደራጀ ገለልተኛ በተባለ አንድ አጥኚ ቡድን የክልሉን ሁኔታ በተመለከተ ጥናት ተደርጎ ነበር።
በዚህም ፦
➡ በክልሉ ሕገወጥነት መስፈኑ እና ይህም ወደ ስርዓት አልበኝነት የሚሄድበት ዕድል ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።
➡ የመንግሰት መዋቅር በአንድ ፓርቲ መጠለፉን ያመለክታል።
➡ የክልሉ ህዝብ እና መንግስት ሀብት በግለሰቦች ፣ የውጭ ዜጎች ጭምር እየተዘረፈ እንደሆነ ያሳያል።
➡ የፍትህ ስርዓቱ ተአማኒነት ማጣቱን ያመለክታል።
➡ በህዝቡ ዘንድን ተስፋ ማጣትና ስደት መንሰራፋቱ ይኸው ጥናት አሳይቷል።
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ መንግስት ስራው እንዳይሰራ መቸገሩን ገልፀዋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ ፤ " የክልሉ አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ከመስራት ይልቅ፥ ችግሮች በመዘርዘር ተጠምዷል " ብለዋል።
" እኔ እኮ በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር በትግራይ ችግሮቹ ተዘርዝረው እየተነገሩ ያሉት፣ ችግሮቹን ሊፈቱ ስልጣን በያዙ ሰዎች ነው። ኃላፊነታችሁ ልትወጡ ይገባል " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ተናግረዋል። #ዶቼቨለ
@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹
ሀገራችን ኢትዮጵያ በወንዶች የ10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር በበሪሁ አረጋዊ አማካኝነት የብር ሜዳሊያ አመጣች።
ዮሚፍ ቀጀልቻ 6ኛ ፤ ሰለሞን ባረጋ 7ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
#ኢትዮጵያ❤
More - @tikvahethsport
@tikvahethiopia
🔈#የወላጆችድምጽ #AddisGlobalAcademy
“ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” - ወላጆች
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው “ አዲስ ግሎባል አካዳሚ ‘ለኮሪደር ልማት ያስፈልጋል ’ ” በመባሉ ልጆቻቸውን ሌላ ት/ቤትም ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ወላጆችና ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
ሌላ ት/ቤቶች እንዲያስመዘግቡ የተነገራቸው ሰሞኑን እንደሆነ፣ ሌሎች ት/ቤቶች ምዝገባ በማጠናቀቃቸው ልጆቻቸውን ማስመዝገብ እንዳልቻሉ የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል።
“ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ውሳኔውን ቀድመው ማወቅ እንደነበረባቸው ገልጸው፣ ምዝገባ እየተገባደደ ባለበት ወቅት ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ስላልቻሉ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረው የትምህርት ቤቱ በበኩሉ፣ ልማቱን ባይቃወምም ቢያንስ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ፣ የወላጆች ቅሬታ ትክክል መሆኑን ገልጿል።
አንድ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አካሌ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ/ም የቦሌ ክፍለ ከተማ አካላት ትምህርት ቤቱ እንደ ት/ቤት እንደማይቀጥል ገልጸው፣ ውሳኔውን ለወላጆች እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ እንደሰጧቸው አስረድተዋል።
ት/ቤቱም ለወላጆች ጥሪ አድርጎ ‘ት/ቤቱ ለልማት ይፈለጋል ባዮቹ’ ራሳቸው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ማድረጉን፣ የተማሪ ወላጆችም ውሳኔው ዱብእዳ ሆኖባቸው ብዙ ጥያቄዎች እንዳነሱ ገልጸዋል።
የወላጆችም ቅሬታ ውሳኔው የአጭር ጊዜ በመሆኑ ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ስለማይችሉ እንጂ ልማቱን መቃወም እንዳልተቃወሙ ያስረዱት እኝሁ አካል፣ “ ብዙ ወላጆች እያቀሱና እያዘኑ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል።
“ እውነትም ብዙ ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ጨርሰዋል። በጥራት ችግርም ፈቃዳቸው የተወሰደባቸው ብዙ ትምህርት ቤቶች ስላሉ ጫናዎች አሉ ” ሲሉም ተናግረዋል።
“ ለምሳሌ ዛሬ አንዷ ወላጅ አንድ ት/ቤት ልጇን ልታስመዘግብ ሂዳ ስታለቅስ አይቷት ዳይሬክተሩ ደወለልኝ። እጅግ ልብ የሚሰብር ነገር ነው የሆነው ” ነው ያሉት።
“ በትምህርት ቤቱ ወደ 1,300 የሚሆኑ ተማሪዎች፣ ከ200 በላይ ሠራተኞች አሉ ” ብለው፣ መንግስት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት እንደሚበተኑ ቢገልጽም በተለይ ተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው የሥነ ልቦና ጉዳት ሊጠን እንደሚገባ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት ከመንግስት አካላት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ሙከራው ይቀጥላል።
(ክፍለ ከተማው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ግብር ለመክፈል መጉላላት ሳይጠበቅብዎ በቴሌብር ሱፐርአፕ onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ባሉበት ቦታ ሆነው በስልክዎ ይክፈሉ!
ሁለቱን የከተማ መስተዳድሮች ጨምሮ የአብዛኛዎቹ የክልል ገቢዎች ግብር በቴሌብር መክፈል ተችሏል፡፡
ሥራን በክብር
ግብርዎን በቴሌብር !
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ !
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ /channel/EthiotelecomChatBot 24/7 ያግኙን!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba
ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 ሰዎች መሞታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ከሟቾች በተጨማሪ 4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
አደጋው የደረሰው 7 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ ደብል ፒካአፕ ተሽከርካሪ ከቆመ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ መሆኑን አስረድተዋል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎችን ከተሽከርካሪው በማውጣት ወደ ህክምና ተቋም እንደላኩ ያወሱት አቶ ንጋቱ ፣ ህይወታቸው ያጡትን ሰዎች አስከሬን ለፖሊስ እንዳስረከቡ፣ ዝርዝር የአደጋ ምክንያት ደግሞ በፖሊስ እየተጣራ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ ትላንት ምሽት 4 ሰዓት ከ43 ደቂቃ ላይ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 አደይ አበባ አካባቢ በሚገኝ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ እስት አደጋ እንደደረሰ ተናግረዋል።
➡️ አደጋው የደረሰበት ፋብሪካ ፦ DN የጨረቃ ጨርቅ ፋብሪካ
➡️ ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
➡️ በመጋዘን ውስጥ የነበረ የጥጥ ክምችት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
➡️ የእሳት አደጋው ወደ ፋብሪካው ማሽነሪዎችና ሌሎች ጨርቃ ጨርቆች ላይ ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል።
➡️ አደጋውን ለመቆጣጠር 3 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ፈጅቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
ኤቲኤም ካርድ ያዝኩ አልያዝኩ ብሎ ሐሳብ ቀረ!
የአቢሲንያ ዲጂታል ቪዛ ካርድዎን በመጠቀም ስልክዎን በማስጠጋት ፖስ ላይ ክፍያ መፈጸም እንዲሁም ከአቢሲንያ ኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! /channel/BoAEth
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all